# አዛኝቷ እመቤት አትርሺኝ አዛኝቷ እመቤት አትርሺኝ የፈጣሪዬ እናት አስታውሺኝ በምህረትሽ /3/ ተማለጂኝ የመከራ ነፋስ አጠቃኝ ህይወቴ ዝላለች ደከመኝ ከጥላሽ ስር /3/ አሳርፊኝ ከጭንቀት ባህር ውስጥ አድኚኝ ሰጥሜ እንዳልጠፋ አስጥይኝ እመቤቴ /2/ ተመልከችኝ አምላኬን ለማየት አልችልም ሀጢያቴ ብዙ ነው አይሆንም ካልደገፍሽኝ /2/ እኔ አልድንም አዛኝቷ እመቤት አትርሺኝ ድንግል እመቤቴ እባክሽ ከፈጣሪዬ አስታርቂኝ ከልጅሽ ያለ አንቺ ማን /2/ አለኝ አስታዋሽ አዛኝቷ እመቤት አትርሺኝ 294 views19:12