ጦርነትን ማስቀረት! -------------------------- ከልምድ የተቀመረ ድንቅ ንግግር ነው ። "የጥሩ ስለላ ትልቁ ጥቅም ጦርነትን ማሸነፍ ሳይሆን ውጊያን ማስቀረት ነው " ቴኔት የአሜሪካው የስለላ ተቋም ዳይሬክተር ሲሆኑ በ2004 የኢራቁን ጦርነት " ሙሉ በሙሉ ተሳስተናል " ካሉ በኋላ ወደ ኋላ ተመልሰው ለጦርነት የፈሰሰውን ትሪሊዮን ዶላርና የሚሊዮን ዜጎችን እልቂት ባሰቡ ጊዜ ይህን ወርቃማ ዓረፍተ ነገር ተናገሩ ። ------ ጦርነት እጅግም አስቀያሚ የሰው ልጅ የድንቁርናና የክፋት መገለጫ ነው ። ከጦርነት ማንም ምንም አያተርፍም ። ሚሊየኖችን እንደቀልድ የሚቀጥፍ ፣ ሕጻናትን ያላሳዳጊ ፣ አዛዎንትን ያለ ጧሪ የሚያስቀር ፣ ግዙፍ ከተማን ወደ ምድረ በዳነት የሚቀይር አንዲትን ሃገር ወደ ኋላ የሚጎትት የደደቦች ጨዋታ ነው ። ጦርነትስ ካለ ሰውን ቀፍድዶ ከያዘው ከተፈጥሮ ህጎች ጋር ነበር .... ምድራችን እኮ እጅግ ሰቅጣጭ ፣ አስቀያሚና ዘግናኝ የጦርነቶች እልቂትን አስተናግዳለች ። ለምሳሌ ያህል ከክርስቶስ ልደት በፊት ፐርሺያውያን ፣ግሪካውያን ከሌሎች ግዛቶች ጋር ያካሄዱትን አስቀያሚ ጦርነት ትተን ከዚያ ወዲህ ታላላቅ እልቂቶችን ብንመለከት ። ------- ለምሳሌ ያህል --- ከ264 -146 B C ሮምና ካርቴጅ ባካሄዱት ጦርነት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ አልቋል። --- ዊ ፣ሹ እና ው የተባሉ ጎሳዎች ባደረጉት ጦርነት ወደ 38 ሚሊዮን ህዝብ ሞቷል ። አይገርምም ! --- በቻይናና በእስልምና ሃገሮች መካከል በተደረገ ጦርነት ወደ 22 ሚሊዮን ሕዝብ አልቋል ።የሃይማኖት ጦርነት በሉት ። --- በሞንጎልና በኢራሽን ግዛት መካከል በተደረገ ጦርነት ወደ 34.6 ሚሊዮን ሕዝብ አልቋል ። ሚሊዮኖች እያልኩ ነው ---በስፔንና በሜክሲኮ ፣ በፔሩና በሚያ ግዛቶች በተደረገ መራራ ጦርነት ወደ 34 ሚሊዮን ህዝብ ሞቷል። ---በኘሮቴስታንትና በካቶሊክ ጦርነት ወደ 2.8 ሚሊዮን ህዝብ አልቋል ። --- በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የዘረኝነት ጦርነት ወደ 1.7 ሚሊዮን ህዝብ አልቋል ። ------------ ---በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ወደ 24 ሚሊዮን ህዝብ ሞቷል --- በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወደ 69 ሚሊዮን ሕዝብ ወደ አፈርነት ተቀይሯል ። --- ከ1950-1953 ዓ.ም በሰሜን ኮሪያና ደቡብ ኮሪያ ጦርነት ከ3 ሚሊዮን እስከ 5 ሚሊዮን ህዝብአልቋል ። --- በሁለቱ ቬትናሞች ጦርነት እስከ 1.7ሚሊዮን ህዝብ ሞቷል ። ---- በባንግላዲሽና በፓኪስታን በ1971 ዓ.ም በተደረገ ጦርነት እስከ 3 ሚሊዮን ህዝብ አልቋል ። --- በሰሜንና ደቡብ ሱዳን በተደረገ ጦርነት እስከ 1.4 ሚሊዮን ህዝብ አልቋል ጦርነት ሚሊዮኖችን ወደ አለመኖር ከመቀየሩም በላይ የአንዲትን ሃገር ትውልድ እድል በዜሮ ያባዛል ። --------- እኔ የተደራጀ የጦር መሣሪያና የሰለጠነ ወታደር አለኝ እያሉ የጦርነት አታሞ መምታት ጅልነት ነው ። የተደራጀ ሃይል ስላለህ አሸናፊ አትሆንም.... ጀግንነትስ ካለ ጦርሜዳ አንድም ሰው ሳይሞት መማረክ ስትችል ነው ።ሰው እያደገ ሲሄድ ጦርነቱንም አየቀየረ ይሄዳል ። ኢትዮጵያችን ከራሷም ሆነ ከአለም አቀፉ ቀፋፋ ታሪክ መማር ካልቻለች በርግጥም ለሚመጣውም ትውልድ የዓለም ጭራነትን ታወርሳለች። 1.5K viewsmelat..., 09:38