Get Mystery Box with random crypto!

ከ34 አመት በኃላ የእዉቀት አባቶቹን ፈልጎ ያገኘዉ ዶክተር!!! በወልቂጤ አሁን ላለሁበት መሠረቶ | ethio Nure( ኑሬ ረጋሳ)

ከ34 አመት በኃላ የእዉቀት አባቶቹን ፈልጎ ያገኘዉ ዶክተር!!! በወልቂጤ

አሁን ላለሁበት መሠረቶቼ በመሆናቹህ ማመስገን እወዳለሁኝ ዶክተር ጅላሉ አስመራ።

ለመጀመሪያ ጊዜ ነዉ አስተምረናቸዉ ትልቅ ደረጃ ደርሰዉ ከነበሩ ተማሪዎቻችን መካከል ዶክተር ጅላሉ አስመራ ከአለንበት ቦታ አሰባስቦ ምሳ ግብዣ ያደረገልን ይላሉ መምህራኖቹ።

ዛሬ ጡረታ ወጥተን ባለንበት ጊዜ የቀድሞ የቀለም ትምህርት ዉለታዉን አስታዉሶ እንዲህ ፈልጎን ሲመጣ ደስታዉ ከምንጠብቀዉ በላይ ነዉ ይላሉ መምህራኖቹ።

ዶክተር ጅላሉ አስመራ አንደኛ ደረጃ ራስዘስላሴ ትምህርት ሁለተኛ ደረጃ የቀድሞ ጎሮ ወይም የአሁኑ ያበሩስ ትምህርት ቤት በስነ ምግባር የተመሰከረለት ፣ ጎበዝ ተማሪ ፣ መምህራን በማክበር፣ ትሁትና የሚባለዉን ሁሉ በሀላፊነት የሚወጣ ተማሪ ነበር።

ዛሬ እኛን ሰብስቦ ስላጫወተን ምንኛ ደስ እንዳላቸዉ መምህራኖች ተናግረዋል።

ዶክተር ጅላሉ አስመራ በወልቂጤ ከተማ ተወልዶ ያደገ ሲሆን ከ34 አመት በፊት አንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ያስተማሩት መምህራኖችን ከአሜሪካ ወልቂጤ በመምጣት የምሳ ግብዣና ለእያንዳዳቸዉ 20 ሺህ ብር አበርክቶላቸዋል።

የእዉቀት አባቶችን አፈላልጎ ቆየት ያሉ ገጠመኞቻቸዉን እያስታወሱ የምሳ ፕሮግራሙን እየተቋደሱ እየትዝናኑ ዉለዋል።

መምህራኖቹ ከአስተማሩት ዶክተር ጅላሉ ጋር የወደኋላዉን ታሪክ እያስታወሱ ቁም ነገርና ገጠመኞቻቸዉን እያነሱ ጥሩ ቆይታ አድርገዋል።

የቀለም ትምህርት ባለዉለታዎቹን የዘላለም መሰረቶቻችን ናቸዉና ከዶክተር ጅላሉ ሁሉም ሊማርና የቀለም አባቶች የማፈላለግ ባህላችን እናድርግ!!!

አሁን ላለሁበት መሠረቶቼ በመሆናቹህ ማመስገን እወዳለሁኝ። (Thank you) በማለት ለየት ያለ ፕሮግራም አዘጋጅቶ የቀለም አባቶቹሁን አመሰግኗል ዶክተር ጅላሉ።

ቪቫ ዶክተር ጅላሉ አስመራ !!!