Get Mystery Box with random crypto!

ዑመር ተፅዕኖ ፈጣሪው ፊልም በአማርኛ * ውድና የተከበራችሁ የአል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ወዳ | አል ሙነወር ጀምዓ🎧

ዑመር ተፅዕኖ ፈጣሪው ፊልም በአማርኛ
*
ውድና የተከበራችሁ የአል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ወዳጅና ተከታታዮች ባለፉት ቀናት በአንጋፋውና እውቁ የዐረበኛ ፊልሞች ዳይሬክተር ሐቲም ዓሊ የተሰራውንና ከተለያዩ የዐረብ ሀገራት ብቁ የሆኑ ተዋናዮች ተጣምረው የተወኑበትን ዑመር የተሰኘ ፊልም በትርጉም ይዘንላችሁ እንደምንመጣ አሳውቀን ነበር።

እነሆ ይህን የቅርብ ጊዜና መላው ዓለም ላይ ተፅዕኖ የፈጠረ ጉደኛ ተከታታይ ፊልም በባለ ሁለንተናዊ ሙያና ክህሎቱ የጥበብ ሰው ሷሊሕ አስታጥቄ በላቀ ብቃት ወደ አማርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ፣ በተለያዩ ማዲሆችና ተዋናዮች ድምፅ አቻ ለአቻ ተተውኖ ፣ በአል ፋሩቅ አዲስ ስቱዲዮ ውስጥ በተዋጣለት የኤዲቲንግ ባለሙያው ዐብዱለጢፍ ዐሊ (አንበስ) ኤዲት ተደርጎ ፣ በከፍተኛ ጥራት በ30 ክፍል ወደናንተ ሊደርስ ቀናት እየጠበቀ ይገኛል።

መልቲሚዲያችንም አሁን ከሚሰራበት የመንዙማ ስራዎች ጎን ለጎን የቀደመውን የፊልም ትርጉም ስራ ዳግም መጀመሩንና ከዚህ በኋላም በርካታ ፊልሞችን ወደናንተ ለማድረስ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።

ይህ ከትርጉም ጀምሮ እስከ ትወና እንዲሁም እስከ ኤዲቲንግ ድረስ በርካታ ብቁ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ፊልም በቅርብ ቀን በዩቲውብ በቴሌግራም ቻናሎቻችን ይለቀቃሉ። ከእናንተ የሚጠበቀው ዩቲዉብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ፣ የቴሌግራም ቻናላችንን ደግሞ ጆይን አድርጎ መጠበቅ ብቻ ነው።

የዩቲውብ ገጻችን Youtube:

https://youtube.com/c/ALFARUKISLAMICTUBE

የቴሌግራም ገፃችን Telegram

https://t.me/ethioalfaruk

የፌስቡክ ገፃችን Facebook

https://www.facebook.com/alfarukmultimediaproduction/
-------------------

Share Share Share