Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅርና የአብሮነት ትስስር ለባልና ሚስቶች . . . ከትዳር አጋራችሁ ጋር አብራችሁ ባሳለፋች | ሚዛናዊ ሕይወት

የፍቅርና የአብሮነት ትስስር

ለባልና ሚስቶች . . .

ከትዳር አጋራችሁ ጋር አብራችሁ ባሳለፋችሁ መጠን ፍቅራችሁ ይጨምራል፡፡ ፍቅራችሁ በጨመረ ቁጥር ደግሞ አብሮ የማሳለፍ ፍላጎታችሁ ይጨምራል፡፡

ከተጋቡ ብዙ አመታቸው ሆኗቸው እንኳን አብረው የሚያሳልፉና የሚዋደዱ ባልና ሚስቶች ካያችሁ ከእነዚህ ከሁለቱ ልምምዶች ውጪ ሌላ ምስጢር እንደሌለው ላስታውሳችሁ፡፡ እንደ መነጋገር፣ ይቅር መባባልና የመሳሰሉት መልካም የትዳር ምስጢራት ሁሉ የእነዚህ ሁለት መሰረታዊ ልምምዶች ውጤቶች ናቸው፡፡

“ታዲያ ከየቱ እንጀምር?” ለምትሉ፡-
አብሮ ከማሳለፍ ጀምሩ፤ ፍቅር ራሱ ይከተላል፡፡ ትዳራችሁን ከመጀመራችሁ በፊት የጀመራችሁት በፍቅር ነበር፡፡ እሱ ከጠፋ መጀመሪያ የተበላሸው አብሮ የማሳለፍ ጉዳይ ነው፡፡

“አብሮ ማሳለፍ ማለት ምን ማለት ነው?” ለምትሉ ደግሞ፡-
አብሮ ማሳለፍ ማለት፣ ጠዋት ቁርስ አብሮ መመገብ፤ ቢቻል ለምሳ መገናኘትና አብሮ መብላት፤ በስራ መካከል ምክንያትም ኖረ አልኖረ መደዋወል፤ ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ ማታ አብሮ ማምሸት፤ እቤት አብሮ መቀመጥ፤ በእረፍት ጊዜ አብሮ መውጣትና መግባት፤ ወሲብ-ነክም ሆኑ ከዚያ ውጪ የሆኑ የአካል ንክኪዎችን ማዘውተር . . .፡፡

“በግላችን የምናደርጋቸው ነገሮችና የምናገኛቸው ሰዎች ጉዳይስ?” ለምትሉት፡-
አብሮነት ሲጨምርና ከዚያው ጋር ፍቅር አብሮ ሲጋጋል በግላችሁ የምታሳልፉት ጊዜያችሁ ጉዳይ በራሱ መስመሩን ይይዛል፡፡

መልካም ትዳር!

D.r eyob
#ሚዛናዊ_ሕይወት_ለተሻለ_ነገ
@mizanawihewot