Get Mystery Box with random crypto!

#OdabultumUniversity በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ | ትምህርት ሚኒሰትር መረጃዎች

#OdabultumUniversity

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9 ሲሆን ምዝገባ የሚካሄደው ግንቦት 10 እና 11 ይሆናል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡-

፨የ8ኛ ክፍል ሰርትፊኬት ኦርጅናልና ኮፒ

፨የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ኦርጅናልና ኮፒ

፨ከ9-12ኛ ክፍል የተማራችሁበት ትራንስክሪብት ኦርጅናልና ኮፒ

፨አራት ፓስፖርት ሳይዝ ጉርድ ፎቶ ግራፍ እንዲሁም

፨አንሶላ፣ የስፖርት ትጥቅ፣ የትራስ ጨርቅ እና ብርድ ልብስ በመያዝ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጭሮ ከተማ በሚገኘዉ ዋናዉ ካምፓስ በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ www.obu.edu.et ወይም https://t.me/OBURegistrar ይጎብኙ

የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

       
@MEREJA_NEAEA
#SHARE