Get Mystery Box with random crypto!

​​​​ ሮ ማ ን የመጨረሻዉ ክፍል ... | NK_Etertainment

​​​​ ሮ ማ ን

የመጨረሻዉ ክፍል

...<<ለዛሬ የቀጠርኩህ በሲጋራ ማጨስና ጉዳቱ ዙሪያ ለጤናችን ፕሮግራም ካንተ ጋር ቃለ መጠይቅ ለመስራት ስለፈለግኩ ነው››

የመጨረሻዎቹን ቃላት በውል አላዳመጥኳቸውም፡፡ የተቀመጥኩበት ወንበር ወደ ውስጥ ይዞኝ የገባ መስሎኝ ከንፈሬን በጥርሴ እንደነከስኩ አይኖቼን በሀይል ጨፈንኳቸውና በዝምታዬ ውስጥ ራሴን ገደልኩ፡፡
ከተቀበርኩበት ድንገተኛ ሰመመን ስነቃ ሮማን በእጇ የያዘችውን የድምጽ መቅጃ እያሻሸች በድንጋጤ እየተመለከተችኝ ነበር፡፡
‹‹ ደህና ነህ? ›› አለችኝ፡፡ ጭንቅላቴን በአዎንታ ነቀነቅኩላት፡፡ ከዚያም እጄን ወደኪሴ ሰድጄ የተጨማተረ ሲጋራ መዘዝኩና አቀጣጠልኩ፡፡ ወደ ውስጥ የሳብኩት ጭስ ከአፌ እየወጣ አየር ላይ ተበታትኖ ወዲያና ወዲህ ሲቅበዘበዝ ሳይ እምባዬ መጣ፡፡

መድረሻውን የማያውቀው ጭስ የኔ ህይወት ተምሳሌት መሰለኝ፡፡ እንዲያውም ይህ የሲጋራ ጭስ መነሻውን ያውቃል፡፡ እኔ ግን መነሻና መድረሻዬን የማላውቅ፣ ከየት መጥቼ ወዴት እየሄድኩ እንደሆነ ያልተረዳሁ ምስኪን ሠው ነኝ፡፡ ሲጋራውን ጠላሁት፡፡ ጭሱን ማየት ቀፈፈኝ፡፡

መሬት ላይ ጣልኩትና በጫማዬ ደፈጠጥኩት፡፡ ኪሴ ውስጥ የነበረውን ሁሉ እያወጣሁ ስብርብር አደረግኩት፡፡
ነፍሴ ስትረጋጋ ታወቀኝ፡፡ በዛፎቹ መካከል እየተሽሎከለከ እኛ ወዳለንበት ጎጆ ቤት የሚገባው ነፋስ አዲሱን የህይወቴን ገጽ መግለጥ ጀመረ፡፡
ከዚህ በፊት የማላውቀው አዲስ ስሜት ውስጤ ገብቶ ቦታ ሲፈልግ አገኘሁት፡፡ ልቤን ሰጠሁት፡፡ በደስታ ተሞላሁ፡፡ መጮህ አማረኝ፡፡ ሮማን በሁኔታየ ግራ ተጋብታለች፡፡ ከአፏ ቃል ሳታወጣ በጭንቀት እየተነፈሰች የማደርገውንና የምሆነውን ትከታተላለች፡፡
የውስጤን ስሜት ሳዳምጥ ቆይቼ ዝቅ ባለ ድምጽ‹‹ አመሰግናለሁ ›› አልኳት፡፡ ከፀጉሯ ጋር በጣቷ እየተጫወተች በዝምታ ተመለከተችኝ፡፡

‹‹ ከረዥም ጊዜ ፍቅረኛዬ ጋ አለያዬሽኝ ›› ደነገጠች፡፡ ‹‹ ምን; ›› እንደምንም ከአፏ የወጣ ቃል ነው፡፡
‹‹ ለረዥም ጊዜ እንደ ፍቅረኛዬ ስንከባከበው ከነበረው ሱስ ጋር ዛሬ አለያየሽኝ››

ከተቀመጠችበት ድንገት ተነስታ ተጠመጠመችብኝ፡፡ ሽቶዋ ልቤን አጠፋው፡፡ ከልቤ ጋር ፍርሃቴም አብሮ ጠፋ፡፡ ለካ የፍርሃት ቤቱ ልብ ነው!
እንደተቃቀፍን የመጣው ይምጣ ብዬ ከንፈሯን ፍለጋ ስኳትን ያ- ክልፍልፍ አስተናጋጅ ዘው ብሎ ገባ፡፡
‹‹ ጠራችሁኝ እንዴ? ›› እያለ፡፡

ተፈፀመ
•═••• @NK_entertaiment •••═•
,,,,, ,,,,,
••●◉Join us share◉●••

━━━━✦ ✿ ✦━━━━━