Get Mystery Box with random crypto!

ቲክቶክ ለወደድነው ቪዲዮ ገንዘብ ቲፕ የምናደርግበት አማራጭ እየሞከረ መሆኑን አስታወቀ። አዲሱ የ | Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ™ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

ቲክቶክ ለወደድነው ቪዲዮ ገንዘብ ቲፕ የምናደርግበት አማራጭ እየሞከረ መሆኑን አስታወቀ።

አዲሱ የቲክቶክ አገልግሎትም በማህበራዊ ትስስሩ ላይ ተጭነው ለወደድነው ምስል ጉርሻ ገንዘብ (ቲፕ) ለመስጠት የሚያስችል መሆኑም ነው የተነገረው። “ቲፕ (tips)” የሚል አማራጭ የሚመጣው አዲሱ አገልግሎት 5፣ 10 እና 15 ዶላር ቲፕ ማደረግ ያስችላል ሲል ዘ ቨርጅ የተባለው ድረ ገፅ አስነብቧል።

ከአማራጮቹ ውጪም ቲፕ ማድረግ የሚፈልግ ሰው ዝቅተኛ ተብሎ ከተቀመጠው 1 ዶላር ጀምሮ እስከፈለገው የገንዘብ መጠን ድረስ ቲፕ ማድረግ የሚችል መሆኑም ታውቋል። በቲክቶክ ላይ በጉርሻ መልክ (ቲፕ) የተሰጠው ገንዘብ ሳይቆራረጥ ለባለ ተንቀሳቃሽ ምስሉ (ቪዲዮ ባለቤት) የሚደርስ መሆኑም ነው የተሰማው።

በቲክቶክ ላይ የጉርሻ (ቲፕስ) ተጠቃሚ ለመሆን ተጠቃሚዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች እንዳሉም ኩባንያው አስታውቋል። ከመስፈርቶቹ ውስጥ ተጠቃሚው ቢያንስ 100 ሺህ ተከታዮች ያሉት ሊሆን ይገባል የሚለው ዋነኛው ሲሆን፤ የቲክቶክ የእድሜ መስፈርት ማሟላትም ሌለኛው ነው ተብሏል።

በቲክቶክ ላይ ቲፕ የሚያደርግ ወይም ጉርሻ የሚሰጥ ሰው እድሜው ከ18 ዓመት በላይ መሆን አለበት የሚለውንም ኩባያው በመስፈርትነት አስቀምጧል። የቲክቶክ ቲፕ አገልግሎት አሁን ላይ በሙከራ ደረጃ የተሰወኑ ገጾች ላይ ብቻ መለቀቁ የነገረ ሲሆን፤ በምን ያክል ስፋት እና መቼ ሙሉ በሙሉ ይለቀቃል የሚለው ላይ ግን ኩባያው አስተያየት አልሰጠም።

Inbox https://t.me/MiaComputech_bot

Join us on https://t.me/MiaComputech