Get Mystery Box with random crypto!

'ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ' ። ⋅⋅⋅⋅⋅⋅⋅⋅⋅⋅ ። የሰላም ልጆች ሰላም ማጣታ | Michael Z Ethiop

"ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ"
። ⋅⋅⋅⋅⋅⋅⋅⋅⋅⋅ ።

የሰላም ልጆች ሰላም ማጣታቸው ለምንድን ነው?

ሁለቱ የክርስትና ማህበረ ሰቦች እንዲህ የሚያባላቸው ምንድን ነው? ማን ነው?

እኛስ የሰላም አቅም የማስታረቅ ኃይል እንዴት ነው ያጣን?

የእውነት ከአመኑበት ክርስትና በላይ የሚበልጥ ጠብ ኑሮ ነው?
ለሰማያዊ ዓላማ በንዲት ርትዕት ሃይማኖት ኪዳን ከተስማሙ ለምን ሴራ አሸነፋቸው?

ወይስ ኪዳኑን ለይምሰል ነው ያመኑበት ?

ስሁት ርዕዮት ስሁት ፖለቲካ ከክርስቶስ ወንጌል በላይ እንዴት ሊያሳምናቸው ቻለ?

የማንኛውም ሰው ሞት ይልቁንም የክርስቲያኖች ሞት የሚያበቃው ምን ቢሆን ነው?

ቤተ ክርስቲያንም ልጆቿን ማስታረቅ ለምን አልቻለችም ? ልጆቿን አንተም ተው አንተም ተው ማለት እንዴት አቃተን?

በመሳሰሉት እንወያይ እስቲ ወደመፍትሔም እንምጣ፡፡
እኔ ግን በግሌ ሁለቱን ክርስቲያን ወገኖች በስሁት ፖለቲካ ሲተላለቁ ማስታረቅ ባለመቻሌ የሁልጊዜ የህሊናየ ለምጽ ነው፡፡

☞ የኔታ ገብረ መድኅን እንየው