Get Mystery Box with random crypto!

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሹን ከጅማ ዩንቨርሲቲ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት ስምምነት ተፈራረ | The Niles ናይል 🇪🇹

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሹን ከጅማ ዩንቨርሲቲ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ
~~~~

የትብብር ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማልና  የጅማ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ናቸው የፈረሙት ።

የስምምነቱ ዋና ዓለማ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በግንባታ ፕሮጀክት አመራርና አስተዳደር ያገኘውን የተግባር ውጤት  ወደ ምርምር እና የእውቀት ተቋማት ለማስተላለፍ እንደሆነ ነው በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገለጸው፡፡

በሥነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ   አቶ ረሻድ ከማል በ እንደገለጹት የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በግንባታ ፕሮጀክት አስተዳደርና አመራር  የላቀ ብቃት አሳይቷል ያሉ ሲሆን ይህንንም ውጤት  ወደ ትምህርት ተቋማት እንዲሸጋገር  እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
ጅማ ዩንቨርሲቲ በሕክምናው እና በጥናትና ምርምር ውጤታማ ተቋም መሆኑን ጠቅሰው ከእንዲህ ዓይነት አንጋፋ እና ጠንካራ ዩንቨርሲቲ ጋር አብሮ መስራት ለኮርፖሬሽኑ ትልቅ አቅም እንደሚሆንም አመለክተዋል፡፡

የጅማ ዩንቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ በበኩላቸው  በዘመናዊና በተለመደው(Conventional) የአሰራር ዘዴ ያገኘውን ውጤታማ የፕሮጀክት አስተዳደርና የማማከር ልምድ ለጅማ ዩነቨርሲቲ በቀጥታ ለማጋራትና በትብብር ለመስራት መወሰኑ  ዩንቨርሲቲውን እንደሚያግዝ  ተናግረዋል፡፡