Get Mystery Box with random crypto!

የአምላክ ዐቃቤ ሕግ ገባሬ መንክራት በገድሉ ያወቅነው የእግሮቹ ትቢያ የአራዊት ስንቅ ነው ገብረ | የማህበር መዝሙር 🙏🙏🙏

የአምላክ ዐቃቤ ሕግ

ገባሬ መንክራት በገድሉ ያወቅነው
የእግሮቹ ትቢያ የአራዊት ስንቅ ነው
ገብረ መንፈስ ቅዱስ
የአምላክ ዐቃቤ ሕግ
የኢትዮጵያ ዋስ ነው ፈጥኖ የሚታደግ


ፀሐይ(2) የምድራችን ፀሐይ
በገድሉ ያበራል እስከ ጥልቁ ቀላይ
የመላዕክት ወዳጅ/2/
ገብረሕይወት ሰማይ
አዝ ======
መብረቅ/2/ሰረገላው መብረቅ
የቃልኪዳኑ ወንዝ ቢጠጣ የማይደርቅ
የፍጥረቱ ደስታ/2/
ገብረሕይወት ፃድቅ
አዝ =====
ኮከብ/2/ክብረ ገድላን ኮከብ
ዓለምን የሚያስንቅ መዐዛው የሚስብ
አርከ ሥሉስ ቅዱስ/2/
ገብረሕይወት ኪሩብ
አዝ =====
ስኂን /2/ ፄና ልብሱ ስኂን
የነፍስን አዳራሽ በገድል የሚሸፍን
የሚነበብ መፃፍ/2/
ገብረሕይወት ድርሳን
አዝ ======
መቅረዝ/2/ የማኅቶት መቅረዝ
ምድረከብድ ዝቋላን ያለመለመ ወንዝ
የዝጊቲው ፈዋሽ/2/
ገብረሕይወት ምርኩዝ