Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል ሁለት ተከታታይ ትምሕርት የወሊድ መቆጣጠሪያ እና የውርጃ አብዮት። | 🌼ናታኒም ቲዩብ🌼

ክፍል ሁለት ተከታታይ ትምሕርት


የወሊድ መቆጣጠሪያ እና የውርጃ አብዮት።


ማሳሰቢያ ይህን ክፍል ምታነቡ ክፍል አንድን ያነበባቹ መሆን አለባቸው ያላነበባቹሁም እርሱን አንብባቹሁ ቅድሚያ ቀጥሎ ይህን ማንበብ ትችላላቹሁ ። የክፍል አንድ ሐሳብ ነውና ወደዚህ ክፍል ሚመራቹሁ።

መልካም ንባብ።


             
በጥንቷ ቤተክርስቲያን ብዙ ዓይነት     የወሊድ መቆጣጠሪያ ነበሩ።


ከብሉይ ኪዳን አንስቶ ብዙ ዓይነት የወሊድ መቆጣሪያዎች ነበሩ ።
ለምሳሌ ግብረ አውናን ፣ የወንዱን ዘር የሚገድሉ ንጥረ ፣ ነገሮችን በሴትዋ መራቢያ አካል ላይ የሚቀመጡ ነገሮች
፣ የዕፅዋት ቅመሞች ተጠቃሽ ናቸው። ኮንዶም ሳይቀር ከክርስቶስ ልደት ከ3ሺሕ ዓመታት በፈት ጥቅም ላይ ይውል እንደ ነበር መረጃዎች ያመለክታሉ።

ለምሳሌ፦ ሚኖስ ዘቄስጤስ የተባለ ንጉስ የፍየል ፍኛዎችን በመራቢያ አካሉ ላይ አድሮጎ ሩካቤ ይፈጽም እንደ ነበር ተጠቅሷል ።




በሰነድ ደረጃ ስለ ወሊድ መቆጣጠሪያ መረጃ የምናገኘው ለመጀመሪያ ጊዜ በግብፅ ነው ። ይኸውም ከክርስቶስ ልደት በፈት ከ1900-1100 ላይ በነበሩበት አምስት የተለያዩ ፓፒረሶች ውስጥ ነው ። በእነዚህ መረጃዎች ላይ እንደ ተቀመጠው ፥ ማርና ሶዲዮም ካርቦኔት በሴትዋ መራቢያ አካል ላይ በመቀባት ይህ ይደረግ ነበር። ቴምር ከማር ጋር ተደባልቆ በሴትዋ ማኅፀን ውስጥ በማስቀመጥ ከኹለት እስከ ሶስት ዓመታት ልጅ እንዳይወለድ ማድረግ ይቻል ነበር። በሌላው የፓፒረስ ቅጂዎች ኹሉ የወንዱ ዘር ከሴትዋ እንቁላል ጋር እንዳይገናኝ መከላከል የመግደል ዓላማ የነበራቸው ናቸው።



እስራኤላውያንም ይህን ከግብፃውያን ተምረው ይተገብሩት ነበር።
ለምሳሌ ፦ ሩካቤ አድርጎ የወንዱን ዘር ማፍሰስ አንዱ መንገድ ነበር በመጽሐፍ ቅዱስ የተመዘገበው ነው - ይህም ግብረ አውናን ብለን የምናውቀው ነው (ዘፍ . 38፥8-10)። በተለይም ጋለሞታዎች ይህን መንገድ ይጠቀሙት ነበር ። ከአሕዛብነት ወደ ይሁዲ እምነት የተቀየረ ሰውም መቀየሩን እርግጠኛ እስከሚኾን ድረስ በዚህ መንገድ ልጅ እንዳይወልድ ይደርግ ነበር ። ነጻ ኾና እስከምትለቀቅ ድረስም አንዲት ባሪያ እንዳትፀንስ በዚህ መንገድ ይከላከሉት ነበር ። ዕቁባቶችም ይህን ይጠቀሙት ነበር። በግብረ አውናን ብቻ ሳይኾን የሚያመክኑ ንጥረ ነገሮችን ይጠቀሙ እንደ ነበር መረጃዎች ያመለክታሉ።




በግሪኮ ሮማን ያለውን ጊዜ ስንመለከትም በጊዜው የሳይንሱ ዓለም ሰዎች የትኞቹ ለውርጃ ፥ የትኞቹ ደግሞ ለወሊድ መቆጣጠሪያ እንደሚያገለግሉ በአግባቡ በብራናዎቻቸው አስፍረውታል።

ለምሳሌ አንዲት ሴት የወር አበባ ከተመለከተች በኋላ ለሚቀጥሉት አራት ቀናት የምትወስዳቸው መድኃኒቶች የነበሩ ሲኾን ፥ እነዚህም ለጊዜያዊ ምክነት ይጠቀሙባቸው የነበሩ ናቸው ።

ለምሳሌ በጊዜው ከነበሩት የሕክምና ባለሞያዎች አንዱ ዲዮስኮሪደስ እንደሚለው ይህ ለአምስት ቀናት ብቻ እንደ ሚያገለግል ይናገር ነበር። ሶርኖስ የሚባለው ባለ መድኃኒት ስለ ማኅፀን ሕክምና በጻፈው መጽሐፍ ላይ በስፍት ዘግቦታል። (soranos;Gynacology 1.19.60-63) እነ አሪስጣጥሊስም የወይራ ዘይት በሴትዋ የመራቢያ አካል ጫፍ ላይ አስቀድሞ ማድረግ የወንዱ ዘር በቀላሉ ተንሸራትቶ እንዲወድቅ እንደሚረዳ ጽፏል። (Aristotle, History of Animals 7:3 , As quoted in Noon p.15) ክርስትና በተመሰረተበት በአንደኛው መቶ ዓመት ላይ ብቻ ከአንድ መቶ በላይ ፅንስን ሊጎዱ የሚችሉ ዕፅዋት ነበሩ። (Jon T.Noonan(1965); Contraception, p.12)



የሕክምናው አባት ተብሎ የሚታወቀው ሄሮድቶስም በስድስተኛው መቶ ዓመት ላይ ስለ ነበረው የአቴንስ ገዢ ሲናገር ፥ መውለድ ስላልፈለገ ከኹለተኛ ሚስቱ ጋር ያልተለመደ ዓይነት ሩካቤ ይፈጽም እንደ ነበረ ገልፆአል። ያልተለመደው ሩካቤ እንግዲህ ግብረ አውናን ሊኾን ይችላል ፤ ሌላም ይኾናል - ግልፅ አላደረገውም ። ( As quoted in Noon,p. 16)



በኋላ ላይም በተለይ ነገስታቱ ቁጥራቸው እየተመናመነ ስለ መጣ የወሊድ መቆጣጠሪያ መጠቀም ይከለከል ጀመር። አልፎ ተርፎም ለሚወልዱት ሽልማት ይሰጥ ጀመር። እንደ ቅጣትም ልጅ የማይወልዱ ሰዎች መኳንንትና አስተዳዳሪ ኾነው ከመሾም ይከለክሉ ነበር። በዐዋጅም በሮም ሕግ የጋብቻ ዋና ዓላማ መውለድ ተብሏል ። ባለ ስልጣን በተለይ በመጀመሪያው መቶ ዓመት አንዱ ግዴታቸው መውለድ ነበር ። ከ166-180 ዓ.እ. በነበረው ከባድ ረሃብ ምክንያት ብዙዎች ስለ ሞቱም ዘመናት ሲሰበክ የነበረው የልጅ ጠል ውጤት ነበር። የመጀመሪያዎቹ ሶስት መቶ ዓመታት እንዲህ አስቸጋሪ የኾኑበት አንዱ ምክንያት ይህ ነበር ።

በዚህ ላይ ከዚህ በፈት ያነሳናቸው የግኖስቲኮች ትምህርት ይህ በትምሕርት እንዳስፍፍ የራሱ የኾነ የአንበሳ ድርሻ ነበረው ። ማኒያውያን ሴትዋ የማታረግዝበትን ጊዜ እየጠበቁ ሩካቤ መፈጸም እንደ ዋነኛ የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገድ ይጠቀሙበት ነበር ። ጋለሞታ ሴት ተመራጭ የኘበረችውም ለዚህ ነው ፤ አትወልድምና ( As quoted in Noonan P. 123)


(ትንሻ ቤተከርስቲያን ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ ፣ ቤተሰብ እና የሕፃናት አስተዳደግ "ገብረ እግዚአብሔር ኪደ")



ይቀጥላል .....


ቀጣይ ክፍል ሶስት ይጠብቁኝ

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ


SHARE SHARE


█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵  ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░ ► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵  ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌