Get Mystery Box with random crypto!

አጀብ ነው አቦ! ሰይጣን በሀሳቡ ብዙ ሰዎች ሰርቶ ጀነራል ዶክተሩን ከፋፍሎ ለይቶ ለግብሩ የፎቅ | For ethios መፀሀፍ, ትረካ, አጫጭር ታሪኮች 📚📜📓🚵🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪novels, 🇹ethiopians books

አጀብ ነው አቦ!

ሰይጣን በሀሳቡ ብዙ ሰዎች ሰርቶ
ጀነራል ዶክተሩን ከፋፍሎ ለይቶ
ለግብሩ የፎቅ ቤት መገንባትን ሲሻ
ለህመሙ መዳኒት ሲያስብ ማስታገሻ
እሳትን ሲያሳየን በጠጠር ወርቅ አርጎ
ለሞታችን ድግስ ዝምታን ሰርጎ
መድከምን ስናስብ መዛል መሰልቸቱን
ምርጫችን ይሆናል ለሰዓታት መኖሩን
ጉልቻ ቢቀየር በሆታ ቀብተን አንግሰን
ለካስ ከዛው ኖሯል ማያጣፍጥ ወጥን

ግን.......... ምን ቢያጨስብን ነው
ምን አዚም ቢያስነካን
የአመድ ዘመድ መሆን የንጉስ ልጅ ሳለን።

ቴዲ ጌትነት።