Get Mystery Box with random crypto!

​​​ ሮ ማ ን ክፍል ...ይሁንና አንዴ ሲጋራውን ሌላ | NK_Etertainment

​​​ ሮ ማ ን

ክፍል

...ይሁንና አንዴ ሲጋራውን ሌላ ጊዜ ደግሞ አይኔን እያፈራረቀች መመልከቷን አላቆመችም፡፡ ይህቺ ቆንጆ ሴት ከዚህ በፊት እንደምታውቀኝ እርግጠኛ ሆኛለሁ፡፡ በውበቴ ሳትነደፍ አልቀረችም፡፡ የአበሻ ልማድ ይዟት እንጂ የፍቅር ጥያቄ ልታቀርብልኝ ፈልጋለች፡፡
አይኖቿ ውስጥ ‹እወድሃለው› የሚሉ ፊደላትን እያስነበበችኝ ነው፡፡
በአፏ የምታወራው ግን የማይጨበጥ ነገር ነው፡፡
‹‹እነዚህ አስተናጋጆች አለባበሳቸው በጣም ያምራል፤ አለባበስ ደንበኞችን ለመሳብ ከሚያስፈልጉ ወሳኝ ነገሮች አንዱ ነው፡፡›› ትለኛለች፡፡ እኔ ጭንቅላቴን ከመነቅነቅ ውጪ መልስ አልሰጣትም፡፡ ትንሽ ቆይታ ደግሞ ሎተሪ አዟሪ በፊታችን ሲያልፍ አይታ
‹‹ሎተሪ አዟሪዎች እድለኛ ባይሆኑም ሊከፋቸው አይገባም፡፡ ምክንያቱስ በለኝ.....››

የምትፈልገውን ልልላት ምላሴን ሳዘጋጅ የኔን ‹ምክንያቱስ› ሳትጠብቅ
‹‹ምክንያቱስ ብትለኝ ሎተሪ አዟሪዎች እድል ባይኖራቸውም ይዘውት የሚዞሩት ግን አድልን እራሱን ነው፡፡ ስለዚህ ደስ ሊላቸው ይገባል›› አለችኝ፡፡ ሀሳቧ ቢገባኝም እኔ ግን ምንም አልተናገርኩም፡፡
በዚህ መሃል ‹‹የጋዜጠኛ ነገር የኔን ወሬ ብቻ እንድታዳምጥ አደረግኩህ አይደል?›› አለችኝ ያንኑ ልብ የሚሰውር ፈገግታዋን በፊቷ እየረጨች፡፡ ተገረምኩ፡፡ ከአንደበቴ ድንገተኛ ቃላት ወጡ፡፡
‹‹እንዴ ጋዜጠኛ ነሽ እንዴ?›› ስል ጠየቅኳት፡፡
‹‹ምነው አንሳለሁ ወይንስ....››
‹‹አይ እንደዛ ማለቴ ሳይሆን........››

ንግግሬን ገታ አድርጌ ፈገግ ለማለት ሞከርኩ፡፡ ለጥቂት ጊዜ በመካከላችኝ የፀጥታ ድባብ ተዘረጋ፡፡ በዝምታ ውስጥ ሆነን በአይን መጠናናት ያዝን፡፡ ከዚያም ድንገት ‹‹ነገ 12 ሰዓት አካባቢ ስራ ይኖርሃል፡፡ ማለቴ ‹ቢዚ› ነህ?›› ጠየቀችኝ፡፡ የፈጣሪ ያለህ! ድንጋጤ ነፍሴን ሊነጥቀኝ ደረሰ፡፡ የልብ ትርታዬ ከመጠን በላይ መታ፡፡
ማራቶን የሮጥኩ መሰለኝ፡፡ ‹እወድሃለሁ› የሚል ቃል ብትናገር ምን ልሆን ነው?
ድንጋጤዬን ለመቆጣጠር እየሞከርኩ

ይቀጥላል...

ክፍል 5ይቀጥላል


•═••• NK_Entertaiment •••═•
,,,,, ,,,,,
••●◉Join us share◉●••