Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒሰትር መረጃዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ mereja_neaea — ትምህርት ሚኒሰትር መረጃዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ mereja_neaea — ትምህርት ሚኒሰትር መረጃዎች
የሰርጥ አድራሻ: @mereja_neaea
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.23K
የሰርጥ መግለጫ

Students Info

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-30 19:15:53 #MettuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ 4 ሺህ 500 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።

አዲስ ገቢ ተማሪዎቹ በመቱ እና በደሌ ካምፓሶቹ የሚመደቡ መሆናቸው ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በሂሳብ እና ማኔጅመንት የሦሥተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን የተቋሙ ከፍተኛ ኃላፊ ድሪባ ገመቹ (ዶ/ር) ለኦቢኤን አፋን ኦሮሞ ተናግረዋል።

የመማር ማስተማር ሥራውን በ2004 ዓ.ም የጀመረው መቱ ዩኒቨርሲቲ፤ አሁን ላይ በሁለት ካምፓሶች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብሮች ከ20 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል።

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
2.0K viewsEYU, 16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 19:52:37 #DebreBerhanUniversity

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም በመደበኛ መርሃ-ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ሚያዚያ 29 እና 30/ 2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በመሆኑም አዲስ ገቢ ተማሪዎች በተገለጹት ቀናት በአካል በመገኘት ምዝገባ አድርጉ ተብሏል።

መደበኛ ትምህርት ግንቦት 01/2014 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገልጿል።

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
2.0K viewsEYU, 16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 19:52:07
1.9K viewsEYU, 16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 16:50:12 #AAU

የአዲስ ተማሪዎች ጥሪ ፦

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2014  የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ሚያዚያ 24 ቀን እና ሚያዚያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥሪ አቅርቧል።

ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ የሚያስፈልጋችሁ ነገሮች ከላይ ተዘርዝረዋል አንብቧቸው።

ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን ተገልጿል።

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም ከ https://portal.aau.edu.et ማግኘት ትችላላችሁ።

በሌሌላ በኩንል ፤ ተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ከሚያዚያ 27 እና 28 2014 ዓ.ም እንዲያመለክቱ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አቅርቧል።

መረጃው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ነው የደረሰን።

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
2.1K viewsEYU, 13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 09:09:42 የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ
-----------------------------
ትምህርት ሚኒስቴር የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ አድርጓል።

የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ምደባ ተደርጓል።

ከዚህ በፊት በተገለጸዉ የመቁረጫ ነጥብ እና ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋርና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች ምደባ የሚያስገኝላቸው ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት በድህረገፅ፡-https://result.ethernet.edu.et ፣ በSMS፡- 9444 እንዲሁም በቴሌግራም፡- @moestudentbot መጠቀም ይችላሉ።

ተማሪዎች ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችው ማንኛውም ጥያቄ በድህረገፅ https://complaint.ethernet.edu.et በማመልከት ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 24/2014 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ጥሪ ያቀርባል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
2.4K viewsEYU, 06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-09 19:25:43 #MettuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ የአንደኛ እና 2ኛ ዓመት መደበኛ እና የእረፍት ቀናት ተማሪዎች የ2014 ዓ.ም የ2ኛ ሴሚስተር ምዝገባ መጋቢት 05 እና 06/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

መጋቢት 07/2014 ዓ.ም ብቻ በቅጣት መመዝገብ ይቻላል ተብሏል።

የመመዝገቢያ እና የትምህርት ክፍያ በመቱ ዩኒቨርሲቲ የኢ/ን/ባ ሂሳብ ቁጥር 1000025592569 በመክፈል ደረሰኝ መያዝ እንዳለባቸው ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

የመደበኛ ተማሪዎች ትምህርት መጋቢት 07/2014 ዓ.ም ይጀምራል የተባለ ሲሆን የእረፍት ቀናት ተማሪዎች ትምህርት መጋቢት 11/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

በመንግስት ተቋማት ስፖንሰርነት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የስፖንሰርሺፕ የውል ስምምነት እንዲያሟሉ ተብሏል።

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
4.7K viewsEYU, 16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-09 19:25:41 #DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ እና 4ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የ2014 ዓ.ም የአንደኛ ሴሚስተር ምዝገባ መጋቢት 08 እና 09/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

መጋቢት 10/2014 ዓ.ም ብቻ በቅጣት መመዝገብ ይቻላል ተብሏል።

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
4.1K viewsEYU, 16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-28 19:48:08 ማስታወቅያ
#NEAEA

ለ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቅያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ ከውጤት ጋር በተያያዘ ከሐሙስ የካቲት 17/2014 ዓ.ም ጀምሮ በኦንላይን እና በአካል እየተገኛችሁ ቅሬታ ማቅረባችሁ ይታወሳል፡፡

ቅሬታ የመቀበል ሂደቱ እስከ ማክሰኞ የካቲት 22/2014 ዓ.ም 11፡30 ሰዓት ድረስ መሆኑን በማወቅ ቅሬታችሁን በጊዜ ገደቡ እንድታቀርቡ እያሳሰብን ከዚህ ጊዜ ገደብ ውጪ የሚመጡ ቅሬታዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
4.9K viewsEYU, 16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-07 20:27:22 #Update

የፈተና ውጤታችሁን ከነገ ጀምሮ መመልከት ትችላላችሁ።

በህክምና /Medicine/ ሙያ የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች የፈተናው ውጤት ከነገ ጀምሮ መመልከት ይቻላል።

ከታህሳስ 21-27/2014 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ የህክምና /Medicine/ ተመዛኞች ከየካቲት 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተመዛኞች ከየካቲት 1 ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0118275936/37 በመደወል ወይም በኢሜይል hpcald@moh.gov.et ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ጤና ሚኒስቴር በሌሎች የሙያ ዘርፎች ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች ውጤት በቅርብ ቀን ውስጥ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
6.3K viewsEYU, 17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-04 21:09:25 #HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች የ2014 ዓ.ም የ2ኛ ሴሚስተር የምዝገባ ጊዜን አሳውቋል።

የመደበኛ ፕሮግራም የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 14 እና 15/2014 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን ትምህርት የካቲት 16/2014 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

የዕረፍት ቀናት ፕሮግራም የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ከየካቲት 16 እስከ 18/2014 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን ትምህርት የካቲት 19/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

@MEREJA_NEAEA
#SHARE
5.5K viewsEYU, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ