Get Mystery Box with random crypto!

Nejashi Printing Press

የቴሌግራም ቻናል አርማ nejashipp — Nejashi Printing Press N
የቴሌግራም ቻናል አርማ nejashipp — Nejashi Printing Press
የሰርጥ አድራሻ: @nejashipp
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.50K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የነጃሺ ማተሚያ ቤት ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው። የተለያዩ ጠቃሚ መልዕክቶችን፣ አዳዲስ የህትመት ውጤቶቻችንና አገልግሎቶቻችንን ተከታተሉን፣ ለሌላውም ሼር አድርጉ።

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 19:41:09 አል-ከሪሙ
አላህ (ሱ.ወ) ከውሃና ከአፈር በመፍጠር እኛን የሰው ልጆችን ክብር ሰጥቶናል፡፡ ውሃና አፈር በፍጥረተ-ዓለሙ ውስጥ የሚገኙ እጅግ ንፁህ የሆኑ ነገሮች ናቸው፡፡ ይህም ፅዱና ንፁህ ፍጡር መሆናችንን ያመለክታል፡፡ ስለሆነም በሀጢአትና በመናፍቅነት ራሳችንን አንነጅስ፣ ራሳችንን አናዋርድ፡፡ እኛ የጠራን ፍጡር ነን፡፡ የቁርአን እናት ፈቲሓ እንደሆነችው ሁሉ እኛም የፍጥረተ-ዓለሙ ቁንጮ ነን፡፡ ….
እኛ በምድር ላይ የአላህ ምትኮች ነንና ከርካሽ ነገሮችና ከርካሽ ስሜቶች ከፍ ማለት ይኖርብናል፡፡ ያከበረንን አላህ ማክበር ይኖርብናል፡፡ ራሳችንን የማክበር ሰሜት ውስጣችንን የፈጠረውን አምላክ ልናከብር ይገባል፡፡
በስህተት ላይ በምንወድቅበት ጊዜ ራሳችንን እንንቃለን፡፡ ትላልቅ ወንጀሎች ትላልቅ የተባሉበት ምክንያት እነርሱ እኛን በማዋረዱ ረገድ ትልቅ ስለሆኑ ነው ይባላል፡፡
እኛ የቸሩ፣ የተከበረው ጌታ ባሮች ነንና ራሳችንን አናዋርድ፡፡ በሀጢአት፣ በንፍቅና በውሸት ራሳችንን አናዋርድ፡፡ አንድም ሰው ሀጢኣታችንን ባያውቅ እንኳ ራሳችን በራሳችን ላይ የምንመሰክረው ይብቃ፡፡ ራሳችን ራሳችንን የምንታዘበው ይብቃን፡፡ በሌሎች እይታ ውስጥ ገብተን ከመዋረድ እንጠንቀቅ፡፡ ሁሌ እየተሸማቀቁ ከመኖርና መጠቋቆሚያ ከመሆን እንራቅ፡፡ ሰላም አይኖረንምና፡፡ ኃጢኣተኛ እንደሌባ ነው፤ጩኸት ሁሉ ወደርሱ ይመስለዋል፡፡

"ቢስሚከ ነሕያ" ከተሠኘው መጽሐፍ የተወሰደ
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኙታል፡፡

ዶ/ር ዐምር ኻሊድ እንዳዘጋጀው
ሙሐመድ ሰዒድ ABX እንደተረጎመው


https://t.me/NejashiPP
2.3K views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 16:27:47 አንዲት በዐይኗ የማታይ ድመት ወደ ቤትህ የተጠጋች እንደሆነ እሷን መቀለብ ግዴታ አለብህ ይላሉ አንዳንድ የሙስሊም ሊቃውንት ።

ኢስላም ለማንኛዉም ነፍስ ላለው ፍጡር ሁሉ እዘኑ ብሏል።

https://t.me/NejashiPP
2.5K views13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 14:37:27 https://forms.gle/fNKKyHfgTiLdDt778
615 views11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 18:58:45 አደብ የማጣት ጉዳት
‹‹ለአንድ ግለሰብ አደቡ የደስታውና የስኬቱ መሠረት ሲሆን፤ አደበ ቢስነቱ ደግሞ የደስታ-ቢስነቱና የስቃዩ ምንጭ ነው፡፡ የዚህችንም ሆነ የሚቀጥለውን ዓለም መልካም ነገሮች በማምጣት በኩል ከአደብ ጋር የሚስተካከል ነገር እንደሌለ ሁሉ፣ በማሳጣት በኩልም እንዲሁ አደበ-ቢስነትን የሚያህል የለም፡፡ የአደብን ምንነት እስቲ አስተውል! ዋሻ ውስጥ እንዳሉ ቋጥኙ ተንከባሎ በተዘጋባቸው ጊዜ፣ ያ ሰው ከወላጆቹ ፊት ያሳያት አደብ ባለቤቱን እንዴት ነፃ እንዳወጣቸው! በሌላ በኩል ደግሞ ሰላት ይበልጥብኛል ብሎ እናቱን ያሳዘነውን ሰው ሰዎች የማምለኪያ ቦታውን እንዲያፈርሱበት፣ እንዲደበድቡትና በብልግና እንዲከሱት በማድረግ እንዴት ፈተና ላይ እንደጣላቸው ልብ በል!?››
 
ምንጭ - የአደብ አስፈላጊነት መጽሐፍ
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ነጃሺ መፃህፍት መደብር
 
https://t.me/NejashiPP


https://bit.ly/3r4948i
2.9K views15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 21:22:16 ታላቁ ሰሓባ ዐብዱላህ ኢብኑ ሑዛፋ ረ.ዐ. ከእስልምና በፊት ምንም ጥረትም ሆነ አስተዋጽኦ አልነበረውም፡፡ የአላህ ፈቃድ ሆነና እስልምናን ተቀበለ፡፡ ከሰለመ በኋላ በምርኮነት በሩም ንጉስ እጅ ወደቀ፡፡ ንጉሱም ሊገድለው አሰበ፡፡
‹ሃይማኖትህን የምትተው ከሆነ ይህን ያህል ሀብት እሰጥሃለሁ፡፡› አለው፡፡
ሑዘይፋም ‹በአላህ እምላለሁ ሃይማኖቴን እንድተው ብለህ ሙሉ ሀብትህን ብትሰጠኝ የምተው አይደለሁም፡፡› አለው፡፡
ቀጥሎም ‹ሃይማኖትህን ከተውክ ከሥልጣኔ አካፍልሃለሁ፡፡› በማለት ሊያግባባው ሞከረ፡፡
ሑዘይፋም ‹በአላህ እምላለሁ የዚህ ዓለም ስልጣን ለኔ ምንም አይደለም፡፡› አለው፡፡
‹እንግዲያውስ እገድልሃለሁ፡፡› አለው፡፡
ሑዘይፋም ‹የሻህን መስራት ትችላለህ፡፡› አለው፡፡
ንጉሱ ጋሻጃግሬዎቹን ‹በቀስት ወጋጉትና አሰቃዩት፡፡ አትግደሉት፡፡› በማለት አዘዛቸው፡፡
ከፍተኛ ስቃይ እስኪሰማው ድረስ እጆቹን በቀስት ወጋጉት፡፡
‹ሃይማኖትህን ተው፡፡› በማለትም ጠየቁት፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አላቸው፡፡
‹በቀስቱ እግሩን ወጋጉት› አላቸው፡፡
‹ሃይማኖትህን ተው፡፡› አሉት፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አላቸው፡፡
ንጉሱ በመቀጠልም ‹ሁለት ባልደረቦቹን አምጡና በበርሜል ዘይት በማፍላት እዚያ ውስጥ ክተቷቸው፡፡› አለ፡፡ ከሱ ጋር የነበሩትን ሁለት ሙስሊሞች አመጡና ዐይኑ እያየ በፈላ ዘይት ውስጥ ከተቷቸው፡፡ አሁንም ጠየቁት፡፡
‹ሃይማኖትህን ተው፡፡ አለበለዚያ …› አሉት፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አላቸው፡፡
‹በሉ ውሰዱና ዘይቱ ውስጥ ክተቱት፡፡› አላቸው፡፡
ሊከቱት ወደ በርሜሉ ሲያስጠጉት ታላቁ ሑዘይፋ ረ.ዐ. አለቀሰ፡፡
ሰዎቹ ይህንኑ ለንጉሱ ነገሩት፡፡ ንጉሱም ‹መልሱት ወዲህ› አላቸው፡፡ መልሰው አመጡት፡፡
ንጉሱም ‹ማልቀስህ ተነግሮኛል፡፡› አለው፡፡ ሑዘይፋም ‹አዎን› አለው ለንጉሱ፡፡
‹እንግዲያውስ ሃይማኖትህን ተው፡፡› አለው፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አለ፡፡
‹እንግዲያውስ ለምን አለቀስክ?› አለው፡፡
‹በአላህ መንገድ የምሰጠው ነፍስ አንዲት ብቻ መሆኗ ነው ያስለቀሰኝ፡፡ በሰውነቴ ላይ ባለው ፀጉር ልክ ነፍስ ቢኖረኝና በአላህ መንገድ አንድ በአንድ ብሰጥ እመኝ ነበር፡፡› አለው፡፡

ለተጨማሪ መሳጭ ታሪኮች
ቢስሚከ ነሕያ መጽሐፍን ያንብቡ።
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኙታል።

https://t.me/NejashiPP
3.4K views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 11:36:14 በቆንጆ ተተርጉመው የቀረቡ የተለያዩ የሐዲሥ መፃሕፍትን ከነማብራሪያቸው በመደብራችን ያገኛሉ
1- ኩኑዝ
2- ተጅሪድ
3- ሪያዱሷሊሒን
4- መቶ ሐዲሥ አል-ቁድስ
5- ሪያዱሷሊሓት
6- ፈዷኢል አል- አዕማል
7- 450 ሶሒሕ ሐዲሦች

https://t.me/NejashiPP

https://bit.ly/3r4948i
936 views08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 11:32:15
833 views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 10:09:37 "አላህ ሆይ ወደ መልካም ሥነምግባራት ምራኝ። ወደ መልካም ነገር የሚመራ ካንተ ዉጭ ማንም የለምና።"
ይሉ ነበር የአላህ መልዕክተኛ ሶ.ዐ.ወ.

https://t.me/NejashiPP

https://bit.ly/3r4948i
3.2K views07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 13:26:05
ስለ ኢስላም ብዙ ባወቅክ ቁጥር
ኢስላምን ይበልጥ ትወደዋለህ።

ጁምዓ ሙባረክ!

ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ
Nejashi BookStore
1.2K viewsedited  10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 17:17:07 ነጃሺ ማተሚያ ቤት የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ምክኒያት በማድረግ ድርጅቱ ያሳተማቸው መጽሐፍት ህብረተሰቡ ላይ ያመጡትን የአስተሳሰብ፣ የባህሪና የዕውቀት ለውጥ ለመገምገም ዳሰሳ ማድረግ በማስፈለጉ ጥቂት ደቂቃዎች ወስደው ፎርሙን በመሙላት እንዲተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

>>>ይህን ይጫኑ<<

Nejashi Printing Press
1.1K viewsedited  14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ