Get Mystery Box with random crypto!

poeM lovers 💓

የቴሌግራም ቻናል አርማ mypoemlovers — poeM lovers 💓 P
የቴሌግራም ቻናል አርማ mypoemlovers — poeM lovers 💓
የሰርጥ አድራሻ: @mypoemlovers
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 421
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የግጥም ስራዎቼን ለአንባቢያን ወዳጆቼ ለናንተ የማደርስበት ነው ወዳጅ ዘመዳችሁን አድ በማድረግ ስራዎቼም ላይ ያላችሁን አስተያየት በማድረስ ከጎኔ እንደምትቆሙ አምናለው። አመሰግናለው ሀሳብ ወይም አስተያየታችዉን 👉 @modelSeNe ላይ ላኩልኝ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-05 11:04:56 ይድረስ ለ #ብራናየ......


በዝምታ ውስጥ - መናገር እንዳለ
ከእኔና አንተ ቀድሞ - ማነው ያስተዋለ ?
ዝም ብየ ተናገርኩ ....የልቤን ዘርዝሬ
መች ችየ - ልደብቅ እኔማ ደፍሬ
በዝምታየ አይደል - እኔማ ማወራው
የቀረብህ የለም - ካንት ምደብቀው
አፍ ለ አፍ ውርርድ - ወሬ ባልሰንቅም
ላንተ የምነግረው - ውሸት ሁኖ አያውቅም !
ለዛ ነው ቀን በቀን - የልቤን ምነግርህ
ስለምትሰማኝም - ምስጋና ይድረስህ
ደሞ ተናድጄ ብዙ ነገር ብየ ደልዤ ቀድጄ
እኩርፌ ትቼህም ....
ካስቀመጥኩበት ነው - የማገኝህ ነገም...,,
ብቻ ግን ......አመሰግናለው......!!!
እኔን እንዳንተ - ማነው የሚችለው......?
የስሜቴን ናዳ - ችለሀል ቀን በ ቀን
በዝምታየ እይደለ - ካንት ምነጋገር.......
ብቻ የኔ ወዳጅ - በእኔ እጅ ካልሆነ አይጠቁርብኝ ገጽህ ...
ንዴቴን ማብረጃ - መሸሸጊያ ነህ....
አንተ ወረቀቴ - የጥንት ጓደኛየ
ከዘመኑ ሰውስ - አንተ ነህ ምርጫየ !
ስነ
104 views08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 18:55:45 አለም እንቆቅልሽ - አፈታቱዋ ግራ
እንኳን ለኔ ቀርቶ - ለራሱዋም ደንባራ
ላሰበላት ሳይሆን - ሚሰርቃትን ሹዋሚ
እንዲያ አይደለም ሀቁ - ትሰሚ እንደው ስሚ
ሚያጎርስሽን ነካሽ - ሚያከብርሽን ናቂ
መሆንሽ ታወቀ - ጠመሻል ልትወድቂ
ዋ !!!
ተይ በልኩ አድርጊው - ያንቺ ተለይቱዋል
በክፍት ተጣመሽ - መቃናት ታክቶሻል
ዋ እልሻለው ዛሬም - ከበፊት በባሰ
ምግባርሽ ቀን ከቀን - ሲታይ እያነሰ
የሰራሽው ሁሉ - ለሚዛን ሳይበቃ
ያንቺ ዘመን ጊዜ - በዚሁ አበቃ
ስነ
380 views15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:03:25
210 views14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 17:02:43 እራሱዋ ትሰራ - እራሱዋ ታፈርሰው
ይቻላታል ወፏ - ውሳኔው በአፏ ነው
አንድ ሰበዝን ስባ - ቋጥራ ችላ እንደሆን
ምኑ ነው ሚገዳት - ፈፅማ ቤት መሆን
ደንባራ ጠያቂ - ጥያቄ የከዳው
እንዴት ችላ ይላል - ወኔዋን ሳያውቀው
ከጅምር የናቃት - አንገት ደፍታ ቢያያት
መች ተረዳው እና - ቤት እንደሰራላት
ወትሮም የተናቀ - አይችልም ተብሎ
መሬት የተደፋ - ይገኛል አብቅሎ ..,,,,,
ደንባራ ጠያቂ - ጥያቄ የከዳው
እንዴት ችላ ይላል - ወኔዋን ሳያውቀው
እሁን ገባን መሰል - ከረፈደም ቢሆን
ዝቅ ብሎ መታየት - ከፍታ እንደሚሆን
ታዲያ ይህችም ወፋ - እሄን ስለምታውቅ .....
ትግስትን ተላብሳ - ከናቁዋትም ልቃ
ዘውትር ትታያለች - ከምድር ከፍ ብላ
.......በናቋት ልክ - ከፋታዋ ልቋ.....
አይደለም ውሎዋ - ቤቱዋም በላይ በላይ
የተናቀ ነው - ከፍታንም የሚያይ.....,
ስነ
577 views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 16:05:20 እግሩ ሳተ ዛሬም - ኋላ ኋላ እያየ
የፊቱን ዘንግቶ - ነገውን ተለየ
እረ ጉድ ዘንድሮ - መደናበር በዛ
ትውልድ መከነብን - ሆነብን ፈዛዛ
እሺ አሁን እንዴት ነው - በየትኛው ስሌት
ኋላ ኋላ እያዩ - ፊት ቀድሞ መገኘት
ስነ
816 views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 10:39:27 አካል እንዴው ትቢያ - እይጠራ ዘላለም እፈር የሚገባ
የነፍስ ስራ ይሁን - ሆድን የሚረታ ልብን የሚያባባ
ተው ዝም ብለህ ስማ - አታቁዋርጠኝ ላውራ
አሁን ምን ያደርጋል-ለሚሸት ስጋችን እሄ ሁሉ ጉራ
ኤድያ........
ልፋ ያለው ትውልድ - ግንድ ይዞ ይዞራል
መሰረት ስር የለሽ - ለግንድ ይጨነቃል
ወትሮም ስር አልባ ነው - ዘፈቀደ ኑሮው
በየሄደበት ሚያብብ - የትም ሁኖ ውሎው.....
ወይ ሀረግ እይባል - ውበትነት የለው
ዝም ብሎ መጥለፍለፍ - ትርፉ ለመቀስ ነው
በአጭር ለመቀጨት
ህይወትም እንዲ ናት - ስርህ ሚወስናት
ኮትኩተህ አሳድግ - አጥብቀህ ልፋባት
በግንድህ አትኩራ - ስርህን አስቀድም
እሱ ነው ዋንኛው - ህይወት ሚያለመልም
ስነ
1.1K views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 11:19:21 ሚዛንን ማያሻ - በአይተሽ የሚሰፈር
ትውልድ በዝቶ ሳለ- ውሸት የሚመክር
ምነው ሚዛን ላቀ - ለይስሙላ በዝቶ
ደጋግመው መደቡት - የሚመዝን ጠፍቶ
ስነ
1.3K views08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-03 17:04:08 ሞኝ አትባል ብልህ ግራ ታጋባለች !
መድማት እየፈራች ሾህን ትተክላለች !
እንዳይቀጥፉዋት ይሆን ??
ወይስ ሌላ ሀሳብ እሄን እንቆቅልሽ ሚፈታላት የታል ???
ስነ
1.8K views14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-03 09:38:45
2.0K views06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-12 09:43:40 "መቅደላ አፋፉ ላይ - ጩኸት በረከተ
የሴቱን አናውቅም - ወንድ አንድ ሰው ሞተ"
........
ተብሎ ተገጠመ - ወንድ የሞተ ለታ
ተብሎ ተሸለለ - ጀግና የሞተ ለታ
ለአንዱ የጀግና ሞት - ጥንቶቹስ ተቆጩ
ዛሬ ዝምታ ነው - ባጭር ለተቀጩ
አይ ልዩነታችን - የአሜኬላ ትውልድ
ትርፉ ያልተለየ - የሞላው እንክርዳድ
የዘራነው ሁሉ - ውጤቱ ደም ሁኖ
ደግነትን ሳናውቅ - ጭካኔያችን ገኖ
አወይ እሄስ ዘመን - ምንኛ ይመራል !
እንኳንስ ለኑዋሪ - ለሙዓች መቺ ይመቻል
እንዴት አልከኝ ?
እንዴት ማለት ጥሩ.......
ደም እየሰረገ - በተኛበት አፈር
ግፍ እያሰከረው - አለም ሲደናበር
የሙት አጽም እንኳን - የሰው ደም ከበደው
ሰርጎ እየገባበት - ማረፍም ቸገረው
አንተስ ችለህ ተኛህ
ስነ
2.3K views06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ