Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮች በአዳማ ከተማ ም/ቤቱ እያስገነባው የ | Adham TUBE አድሀም ቲዩብ أدهم تيوب

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮች በአዳማ ከተማ ም/ቤቱ እያስገነባው የሚገኝውን ህንፃ ጎበኙ

...
የአ/አ/እ/ጉ/ከ/ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን ሀጂ አማን ፣ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ ፈትሁዲን ሀጂ ዘይኑ ሙቅና ፣ ዋና ፀሀፊ ሼህ ሁሴን በሽርን ጨምሮ ከፍተኛ የም/ቤቱ አመራሮችና የስራ አስፈፃሚዎች በተገኙበት 1000ካ.ሜ ላይ ያረፈውን እና እየተገነባ የሚገኝውን ህንፃ በስፍራው ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል።
..
ይህ የህንፃ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የተጣለው በ2010 ቢሆንም በተቋሙ የውስጥ ችግር ለአምስት አመታት መሰረት ብቻ ተጥሎ ሳይገነባ ዘልቋል። የአ/አ መጅሊስ በአዲስ መልክ ከተዋቀረ በኃላ ባለፉት ሁለት ወራት ለአዳማ የህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ልዩ ትኩረት በመስጠት የመጀመሪያውን ወለል በማገባደድ ሁለተኛ ወለል ግንባታ ላይ ለመድረስ ችሏል።
...
በጉብኝቱ ወቅት የአ/አ/እ/ጉ/ከ/ም/ቤት ፕሬዝዳንት ግንባታውን በዋናነት እያስተባበሩ ለሚገኙ ሰራተኞች ልዩ ማበረታቻ አበርክተዋል። በመጨረሻም ግንባታውን እዚህ ለማድረስ አስተዋፆ ያበረከቱትን ባለድርሻ አካላትን በማመስገን በፕሮጀክቱ ሂደት ደስተኛ መሆናቸውን ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ በጉብኝቱ የተሳተፉት አመራሮችና ስራ አስፈፃሚዎች ገልጸዋል።