Get Mystery Box with random crypto!

ፈተና መብዛቱ ለኸይር ነው አብሽር አሏህ ፈተናን ባንተ ላይ ማፈራረቁ ስለጠላህ አይደለም። ነብያች | ሚናራ ቲቪ ~ 🅜𝕚𝕟𝕒𝕣𝕒 𝕥𝕧

ፈተና መብዛቱ ለኸይር ነው

አብሽር አሏህ ፈተናን ባንተ ላይ ማፈራረቁ ስለጠላህ አይደለም። ነብያችን - ﷺ - የቲም ነበሩ። እናታቸውን በ6አመታቸው አጥተዋል ፤ ርቧቸው ድንጋይ ሆዳቸው ላይ አስረዋል ፤ ሌላም ብዙ ፈተና ደርሶባቸዋል። ታዲያ አሏህ ጠልቷቸው ነው ብለህ ታስባለህን? በጭራሽ.
°
እንደውም በተቃራኒው እንደሚወድህ አመላካች ነው። ነብያችን - ﷺ - ይህን ስላሉ ፦ [ አሏህ ህዝቦችን ከወደደ ይፈትናቸዋል። ] (ሙስነድ ኢማሙ አሕመድ ፥ 23623). በሌላም ሐዲስ ላይ [ ከሰዎች ሁሉ በላእ የሚበረታባቸው ነብያቶች ናቸው ከዛም ደጋግ የአሏህ ባሪያዎች ናቸው። ] (ሲልሲለት አስሶሒሓህ ፥ 144).
°
አማኝ በሆነ ሰው ላይ ፈተና መብዛቱ አሏህ ለሱ መልካምን ነገር እንዳሰበለትም አመላካች ነው። ረሱል - ﷺ - እንዲህ ብለዋል ፦ [ አንድን ሙስሊም ከድካምም ይሁን ከበሽታ ከጭንቅም ይሁን ከሓዘን ከችግርም ይሁን ከጭንቀት ሙሲባ አይደርስበትም ከምትወጋው የሆነች እሾህም ብትሆን አሏህ በሷ አማካኝነት ከወንጀሉ ቢያፀዳው እንጂ። ] (ሶሒሁል ቡኻሪ ፥ 5641). አሏህ ፈተናን ታግሰው እሱ ከሚወዳቸው ባሪያዎቹ ያድርገን።

https://t.me/AbdulKereem_AlHanani