Get Mystery Box with random crypto!

ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ነዉ። 2ኛቆሮ፤11፤28 ቤተ ክርስቲያን ዘለዓለ | ንቁ'የመዳን ቀን ዛሬ ነዉ!

ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ነዉ።
2ኛቆሮ፤11፤28 ቤተ ክርስቲያን ዘለዓለማዊ ልጅነትን የምናገኝባት፤ ስንታመም የምታክመን ስናዝን የምታፅናናን ዕዉቀት የምትመግበን ስንሳሳት የምታርመን ስንቆሽሽ የምታጥበን የክርስቶስ ማደሪያ የሆነች መላዕክቶች የሚወጡባትና የሚወርዱባት በስዉር ያሉ ቅዱሳንና ምዕመናን መሰብሰቢያ ናት። ዛሬ እኔና መሰሎቼ በሰራነዉ ኀጢአት ማቅ ለብሳ አዝናለች ከቅድስት ቤተክርስቲያን ቀጥሎ የክርስቶስ ማደሪያ ሰዉነታችን ነበረ። ሰዉነታችንን በኀጢአት ረክሶ የእርኩስ ማደሪያ በመሆኑ መድሃኒቱን ከዉስጣችን አሳደነዋል ሐዋ፤9፤4-5 በዉጪ ያሉትን አሳዳጆችና ገዳዮችን ብቻ ተመልካች አንሁን ወደ ዉስጣችን ልንመለከት ይገባናል የአመፅ ልጆች ሆነን በሰራነዉ ኀጢአትና ራሳችንን በኀጢአት በማርከሳችን ነዉ እንዲህ የመከራ ባለቤት የሆነችዉ የትኛዉም ደፋር ነኝ ብሎ የሚያሰብ ቅድስት ቤተክርስቲያን ቅጥር ዉስጥ ሲጋራ ጫት ዝሙት ሆነ ሌሎች እርኩሰትን አይሰራም ለምን? ቅድስት ቦታ እንደሆነች ስለምናዉቅ ግን ራሳችንን በኀጢአት ለማርከስ ምንም ሳንፈራ ኀጢአትን እንሰራለን በዚህም ምግባራችን መድሃኒታችንን ስላስመረርነዉ ተለይቶን ኀጢአት ስለነገሰብን ነዉ ዲያቢሎስ እርስ በእርስ እያለያየን ያለዉ እባካችሁ ሁላችንም የየራሳችንን ኀጢአት እያሰብን ልናለቅስ ይገባል ዓይናችንን ከሰዉ ላይ ልናነሳ ይገባል ሉቃ፤18፤9-14 ወደ ዉስጣችን ልንመለከትና ከልብ በሆነ ሀዘን የእግዚአብሔርን ይቅርታ ልንፈልግ ይገባል 2ኛቆሮ፤6፤12-20 አምላክ እንዲታረቀን ልንጾም ልንጸልይ ይገባናል። መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለም ከሰማይ በታች ካሉ ከክፉዎች አጋንንት ጋር ነዉ እንጂ ኤፌ፤6፤12 አንደበታችሁን ከክፉ ከልክላችሁ 3ቷን ቀን በአግባቡ ተጠቀሙባት። ሮሜ፤12፤17-19

@Nkuyemedankenzare