እናና እረኛ ፥ እሆናለሁ ፣ በግ ፥ እጠብቃለሁ ፣ ብለሽ ፥ እንዳልነበር ፣ በግ ፥ አበቃሽ ላፈር ? እንዳብዬ ፥ አስተዋይ ፣ መቼም ፥ አይኔ ባያይ ፣ ፍቅር፥ ሲናፍቀን ፣ እንባ እንዴት፥ አያንቀን ? ዘመን ቢጎል ካምናው ፥ ዘንድሮ ቢከፋም ፣ ሐገር ብትመነምን ፥ ደግሰው አይጠፋም ፣ ነብስ ንጹህ ስትሆን ፥ ትዘራለች ፍቅር ፣ እንኳን ደጉ ቀርቶ ፥ ክፉም ይላል ይቅር ፣ ቸርነት እምዬ ፥ እናንዬ አማራ ፣ መስለው እዬታዮኝ ፥ እምባዬ እንዴት ያብራ ፣ ጥጋቡ ይሉት በግ ፥ ወግቶኛል እያለች ፣ በባረቀ ሃሳብ ፥ ያች እንቡጥ ተቀጨች ፣ ባይለው ነው እንጂ ፥ ትረፊ ባይላት ፣ በጉ ወንፈል ያውቃል ፥ እንኳንስ ሊገላት ፣ ቀልብ የታጣ ጊዜ ፥ ሀገር ይታመማል ፣ የባረቀ እያለ ፥ እንዴት ቀንድ ይታማል ? ወግ ጥሰው ቢንቋት ፥ አልፋለች ግዴለም ፣ ጫንቃዋ ያዘለው ፥ ጅራፍ ብቻ አይደለም ፣ እንዳረገው ፍቅር ፥ አብነትን ያ ደም ፣ ምናለ እውን ሆኖ ፥ ለሐገር ቢደገም ! እናና ዳን አበባው ንጋቱ ነሐሴ 2014 ዓ.ም 2.7K viewsmelat..., 10:52