Get Mystery Box with random crypto!

#ለቅሶ_ሄዶ_ደስታን_መማር የአንድ ወዳጄ አያት ሞተው ለቅሶ ልደርስ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጬ | Moha Mossen መሐመድ ሐሰን

#ለቅሶ_ሄዶ_ደስታን_መማር
የአንድ ወዳጄ አያት ሞተው ለቅሶ ልደርስ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጬ ሄድኩኝ። ይሄኔ ወዳጄ ከማመስገን ይልቅ ወቀሰኝ።
"ልጄ ስትወለድ፣ ለክርስትናዋ፣ ለልደቷም አልመጣህ። ምነው ለአያቴ ሞት ይህንን ሁሉ ኪሎ ሜትር አቋርጠህ መጣህ?" ብሎ ኩምሽ! ንቅት! ሸንቆጥ! አደረገኝ።

በሳቃችንና ደስታችን ጊዜ ከዝምታም አልፈው የሚያለቅሱ ሰዎች፣ በለቅሷችን ጊዜ ሊያጅቡን ይንጋጋሉ። ዝምታቸውን እንደ ውለታ፣ ለቅሷቸውን እንደ ቅኔ፣ ጩኸታቸውን እንደ ዜማ እንድንቆጥርላቸው የሚያስቡ አሉ። ወገኔ ለቅሶ ምንም አጃቢም ማጀቢያም አያስፈልገውም። እውቀትም ስራም አይፈልግም። ብርሀን ነው ከባድ። ደስታ ነው ውድና ለሰው ልጅ የሚገባው። በየቀኑ መጀመሪያ ራሳችንንና ዙሪያችንን እያስደሰትን፣ ለዙሪያችን ብርሀንና ደስታ እየሰራንና ዋጋ እየሰጠን እንሂድ። ከዛ ትልቁና ውዱን ደስታ እንደ ሀገር እናጣጥማለን።
መጀመሪያ ለራስሽ ስሪ! ለራስሽ ቃል ግቢ። የሌለሽንና የማታውቂውን መስጠት አይቻልም። ለሱ ደግሞ ወርቅ እንዳጠልቅልሽ አትጠብቂ።
እኔ በጭራሽ ጨለማንና ግፍን በማዋጣት ውስጥ ዝር እንደማልል ለራሴ ቃል አለኝ። ሰላማችን እንዲበዛ ሰላምን እንወቀው። እናክብረው። እናዋጣለት። ውዱን ሰላም እያጣጣማችሁና እያሰላሰላችሁ ዋሉ። ጁመዓ ሙባረክ