2022-08-23 18:17:37
~ቁርዐን በዳይመንድ ሲገለፅ~
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬
✎﹏በጣም ፣ በጣም አስተማሪ ታሪክ ➥#የቁርዐንን ምንነት በዚህ ታሪክ ካልተረዳነው በጣም ከባድ ነው! ! ! !ልባችን ደርቋል ማለት ነው። :ከዕለታት አንድ ቀን ተማሪው ለኡስታዙ ድንቅ ጥያቄ ያቀርብለታል ፤ ጥያቄውም እንዲህ ነበር➘
▮
ኡስታዝ ሆይ! ቁርዐን ልክ እንደ #ዳይመንድ ነው። ዋጋው በጣም ከፍተኛ ነው እያልክ ትናገራለህ። ነገር ግን እንደ ዳይመንድነቱ ማንም ሲፈልገው አላየሁም?! እንደውም ሰዎች ጋር ሲነበብ እንደ ቆሻሻ አርገው ነው የሚያዩት! ክብር እንኳ አይሰጡጥትም ፣ ይሄ ነገር ሃላል ነው ሀራም ነውም ስትላቸውም ችላ ይሉታል. . . .።▮
:ኡስታዙ በጣም ብልህ ሰው ስለነበር አንድ ቆሻሻ ድንጋይ ይሰጠውና. . . .➘
▮
ይሄን ድንጋይ ወደ ጫማ ቤት ይዘህ ትሄድና ድንጋዩ ስንት ብር እንደሚያወጣ ትጠይቃለህ ነገር ግን አትሸጠውም!፣ በመቀጠልም ወደ ስጋ ቤት ይዘህ ሂደህ ድንጋዩ ስንት ብር እንደሚያወጣ ትጠይቃለህ መሸጥ ግን የለብህም ፣ ከዛም ወደ አናጢ ቤት ወስደህ ስንት ብር እንደሚያወጣ ትጠይቀዋለህ ለዚህም ግን መሸጥ የለብህም ፣ በመጨረሻም ወደ #ዳይመንድ ቤት ትወስደውና መሸጥ ፈልጌ ነበር ስንት ትገዙኛላችሁ በላቸው። መሸጥ ግን የለብህም...!። በመጨረሻም ድንጋዩን ይዘህ ወደኔ ትመለሳለህ▮ ይለዋል።
:ልጁም በተባለው መሰረት ወደ ጫማ ቤት ይሄድና ለጫማ ሰፊው "ይህሄን ድንጋይ ትገዛኛለህ? ብሎ ይጠይቀዋል። ጫማ ሰፊውም በመገረም "እንዴ! ምን ነክቶህ ነው? በቀን ከ100 ጊዜ በላይ ስመላለስ የማየውን ድንጋይ የምገዛህ?.. . .. ልጁም ግዛኝ እያለ ይጨቀጭቀዋል. . . .። በስተመጨረሻም ጫማ ሰፊው በቃ በ5$(dollar) እገዘሃለው ይለዋል። ልጁም መሸጥ የለብህም ስለተባለ ዋጋውን ብቻ አረጋግጦ ሳይሸጠው ወደ ስጋ ቤት ይሄዳል።
:ስጋ ቤትም እንደ ደረሰ ተመሳሳይ ጥያቄ ለባለ ስጋው ቤቱ ያቀርብለታል። የባለ ስጋው ቤቱ በጣም በማሾፍ "ድንጋዩን እዚህ ጥለሀው ብትሄድ ራሱ ወደዛ እወረውረዋለሁ ይለዋል". . . .ልጁም ወደ አናጢ ቤት መንገዱን ይቀጥላል. . .. ።
:አናጢውም ቤት እንደደረሰ ልጁ ለአናጢው ተመሳሳይ ጣያቄ ያቀርብለታል። አናጢውም በጣም በመደነቅ እንዲህ ይለዋል" ይሄን ድንጋይ እኔ እንድወስደው ከፈለክ 5$ ትከፍለኛለህ" ይለዋል።
.
.▷ልጁ በጣም ግራ ገባው ፣ ምን እየተካሄደ ነው ያለው? ኡስታዜ ምንድን ነው የነገረኝ ነገር? በማለት ጥልቅ ሀሳብ ውስጥ ይገባል. . . .¿ የዚህን ጊዜ ምሳ ሰዐት ይደርሳል ሀሉም ሰው ምሳውን የሚበላበት ሱቆች በጠቅላላ የሚዘጉበት ሰዐት ነበር። ሆኖም ግን እሱ ወደ ዳይመንድ ቤቱ ጉዞውን ቀጠለ. . . .።
:በመጨረሻም ዳይመንድ ቤት ውስጥ ይገባል። ለሰራተኛውም "ይሄን ድንጋይ ስንት ብር ትገዛኛለህ?" ይለዋል። ሰራተኛውም አይ ይሄ ዝም ብሎ መሬት ላይ ያለ ድንጋይ ነው ሲታይም በጣም ቆሻሻ ነው በጭቃም ተሞልቷል እንዴት ነው የምገዛህ ይለዋል። ነገር ግን ሰራተኛው ድንጋዩን አቱኩሮ ሲመለከተው ትንሽ ማንፀባረቅ ይጀምራል። ከዛም አለቃውን ይጠራውና እስኪ ይሄን ድንጋይ እንመርምረው ብሎት በአጉሊ መነፀር ሲመለከቱት ከቅድሙ በበለጠ ሁኔታ ማንፀባረቅ ይጀመራል. . . . .። አለቃውም በጣም በመገረም "ድንጋዩን ከየት ነው ያገኘሀው???" ብሎ ይጠይቀዋል። አይ እኔ መሸጥ ፈልጌ ነው የመጣሁት ባለቤቱ ማን እንደሆነ ልነግረህ አልችለም ይለዋል ። እርግጠኛ ነህ ድንጋዩን ትሸጠዋለህ?? አዎ ለመሸጥ አይደል እንዴ የመጣሁት። አለቃውም አስቀጥሎ፦ ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ድንጋይ በፍፁም አይተን አናውቅም!!! ይገርመሃል?ሰዓቱ የምሳ ሰዕት ነበር ነገር ግን ችግር የለውም በሩን ዘግተነው ማንም እንዳይመጣ አድርገን ትንሽ በድንጋዩ ላይ ምርምር እናደርጋለን"።
➥ድንጋዩን በጥልቅ ሲመረምሩት በጣም ያንፀባርቃል። ድንጋዩም #ዳይመንድ ሁኖ ተገኘ!!! ለልጁም "ለዚህማ 50,000$(ሀምሳሺ ዶላር) እንገዘሃለን" ይሉታል። ልጁም በመደንገጥ "እርገጠኛ ናችሁ ??? በጣም ብዙ ብር እኮ ነው!!!"
"አዎ መሸጥ ራሱ ባፈልግ በትልቅ ሳጥን ውስጥ ከተነው ከሁለት ጋርዶች(ተከላካዮች) ጋር አድርገንህ ነው ነው ወደቤት የምንሸኝህ። ምክንያቱም የያዝከው እቃ ቀላል አይደለም በጣም ውድ ነገር ነው!!!። ልጁም ማመን አልቻለም " ምን እያልከኝ ነው???" ብሎ በድጋማ ይጠይቀዋል። አለቃውም " ስማኝማ! እኔ የዚህ ቤት አለቃ ነኝ በጣም ብዙ ዐመት ሰርቻለሁ ነገር ግን እንዲህ አይነት በጣም ውድ የሆነ ፣ የከበረ ድንጋይ አጋጥሞኝ አያውቅም!!!" ልጁም "እሺ አንዴ ተመልሼ እመጣለሁ"
. . . . . .. .
:. . . .ከዛም #ኡስታዙ በተቀመጠበት ከፊት ለፊቱ ልጁ ከሁለት ትላላቅ ሰዎች ጋር እና ከቀይ ሳጥን ጋር ሲመጣ ያየውና ለልጁ እንዲህ ይለዋል➘
▮
ቁርኣን እንደ ዳይመንድ መልክ ነው ስልህ ህዝቡ ቁርኣንን እየገመገመ አይደለም እያልከኝ ነው፣አየሃ!!! እውነተኛ ዳይመንድ ሰጥቼሃለሁ፣ የሚያውቀው ሰው ከሌለ በቀር ማንም ዋጋ አይሰጠውም(ማንም አያውቀውም)▮
:"اِنَمَا يَعۡرِفُ ذَالفَضۡلِ مِنَ النَّاسِ ذَوُوهُ"
:"እሱ በሰዎች መካከል የተሻለው ብቻ ነው የሚያውቀው"
┊ ┊ ┊ ┊
┊ ┊ ┊ ✿
┊ ┊ ❀
┊ ✿
❀
╠═════ •『 ﷽ 』• ═════╣
┣𝐆𝐫𝐨𝐮𝐩• @Muslim_group2
┣━━━━━━╗ ╔━━━━━━━⎙
┣𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥• @Muslimchannel2
╠═══════•❁❀❁•══════╣
#SHARE_The_خير
2.6K views ︎رمـــــص۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۪۬ـــــــــــــاݩے𝕧, 15:17