Get Mystery Box with random crypto!

የዙልሒጃ ወር መግቢያ ጨረቃ ታይታለች! የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ሐምሌ 2 ዕለተ ቅዳሜ እንደሚ | Muslime students 🤝

የዙልሒጃ ወር መግቢያ ጨረቃ ታይታለች!
የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ሐምሌ 2 ዕለተ ቅዳሜ እንደሚከበር ተገለፀ!!
የዙልሒጃ ወር ዛሬ ሐሙስ አንድ ብሎ ይጀምራል
አቡ ዳውድ ኡስማን
በሳዑዲ አረቢያ አዲስ የዙልሂጃ ወር መግቢያ ጨረቃ
በመታየቷ የዙልሂጃ ወር ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 23/2014 / June 30/2022 አንድ ብሎ
እንደሚጀመር ታውቋል::
የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልም ቅዳሜ ሐምሌ 2-2014/ July 09/2022 እለተ ቅዳሜ
እንደሚውል ታውቋል፡፡
ከዛሬ ሐሙስ ሰኔ 23 ጀምሮ ያሉትን 10 ቀናት በኢባዳ ልናሳልፋቸው ይገባል፡፡
የዙልሂጃን ዘጠኙንም ቀናት ለመፆም ፍላጎት ያለው ከዛ ሐሙስ June 30 /2022 ጀምሮ
መፆም ይችላል፡፡
ታላቅ ምንዳ የሚያስገኘውን የዙልሒጃ 9 (የአረፋን ቀንን) ለመፆም የሚፈልግም ሐምሌ
1እለት ጁምዓ መፆም ይችላል::
ከዛሬ ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ አስር ቀናቶች በኢባዳ እናሳልፋቸው!
አላህ ይርዳን!