Get Mystery Box with random crypto!

ኸሚስ ምሽት 3 (ኑዕማን ኢድሪስ) አንቺዬ... ከቤትሽ ብመጣ ምሽቱ አሸብርቋል ቄጤማዉ ጉዝጓዙ | Nuiman Edris Official

ኸሚስ ምሽት 3
(ኑዕማን ኢድሪስ)

አንቺዬ...
ከቤትሽ ብመጣ
ምሽቱ አሸብርቋል
ቄጤማዉ ጉዝጓዙ
በጭሳጭስ ደምቋል

ከረከቦትሽ ስር
በሂጃብ ተዉበሽ
ዚክሩ ሶለዋቱ
በሃይባ ተከበሽ

ኸሚሱ አጅቦኛል
ዉበትሽ ማርኮኛል
ይዣለሁ ማብሰልሰል

ሰዉን መላዕክቱን
እንዲህ ያማለልሽዉ
ወሎዬ ነሽ መሰል

አጀብ አጀብ
በቴሌግራም ፦ telegram.me/Nuiman_9