Get Mystery Box with random crypto!

#they_dont_care_about_us #The_people_must_stop_the_war ... | መጽሐፍ ቤት

#they_dont_care_about_us
#The_people_must_stop_the_war

... ተመልከት ከንጉሡ ጀምሮ የፖለቲካ እሳት ድሃውን እንጂ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ መሪዎችን አቃጥሎ አያውቅም።ከላመንክ አንድ በአንድ እያነሳን እንጫወት... እዚህ አገር ተምሮ እና ተንደላቆ የሚኖረው ብዙኃኑ "ግፋ በለው!" ሲል የኖረ ነው። መንግሥቱ ኃ/ ማርያም ያንን ሁሉ የድሃ ልጅ ማግዶ እሱ ዛሬ የት ነው!? "ዙንባብዌ" ተንደላቆ ይኖራል። የኦነግ መሪዎችን ተመልከት ...…ወያኔዎችን ተመልከት ...ምን ሆኑ ? ኢትዮጵያ ውስጥ የእርስ በርስ ጦርነት ወጣቱ ነው የሚማገደው ! ሚስኪን ወጣቶች! በፖሮፓጋንዳ ያበደ አለማስተዋል ነው። ወጣት አልዋጋም ካለ ....መሪዎች ሲጨባበጡ ነው የምታገኛቸው! እንዲች ብለው #ስንጥር አያነሱም። ምድረ ደም መጣጭ! ስንት ጓዶቻችን በርሃ ላይ ቀሩ ! ስንት 'ጂኒየሶች!' እንኳን ጦርነቱ የፖለቲካ ወሬው ያደንዝሃል። ከዚህ ከበከተ እንቶፈንቶ ራቅ ! ተማር ! ተማር ! ተማር ! አሁንም ተማር ! ማንም መሃይም መተኮስ ይችላል ! መግደል ጀብዱ አይደለም÷ ጅብም ሰው ይገድላል። ታይፎይድም ÷ወባም ሰው ይገድላሉ! ዓላማ የሌለው ሞት ; አገር ሸርፎ ከመሸጥ እኩል ነው። ለምንድን ነው የምትሞተው !? ለምንድነው ወጣት የሚሞተው !? ...ሊታረድ እንደሚነዳ በሬ የማይረባ ተስፋና ጥቅማጥቅም እንደርጥብ ሳር እያሸተቱ ወጣቱን ወደ ቄራ ይወስዱታል። ወጣቱም ብልጥ የሆነ ÷ ከሌላው የተለየ የገባው የረቀቀ ÷ የመጠቀ አድርጎ ራሱን ያያል ÷ ሲስተሙ ነው እንደዚያ የሚያደርግህ። ከአንተ በላይ አዋቂ የሌለ መስሎ እንዲሰማህ ....አለፍ ብለህ እጅህን ስትዘረጋ አረፋ ነው።ፖለቲካ እንኳን ይዘቱ ቅርፁ ለማንም ገብቶ አያውቅም ። ፈሳሽ ውሃ ነው ÷ ቅርፅ የለውም ። አንተ ውስጥ ሲገባ አንተን ይመስላል ÷ እኔ ውስጥ ሲገባ እኔን ....ሁላችንም ብርጭቆዎች ነን ። በስልጣን ከፍ ያሉት እያጋጩ 'ችርስ' የሚባባሉብን"

#አሌክስ አብርሃም
ከዕለታት ግማሽ ቀን ገፅ 132-133