Get Mystery Box with random crypto!

ኸሚስ ምሽት 'የሸህ ሁሴን ትንቢት እና የኑዕማን ትቢት' (ኑዕማን ኢድሪስ) ከእለታት በአንዱ | Nuiman Edris Official

ኸሚስ ምሽት

'የሸህ ሁሴን ትንቢት እና የኑዕማን ትቢት'
(ኑዕማን ኢድሪስ)

ከእለታት በአንዱ ቀን አመለሰት ሙጬ ድል ባለ ሰርግ ተሞሸረች። ሃገር ጉድ ብሎ ተነጋገረ። 'ሰይፉን ትታ እንዴት ቴዲን አገባች?' ተብሎ ተወራ።

በዉጭ ሰዉ ወሬ የተነሳ አብይ አህመድ ማለቴ ቴዲ አፍሮ በሰይፉ ላይ ቂም ያዘበት። የጦፈ ጸብ ዉስጥ ገቡ። ቴዲም ሚስቴን አድርጋሃታል፤ ማዕድኗን ዘርፈሃታል፤ ፍትሃዊ አልነበርክም፤ ስልጣኑን ለኔ መልቀቅ አለብህ፤ ሰሜን እዝን አጥቅታሃል  በሚል በሰይፉ ላይ ይዘምትበታል።

ሰይፉም የዋዛ ስላልነበር። ጠጉር አልባ ጭንቅላቱን በትክክል ባለማሰራቱ ከመደራደርና ከመወያየት ይልቅ ወደ ጦርነት ይገባሉ። ሁለቱም ሰራዊቶቻቸዉን አሰማርተዉ አመለሰት በተባለ ቦታ ላይ ይገጥማሉ።

ጦርነቱ ለአመታት ዘለቀ። ከሁለቱም ወገን ብዙ ወታደሮች አለቁ። በዚህ መሃል አክቲቪስቶች (ነገር ጎሳሚዎች) 'የሸህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢት  ሰይፉ ወሎ ላይ ይሞታል' ቢሉም ሰይፉ ግን ያለዉን ሃይል ተጠቅሞ ደብረ ብርሃን ማለቴ አንሶላ እስከመጋፈፍ ደርሷል ይባላል

በስተመጨረሻም ድርድር አካሂደዉ ሰይፉ (ህወሃት) ትጥቁን ፈቶ ቴዲ ከአመለሰት ሶስት ልጆችን ወለደ።

እንግዲህ የዚች ሀገር ታሪክ ይህ ነዉ። ይቀጥላል...

የጁንታ መጥፊያዉ ወሎ ላይ ነዉ ሲሉ
ደ'ሞ ቀየር አርገዉ በራያ ሲምሉ
አብይን ደግፈዉ ሰሜኑን ሲያጥላሉ
እኚህ ዩቱዩበር፤
እኚህ አክቲቪስቶች፤
ይህን የዋህ ህዝብ ገንዘቡን ቀፈሉ

ቀፋይ ሁላ ..