Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር ማለት … ቢላል ረዲሏሁ አንሁ ነብዩ ﷺ ከሞቱ በኃላ አዛን ማድረግ ማቆማቸው ነው ፤ | ሙሀመድዬዬዬ🤩😘😍🤩

ፍቅር ማለት …

ቢላል ረዲሏሁ አንሁ ነብዩ ﷺ ከሞቱ በኃላ አዛን ማድረግ ማቆማቸው ነው ፤

ፍቅር ማለት … ቢላል ረዲሏሁ አንሁ ነብዩ ﷺ ከሞቱ በኃላ መዲና መኖር አለመቻላቸው ነው ፤

ፍቅር ማለት … ቢላል የነብዩን ﷺ መስጅድ ከዘየሩ ጊዚያት ተቆጠረው የአላህ መልክተኛ ﷺ በህልማቸው መጥተው አንተ ! ቢላል ምነው አስቻለህ ? ሲሏቸው እያለቀሱ ለዚያራ መዘጋጀታቸው ነው ፤

ፍቅር ማለት… ቢላል ረዲሏሁ አንሁ ወደ መዲና መጥተው ሀሰንና ሁሴን የሱብሂን አዛን እንዲያደርጉ አዘዋቸው የመዲና ህዝብ አዛናቸውን ሲሰሙ በእንባ መራጨታቸው ነው፤

ፍቅር ማለት … ቢላልን ዑመር አልፋሩቅ ረዲሏሁ አንሁ 'ሻም' ላይ አዛን እንዲያደርጉ አዘዋቸው በማልቀስ ብዛት ' አሽሀዱ አንነ ሙሀመድ ረሱሉላህ ' ማለት ተሰኗቸው ሁሉንም ማስለቀሳቸው ዑመርም ይበልጥ ማለቀሳቸው ነው ፤

ፍቅር ማለት … ቢላል ረዲሏሁ ዐንሁ ሊሞቱ እያሉ ' ነገ ወዳጄ ሙሀመድንና ባልደረቦቹን እገናኛለሁ ' ማለታቸው ነው

ምርጥ ህዝቦች አልፈዋል እኛንም የነርሱ ተከታይ ያድርገን اللهم صلي ال محمد


Share share
join
https://t.me/muhmedeye