Get Mystery Box with random crypto!

የዙል‐ሒጃ ቀናት ከሌሎቹ ቀናት የተለዩ የሆኑበት ምክንያት ﴿وَالفَجرِ۝وَلَيالٍ عَش | ዲን ምክክር ነው

የዙል‐ሒጃ ቀናት ከሌሎቹ ቀናት የተለዩ የሆኑበት ምክንያት

﴿وَالفَجرِ۝وَلَيالٍ عَشرٍ﴾ [الفجر: ١-٢]

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል:‐"በጎህ (ንጋት) እምላለሁ። በአስሮቹ ሌሊቶችም።" (አል‐ፈጅር : 1‐2)

አል ኢማም ኢብኑ ጀሪር እና ሌሎችም ከኢብኑ ዓባስ እንዲሁም ከኢብኑ አዝዙበይር ረዲየ አላሁ ዓንሁማ እንደዘገቡት በዚህ ምእራፍ አላህ ከማለባቸው ነገሮች መካከል አስሮቹ ሌሊቶች የዙል-ሒጃ የመጀመሪያ አስርቱ ቀናቶች ናቸው ብለዋል።

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በነዚህ ቀናቶች መማሉ የቀናቶቹን ታላቅነት እና በውስጣቸው ያለውን ትሩፋት የሚያመለክት ነው።

ኢብኑ‐ሐጀር አል‐ዓስቀላኒ አላህ ይዘንላቸው በእሳቸው እይታ እነዚህ ቀናት ከቀሪው የአመቱ ክፍል የተለየ ሊሆኑ የቻሉበትን ምክንያት ሲገልፁ እንዲህ ብለዋል:— "እነዚህ አስር የዙል‐ሒጃ ቀናት ከሌሎቹ ቀናት የተለዩ የሆኑበት ምክንያት እንደ ሰላት፣ ጾም፣ ሰደቃ እና ሐጅ ያሉ የአምልኮ አይነቶች በአንድ ላይ የተሰባሰቡበት ወቅት በመሆኑ ነው። እነዚህ ሁሉ የአምልኮ አይነቶች በሌላ ጊዜ በአንድ ወቅት ሊፈፀሙ የሚችሉበት ሁኔታ የለም።"
(ፈትሁል‐ባሪን ይመልከቱ)

ለመልካም ስራ አላህ ይወፍቀን!

ጣሀ አህመድ

t.me/nesihaa