Get Mystery Box with random crypto!

#የስኬት_አቦጊዳ አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ አ-ቦ-ጊ-ዳ- ብሎ ስኬትን ከስር መሰረቱ አስጀምሮ የ | 𝙢𝙞𝙣𝙙𝙨𝙚𝙩 𝙚𝙩𝙝𝙞𝙤𝙥𝙞𝙖

#የስኬት_አቦጊዳ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

አ-ቦ-ጊ-ዳ- ብሎ ስኬትን ከስር መሰረቱ አስጀምሮ የሚያስጠና፣ አስጠንቶም የስኬት ዲግሪን የሚያስጭን ምርጥ መጽሐፍ፡፡

አስተሳሰብ ላይ፣ ጽናት ላይ፣ ውጤታማነት ላይ እንዲሁም ስኬትና ገንዘብ ላይ ልክ እንደ የኔታ መሰረት አስይዞ ለውጤታማነት የሚያበቃ!

ከ2 መቶ ሚሊየን በላይ ጎብኚዎች ባሏቸው የስኬት አስተማሪዎች የተዘጋጀ፣ ከፍተኛ ሽያጭ የተቀዳጀ መጽሐፍ ነው፡፡

ስኬታማ የሚያደርጉ መርሆችን ልክ እንደ አቦጊዳ ጥጥት የሚያደርጉበት መጽሐፍ!

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡
#የስኬት_አቦጊዳ


ጊዜ!
አንድ ቀን “ነገ” የሚባል ቀን አይኖርህም! ይህ መራርና ኮስተር ያለ ሀቅ መከበር አለበት፡፡ ከዛሬ ሃያ አመት በኋላ ይበልጥ የምትበሳጨው ባደረግካቸው ነገሮች ሳይሆን፣ ሳታደርጋቸው በቀረሃቸው ነገሮች ነው፡፡ ስለዚህ ከፊትህ የተጋረጡትን ሳንካዎች አንስተህ እንድትወረውራቸው… ከተረጋጋው ወደብ ተነስተህ እንድትቅዘፍ… የምስራቁን ነፋስ በመርከብ ሸራህ እንድትቆጣጠረው… ጊዜ የተሰኘው የስኬት አቦጊዳ ምእራፍ ያስተምርሀል፡፡

አስተሳሰብ
ብዙውን ጊዜ የአስተሳሰብህ እስረኛ በመሆንህ አስተሳሰብህን ካልቀየርክ በስተቀር በሕይወትህ ውስጥ ያለን ምንም ነገር መቀየር አትችልም፡፡ አስተሳሰብህ አልቀየር ብሎ አስቸግሮሀል? እነሆ የስኬት አቦጊዳ… አስተሳሰብ ምእራፍ ይረዳሀል- አስተሳሰብህን ስትቀይር ሕይወትህን ትቀይራለህ!

ጸጸት
ጸጸት ዛሬህን እየበላ ነገህን ለማኝ አድርጎ የሚያስቀር አደገኛ ጅራፍ ነው፡፡ በትናንት ስህተት ዛሬ መገረፍ፣ ነገ ደግሞ ማልቀስ የለብህም፡፡ የስኬት አቦጊዳው ዛሬን ከጸጸት ወጥተህ እንዴት በስኬት እንደምትኖረው ያስተምርሀል፡፡ የቀሪው ሕይወትህ የመጀመሪያ ቀን ዛሬ ነው!

ገንዘብና ስኬት
የሚሊየን ብር ሀሳቦች የሚገኙት በአንተ ውስጥ ነው፡፡ አንተ ብዙ ሀሳቦችን በፈጠርክ ቁጥር የሚሊዮን ብር ሀሳብ የመፍጠር እድልህ ይጨምራል፡፡ የሚያስፈልግህ ትንሽ ለወጥ ያለ ሀሳብ ማሰብ ወይም በተፈጠረው ሀሳብ ላይ ትንሽ ነገር መጨመር ነው፡፡ ይህ የስኬት አቦጊዳ መጽሐፍ አንዱ ተግባር ደግሞ ውስጥህ የተደበቁ የሚሊዮን ብር ሀሳቦችን እንድታወጣ መርዳት ነው- ገንዘብና ስኬት!

ደስታ
የስኬት አቦጊዳ አንዱ መመሪያ ይህ ነው- “ደስታ ሊያድነው ያልቻለውን የትኛውም መድኃኒት ሊያድነው አይችልም፡፡” ደስታህን የሚሰርቁ ነገሮችን ለይተህ መድኃኒቱን እንድታዝ ይህ መጽሐፍ ተዘጋጀ፡፡ በሕይወት ህመም ውስጥ ነህ? እነሆ መድኃኒቱ- ደስታ ምእራፍ!!!

ጽናት
ጽና! ይህ አሁን የገጠመህ ችግር ያልፋል፡፡ ይህ አሁን ያሸነፈህ ችግር ይሸነፋል፡፡ ይህ አሁን ያደከመህን ነገር ጽናት በሚባል ጋዝ ሲሊንደሮችህን ሞልተህ ለውጤታማነት የምታቀጣጥልበት የስኬት አቦጊዳ ነው!

በእያንዳንዱ የመጽሐፉ ገጾች አቦጊዳዎቹን ትማራለህ… ሕይወትህን ትቀይራለህ፣ ስኬትንም ያንተ ታደርጋለህ- በዚህ የስኬት አቦጊዳ መጽሐፍ!!!

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡