➨ አለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር እግዚአብሔር በእኛ ላይ አላማ ነበረው። ➨ ወላጆቻችን ሳንወለድ በእኛ ላይ አላማ ይኖራቸው ይሆናል። አላማቸው ግን ስሜን ያስጠሩልኛል የምል ይሆናል። ➨ እርሱ የህልውናና የስም መገኛ ነውና እጠፋለሁ ብሎ ስሙን እናስጠራ ዘንድ አልፈጠርንም። ገና ህልውናና ስም ሳይጀመር ወደደን። ➨ ከመፈጠራችን በፊት የወደደን ከመገኘታችን በፊት የመረጠን ወላጆቻችን ሳያውቁን ያወቀን ወላጆቻችን ሳይወለዱ የወደደን ድንቅ አምላክ ነው። ➨ ወላጆቻችን ተወልደን ብያዩን ሳሱልን፣ እሱ ግን ደም ሳይረጋ አጥንት ሳይሰካ ከማኅፀን ህልውናችን ሳይጀመር ወደደን። ➨ ወላጆቻችን አድገን ቁም ነገራችንን መዝነው ወደዱን። ➨ እሱ ግን ገና ደግና ክፉ ሳንሰራ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር አፈቀረን። ➨ ከዓለም በፊት ወዶናልና ዓለም ሲያልፍም ይወደናል። ከዘመን በፊት ወዶናልና ዘመን ሲታጠፍም ይወደናል። ከዓለም በፊት ግዜ አልነበረም ➨ከጊዜ ውጪ ወዶናልና ፍቅሩ በግዜ የማያበቃ ዘላለማዊ ነው። ጸጋ ይብዛላችሁ 124 views05:59