Get Mystery Box with random crypto!

የሰኳር ህመም እና የአፍ ጤና ምን ግንኙነት አላቸው ? የስኳር በሽታ በባህሪው የሰውነታችንን ተ | Dr. Won(Dental consulting)

የሰኳር ህመም እና የአፍ ጤና ምን ግንኙነት አላቸው ?


የስኳር በሽታ በባህሪው የሰውነታችንን ተፈጥሮአዊ በሽታ የመከላከል አቅም የማዳከም፣ አፋችን ወስጥ ያሉ የሰውነት ክፍሎችን ጥንካሬ የማሳጣት፣ የምራቅ እጢዎችን ምራቅ የማምረት አቅም ማሳጣትና አፋችን በምራቅ እራሱን የማጽዳት አቅም የመንሳት ብሎም አፋችን ውስጥ የላሙ ምግቦች ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ  ያደርጋል።


እነዚህ ችግሮች ከሰውነታችን የበሽታ መከላከል አቅም መዳከም ጋር ተደማምሮ የተለያዩ የአፍ ውስጥ በሽታዎች በቀላሉ እንድንጋለጥ መንገድ ይከፍታል።  


አፋችን የያዛቸው እንደ ጥርስ እና አቃፊ ክፍሎች ድድ እና የድድ አጥንት በቀላሉ ሽባ የመሖን እና የጥርሶች ጥንካሬ ደካማ የመሖን እንዲሑም ብዙ ጥርሶች በአንድ ጊዜ የመነቃነቅ ባሕሪ ያሳያሉ

ጥርሶች ከመነቃነቃቸው በተጨማሪ በቀላሉ መቦርቦር እና ሕመም ሊያስከትሉ ይችላሉ

ሌላው በስኳር በሽታ ምክንያት አፋችን ለመጥፎ ጠረን በቀላሉ ሊጋለጥ ይችላል

እንደ አጠቃላይ አፋችን ውስጥ ያሉ ጠቃሚ ባክቴሪያዎች ቁጥራቸው እየቀነሰ በተቃራኒው ጎጅ ባክቴሪያዎች ቁጥራቸው እየጨመረ አፈችን እና መላው አፋችን ውስጥ ያሉ ክፍሎች ለጎላ ችግር ይጋለጣሉ