-የህጻን ልጅ ጥርስ መቦርቦር የተለመደ እና በማንኛውም ልጅ ጥርስ ላይ ሊታይ የሚችል ነው -አንድ ህጻን ከተወለደ ከ6ወር ጀምሮ የወተት ጥርስ ሊያበቅል ይችላል -አንድ ህጻን አንድ የመጀመሪያ ጥርሱን ወይም ጥርሷን መብቀል ሲጀምር በንጹህ ለስላሳ ጨርቅ እና በንጹህ ውሀ ብቻ በቀን ሁለት ጊዜ ከ1ደቂቃ ላልበለጠ መጸዳት መጀመር ይኖርበታል -አንድ ህጻን የእርሱን ጥርስ በራሱ ማጽዳት ወይም መቦረሽ እስኪችል ድረስ ቤተሰብ ተከታትሎ የህጻኑን ጥርስ መቦረሽ እና ልጁም ባህል እንዲያደርገው ማለማመድ ይኖርበታል -የማንኛውንም ህጻን ልጅ ጥርስ ተከታትሎ በማጽዳት ሊከሰት የሚችለውን የጥርስ መቦርቦር በእጅጉ መቀነስ ብሎም ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ መከላከል ይቻላል… ቸር ነገር ያሳየን ያሰማን!!! 187 viewsWon Getaneh, 14:21