Get Mystery Box with random crypto!

Mereb: መረብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ mereb_2012 — Mereb: መረብ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mereb_2012 — Mereb: መረብ
የሰርጥ አድራሻ: @mereb_2012
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.78K
የሰርጥ መግለጫ

መረብ ቁጥር አንድ የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርም ነው።የታፈኑ ድምፆች ከፍ ብለው እንዲሰሙ እንሰራን። ስለፍትህ እንተጋለን ።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-30 22:19:45
444 views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 20:40:04 ወገኖቻችን ምን እያደረጉ ነው ያሉት?

ወገኖቻችን የአልሞት ባይ ተጋዳይ መንፈራገጥ ላይ ናቸው። ቡጭሪያቸው ወዲያም ወዲህም ነው። ያገኙትን ይነከሳሉ፣ ያረፈደ ብልጠታቸው እስላሙን የጦስ ዶሮ አድርጎ በሴራ ለማስበላት ብዙ ሞክረው ቀላል በማይባል ደረጃ ተሳክቶላቸዋል።

ይዞ ሟችነት እንዲህ ነው! ያላቸው አማራጭ ሁለት ነው። የገርገራ (የጣዕረ ሞት) ጊዜን ማራዘም (Decreasing at a decreasing rate) ላይ መሰንበት! ከመሞት መሰንበት! አሊያም እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቀልን መርህ አድርጎ ይዞ ሟችነት ላይ ምንችክ ማለት!!

ወዳጄ የክርስቲያን አክራሪነት እያስደነገጠህ ከሆነ አይግረምህ ነገሩ “ሀከዛ” ነው!

ግና መፍትሄው ምንድን ነው ካልከኝ አድምጠኝ።

የግሪቫንስ ፖለቲካ የሚባል አለ። የመጥፋት፣ የመረሳት ስጋት ያለባቸው አካሎች ወደ ተረትነት ከመቀየራቸው በፊት ማንኛውንም ነገር ያደርጋሉ። እሪሪሪታው እየየየው ይቀጥላል። ዓላማው መንፈሳዊ ሳይሆን ብሶተኛ፣ የተበዳይነት ስሜትን ያዳበረ በቀለኛ ኃይልን መሰብሰብ ብቻ ነው። ይህ ተወገርኩ ተቀጠቀጥኩ፣ ነደድኩ እየየው ለሚዲያ ማሳያ ይፈልጋል። በደሉ እውነተኛ ከሆነ እውነተኛ ታጋዮችን ያፈራል። ቤተ-ክርስቲያኗ ብትነጥፍ እንኳን እየተበደለች ከሆነ አላህ ከውስጧ በደልን የሚገፈትሩ ወንዶችን፣ ትውልዶችን ይፈጥራል። አላህ ሃይማኖትህን ሳይሆን መበደልህንና ጥረትህን ነው የሚመለከተው።

ግና እሪታውና ኡኡኡታው ማሳያ አልባ፣ ሀቅ የከዳው የሴራ ጩኸት ከሆነ ጊዜ ያከስመዋል። ግና በራሱ አቅም ማንሰራራት የተሳነው ያገኘው ጋር በመጋጨት፣ በመደቆስ፣ በመገፋት ውሥጥ እሮሮ የኳተረው አቅም ሆኖ ቀስ በቀስ ተመልሶ ለመምጣት “የጠላት ያለህ!” እያለ ይቦጭርሃል! ስለዚህ ወዳጄ እስከመጨረሻው ዝምብለህ ልታካትማቸው ከፈለግክ በፍጹም በፍጹም እትንካቸው፣ የመበደልን ጉልበት አትስጣቸው! ብቻ ይዘውህ እንዳይሞቱ ራስህን ከቻልክ ከጦስ ዶሮነት አግልል፣ ካልቻልክ ራስህን ተከላከል! ከዚያ ያለፈ ዝምምምምም በላቸው! ያኔ ልጆቻችን በተረት ተረት አሊያም ታሪክ መጽሀፍ ላይ ያውቋቸዋል። እነሱም የማይቀረውን ተፈጥሯዊ ሞታቸውን ከብዙ መንፈራፈር በኋላ ይሞታሉ። ያኔ የሮም ታሪክ ራሱን ይደግማል! ደወልና ደዋዩ ብቻ ይቀሩና ታርፋለህ!! እናም አትንካቸው! አጀንዳም አታድርጋቸው! ረስተሃቸው ዝምምም ብለህ በራስህ ላይ ሥራ!!
744 views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 20:40:04 የኛዎቹ ግን ሶሎሞናዊ ነን ብለው መንግሥትነትን ወረሱ፣ መንፈሳዊነት በነ ይምርሃነ ክርስቶስ፣ በነላልይበላ ጊዜ ቀረና መንፈሳዊነትን እየሰበከ ዓለማዊነትን የሚኖረው፣ ገዳማትን እየተከለ ግና ገዳማትን የሚያረክሰው፣ ለፊውዳሊዝም ሥርዓቱ ፊውዳል ቤተ-ክህነትን የተከለው የአጼው ሥርዓት ነገሰ፣ ተጠናከረ። ሁሉም ነገር ወደ “መስቀል ጦርነት” ተባለና አያል መቶዎች አመታትን ያሳለፈ የጦርነት ታሪክን በአገራችንን ምድር ላይ ጻፈ! መንፈሳዊነትና ኦርቶዶክስነት ይጠጌ አይነኬ (asymptotic) ሊሆኑ ተዳረሱ። ይጠጋጋሉ ግና የማይነካኩ ሆኑ! ታላቋ ቤተ-ክህነት በአቡነ ተ/ሃይማኖት ፎርሙላ ፊውዳሊስት ሆነችና አረፈችው! ደጀሰላሞች መንፈሳዊነትን እየራቃቸው መጣና በጥላቻ ስብከት ተሞሉ!
ይህ መልሶ ግብን ሊያሳካ የሚችል ነፍጠኛ፣ አመጸኛ፣ አሸባሪ አደረጃጀትን እንጅ መንፈሳዊ ባለጽናትና ሩቅ አሳቢ ኤጀንቶችን አሳጣቸውና ዛሬ ነፍጠኛ ዲያቆናቱ እንደ አበደ ውሻ ተቅበዘበዙ!

ምን ተስፋ አስቆረጣቸው ?

ሁነኛ መንፈሳዊ የሆነ የአማኝ እጦት
ቤተ-ክህነቷና ቀሳውስቶቿ በታሪክ ውሥጥ በተለይም በአቢሲኒያ በአሃዝም በሚናም የበላይ ሆነው ኖረዋል። በተደጋጋሚ የአባላት ወይም የአማኝ መቀነስ ወይም የመጥፋት አደጋ አጋጥሟቸዋል። በድህረ ግራኝ በአቢሲኒያ ከአስሩ ዘጠኙ እስላም እንደሆኑባቸው ሁሉ አብዝተው ጽፈዋል። ግና እንዲህ ያለውን የአማኝ እጦት ስጋት በምን ፈቱት?

ዴሞግራፊ ሲሳሳብህ ዴሞግራፊህን (የህዝብ ብዛትህን) በሶስት መልኩ ታስተካክላለህ፣ ታሻሽላለህ። አንድም በመዋለድ፣ ሁለትም በአስተምህሮ ሶስትም በግድ ታጠምቃለህ። የኢትዮጵያ ኦ/ቤተክርስቲያን ሰዎች ምዕምኖቻቸው በብዛት እንዲወልዱ በማድረግ በማበረታታት ሥራ ላይ አይደሉም፣ ሙከራው ቢኖርም ምዕምኖቻቸውም ይህን በቀላሉ ሊፈጽሙላቸው አልቻሉም። ዲያቆናቱ ቀሳውስቱና መምህራኑ ቤተ-ክርስቲያኗንና አስተምህሮዋቿን በአገሪቱ ቋንቋዎች ሁሉ ለማስተማር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ኖረዋል፣ ስብከቶቻቸው ትምህርቶቻቸው መንፈሳዊነትን ረስተው እሮሮ፣ የጥላቻ ቅስቀሳ፣ የአጼው ናፍቆት ትርክትና ትምክህት ከሆኑ ዘመናት አልፈዋል።

ስለዚህም እንደ ፕሮቴስታንቱና እንደ ሙስሊሙ ሃይማኖቱን ሰብከው በርካቶች የኢ/ኦ/ቤተክርስቲያንን እንዲቀላቀሉ ማድረግ አልተቻላቸውም። ሶስተኛው በግድ ማጥመቅ ዛሬ አይቻልም! ታቦት ይዞ ንጉስ ቀስቅሶ አንድን ህዝብ ወርሮ በግድ ማጥመቅና ማቁረብ ዛሬ አይቻልም፣ ነፍጠኛ ተከትሎ ደጃዝማችና ራስ አጅቦ ሄዶ አንድን ጎሳና ብሄር ከነመሬቱ መጸበልና ማጥመቅ ዛሬ በፍጹም አይታሰብም።

ስለዚህም በነፍጥና በአጼው ሥርዓት እያስፈራሩ በጉልበት ማጥመቀ ድሮ ቀርቷል ማለት ነው። ታዲያ በመዋለድ በስብከትና አስተምህሮ እንዲሁም በግድ በማጥመቅ አባላትን ወይም ምዕምንን ማብዛት ካልተቻላቸው በየቀኑ በፕሮቴስታንትና በሙስሊሙ አስተምህሮ ምክንያት የሚከዳቸውን አባላት እንዴት ማስቆም ባይችሉ መተካት እንዳለባቸው ግራ የገባቸው ወገኖቻችን ካገኙት ጋር መጋጨትን፣ የግሪቫንስ ፖለቲካ ታክቲክን፣ የጅምላ ጭፍጨፋና የሽብር ሂደትን መከተላቸው የሚጠበቅ አይሆንም?

ቤተ-ክርስቲያኗ በሲሶ መንግሥትነት ዘመኗም ሆነ ከዚያ ወዲህ የሰበሰበችው፣ ያካበተቸው ሀብት እጅጉን ብዙ ነው። ይህ ሀብት ትውልድ ቀረጻ ላይ አልዋለም! ሀብትና ሌጋሲን አስቀጣይ የበቃ የሰከነ መንፈሳዊ ትውልድ አልተዘጋጀም! በመጡባችሁ ስብከት የደነበረ እንጅ የሰከነ ትውልድን መፍጠር የማይችል መምህራን ተሰግስጎባታል።

ዛሬ በወረራም በቢሮክራሲ ላዕላይነት ሳቦታጅም ምክንያት እንዳሻት ኣከብታ የምትቆጣጠራቸው ቦታዎችና ውብ አብያተ ክርስቲያናት እንደ አውሮፓ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ከመቶ አመታት በኋላ ለእስላሞች እየተከራዩ ረመዷን እንደማይሰገድባቸው እርግጠኛ መሆን አይቻልም!
እንደ ድሮው በኢትዮጵያ ስም እየማሉ የኢትዮጵያ ታሪኳና መልኳ ቤተ ክርስቲያኗ ትሆን ዘንድ ከመመኘት ያለፈ ማድረግ ዛሬ አልተቻለም።

በኢትዮጵያዊነት ካባ ሥር የተከለለው ምስጢር ሁሉ ዛሬ ተበትኖ አደባባይ ላይ ተበትኗል። አማራጭ ሲጠፋ ወደ አ*ማራ ክልል ስደቱ ተፋጥኗል። ከዚያም አሳደው አ-ማራ ሳይንት ሊያስገቧት የሚሯሯጡቱ ልጆቿ የቂል ጉዞ ላይ ናቸው።የበላይነትን ሲጠባ የኖረ እኩል ነህ ሲባል የተበደለ ይመስለዋልና እቡይ ምሁራኖቿ ከዘመን ጋር ሊያስታርቋት ከቶ አልተቻላቸውም! ስለዚህም ዛሬ ቤተ-ክርስቲያኗ ዓይኗ እያየ በሁለንተናዊ ተክለ ቁመናዋ ላይ አይደለችም! በስነ-ልቦና የተጠቂነት ልክፍትን እያወረሷት እንጅ ተተኪ ሃይልን እያዘጋጁላት አይደለምና!!

ምን ተስፋ አስቆረጣቸው?

አራት፡- የስልጣኔ ገደብ

በኢኮኖሚክስ ቲዮሪ ቶታል ፕሮዳክት ከርቭ የሚባል ከርቭ አለ። ይህ ከርቭ ምርታማነትና የምርት ግብአትን ምጣኔ ያሳያል። ሶስት ደረጃዎች አሉት መጀመሪያው increasing marginal returns ይባላል። በዚህ ስቴጅ በእያንዳንዷ ተጨማሪ ሀብት የተሻለ ተጨማሪ ጥቅም ወይም ምርት የምታገኝበት ነው። ግብአት በጨመርክ ቁጥር የበለጥ ምርት ወይም እድገት ታገኛለህ። ሁለተኛው እርከን Diminishing marginal returns ይባላል። በዚህ ግብአት በጨመርክ ቁጥር ምርትህ እድገትህ ያድጋል፣ ግን በግብአትህ ልክ ወይም ከዚያ በላይ አይደለም የምታመርተው። እድገትህ በዲክሪዚንግ ሬት ነው የሚያድገው።

ሶስተኛው ርከን ጠቅላላ ምርትህ የፈለግከውን ግብአት ብትጨምር ምንም ዓይነት እድገት የማያሳይበትና ከዚያም እንዲያውም ግብአት በጨመርክ ቁጥር እየከሰርክ የምትመጣበት ስቴጅ ነው። Negative marginal returns ይባላል። በዚህ ስቴጅ ውሥጥ ከገባህ አርጅተሃል፣ የሚጠብቅህ ሞት ነው። ከመጃጃት ከመሞት አትድናትም! ያለህ አማራጭ ሁለት ነው። ሞትህን ማዘግየት! ወድቀትህን ማንቀራፈፍ! Decreasing at a decreasing rate ላይ ለመቆየት መጣጣር፣ መፈራገጥ! ሞትህ ግን አይቀርም! ይህ የተፈጥሮ ህግ ነው። እንደ ቦረቅክ አትቀርም፣ ትጎለምሳለህ፣ ታረጃታለህ ትሞታታለህ!

ታዲያ ይህ ከወገኖቻችን ጋር ምን አገናኘው? ካላችሁኝ የሚያገናኘው ቤተ-ክርስቲያኗን ከትናንቷ ቤተ-ክርስቲያን አንጻር ስትታይ እዚህ አስከፊው Negative marginal returns እርከን ላይ መገኘቷ ነው። የሶሎሞናዊውን ሥርዓት ያመጣችው የአቡነ ተ/ሃይማኖቷ ቤተ-ክህነት ተራ ስርዓት ብቻ አይደለችም! ስልጣኔም እንጅ! የራሷ ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ከፍታና ዝቅታ፣ አስተዳደርና መንግሥት ያላት ስልጣኔ ነበረች!

የዓለምን ጥንታዊና አሁናዊ ስልጣኔዎች ላይ የሚያጠኑ ምሁራኖች እንዲህ ይላሉ። The average lifespan of those surveyed was 336 years ነው ይላሉ። እንደ Daron Acemoglu and James A. Robinson ትንታኔ ደግሞ የአንድ ስልጣኔ ቆይታ 800 ዓመታት ነው።

ይህን የዓለማችንን ተሞክሮ ይዘን የወገኖቻችንን የዘወትር ትዝታና (Golden age memory) እና ናፍቆት የሆነውን የሶሎሞናውያኑን (የደሴታውያኑን፣ የኤጼውን) ሥርዓት ስንገመግመው ከ1270 ጀምሮ ዛሬ ድረስ ወደ ሰባት መቶ አርባ አመት በላይ ሆኖታል። ይህ ሥልጣኔ ሰባት መቶ አመታት ከቆየ በኋላ በይፋ ተገርስሷል። አልሞት ባይ ተጋዳይ ሆኖ፣ የናፍቆት ሩጫ እያደረገ አርባ አመታትን አሳልፏል። ይሁን እንጅ እንደ ማንኛውም የዓለማችን ሲቪላይዜሽኖች ተፈጥሯዊ የሆነውን ሞት ከመሞት ግን በፍጹም አይቀርም! ደሴቷም ላትመለስ እየሰመጠች ናት!
457 views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 20:40:04 የዲያቆናቱ ቡጭሪያና ማለስለሻ መፍትሔው
★★★// //★★★

(እኔ ስፅፈው ያልፈራሁትን አንተ ምን አሰነፈህ?ጨክነህ አንበበውማ)

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት፣ መምህራን፣ ዲያቆናትና በሥሯ የተደራጁ ቡድኖች በተለየ መልኩ የጥላቻ ቅስቀሳ፣ ትንኮሳ፣ የሽብር ድርጊት፣ ጅምላ ጭፍጨፋ፣ የፖለቲካ ውጥረት፣ ጠላት ማብዛት፣ ከመንግሥትም ከሁሉም ጋር መናከስን መጋጨትን ተያይዘውታል። የተቃጠልን ነደድን በሚል ራሳቸውንም ቤተክርስቲያኒቱንም፣ ሙስሊሙንም፣ ፕሮቴስታንቱንም፣ ኦሮሞውንም፣ ሱማሌውንም፣ ስልጤውንም ፣ መንግሥትንም ሰላም መንሳት የተለመደ ጠባያቸው ሆኖ ዘልቋል።
ይህ ለምን ሆነ? ምንስ ይሻላል? ወንድሞቻችን እንዴት ሠላም ያግኙ የሚለው አሳሳቢ ነውና እንዲህ የሚያደርጋቸውን ሥረ-ነገር ማጥናቱ ተገቢ ነው።

ምክንያት አንድ ፡- ተስፋ መቁረጥ

በስነ-ልቦና ምሁራኖች ዘንድ frustration anger aggression theory የሚባል ሃይፓተሲስ አለ። በዚህ ቲዮሪ መሰረት ከአብዛኛው ወንጀል፣ አመጽ፣ ረብሻ፣ ቁጣ፣ ሁከት፣ ሽብርተኝነት እና ተናካሽነት ጀርባ ወይም የዚህ ሁሉ መነሻና ጅምር ተስፋ መቁረጥ ነው። ተስፋ የቆረጠ አካል ይዞ ሟች ነው! ተስፋ የቆረጠ አካል እንዳበደ ውሻ ለካፊ ነው! ተስፋ የቆረጠ አካል እረፍት የለውም ይቅበዘበዛል! ይንቀዠቀዣል! ካገኘው ጋር ይጋጫል! ይላተማል! ያገኘውን ይነክሳል! ይቧጨራል!

ተስፋ የቆረጠ አካል እሪሪሪታው ብዙ ነው! ተስፋ የቆረጠ አካል መርሁ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ነው!”፣ ተስፋ የቆረጠ አካል ቡጭሪያው እንዲሁ አይደለም! ቡጭሪያው እንዳይሰምጥ ወይም ገደሉ ውሥጥ እንዳይገባ አንዲም መፈራገጡ፣ ሁለትም አንተን ይዞ ለመትረፍ የሚያደርገው ደመ-ነፍሳዊ መፈራገጡ፣ ሶስትም ጦሰኛ ሆኖ ይዞህ ሊሞት ገደል ሊገባ የሚያደርገው ደመ-አብራሪያዊ ባህሪው ነው። የቤተ-ክርስቲያኒቱ አንዳንድ ማህበራት፣ አንዳንድ ቀሳውስቶች፣ መምህራን፣ ዲያቆናቱና ህቡእ አደረጃጀቱን ወቅታዊ ተጨባጭ ይህ ነው።

ለመሆኑ ተስፋ ምን አስቆረጣቸው?

ከላይ የተጠቀሰው የጨለምተኝነት ቲዮሪ እንዲህ ይላል

Drive to Goal obstacle to a goal frustration Anger Aggression Catharsis

ግብ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ያለ አካል አንዳች ያልጠበቀው ዓይነት ወይም ሊያሸንፈው ያልቻለው እንቅፋት ሲያጋጥመው ተስፋ ይቆርጣል። ተስፋ የቆረጠ ሰው ደግሞ ይበሳጫል የተበሳጨ አካል ደግሞ ካገኘው ጋር ይጋጫል፣ ወንጀል ይሰራል፣ እብሪተኛ ይሆናል፡፡

ወገኖቻችን ግብ ነበራቸው፣ ለዚህ ግብ ሲሉ አርባ አመት ለፉ፣ ለዚህ ግብ ሲሉ ብዙ ተደራጁ፣ ለዚህ ግብ ሲሉ በ1960ዎቹ ወደ ኋላ የቀለበሷቸውን የያን ትውልድ አባል ጭምር ንሰሃ አስገብተው አተጉ፣ ለዚህ ግብ ሲሉ ከፍተኛ ሪሶርስ በጅተው ተንቀሳቀሱ፣ ለዚህ ግብ ሲሉ እጅግ አደገኛ አደረጃጀቶችንና ኤጀንቶችን በብዛት አመረቱ፣ ይህ ግብ በሴኪዩላሩ ፖለቲካዊ አመጽ መሳሪያነት ለስኬት ቀርቦ የተቀለበሰ ወይም ድንገት አቢዮቱ በሌላ የተቀማበት ግብ ነው። ይህ የወገኖቻችን ግብ ምንድን ነበር? ግባቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያንን ከተቻለ እንደ ቀድሞው በይፋ ሲሶ መንግሥት የማድረግ ግብ ነው።

የቤተ-ክርስቲያኒቱን የመንግሥት ህገ-መንግስት፣ የመንግሥት-ፍልስፍና፣ የአስተዳደር ሞራል፣ የአይዲዮሎጂ ምንጭ የማድረግ ምኞት ነው። የመንግሥትነትና የገዥነት ህጋዊነት (legtimacy) ምንጭ የማድረግ ግብ ምኞት ነው። ቤተ-ክርስቲያኒቱን የአገሪቱ ሲሶ ሀብት ባለቤት የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ፍልስፍናና የበላይ የማድረግ ምኞት ነው። ይህ ካልሆነ ቤተ-ክርስቲያኒቱንና ኦርቶዶክሱን በተለየ መልኩ እውቅና የሚሰጥ፣ ተቀዳሚ ላዕላይ የሚያደርግ፣ ባለርስትና ቀዳማይ ሌላውን መጤና ባሪያ የሚያደርግ አሰራርና ህግ መልሶ እውን እንዲሆን የማድረግ ግብ ነው። ተምኔታዊው ግብ ሲጠቃለል ደሴቷንና የአጼውን ሥርዓት ዳግም የማንበር ምኞት ነው።

ይህን ግብ እውን ለማድረግ በሴኪዩላር ስም በተደራጁ አሃዳዊና ብሄርተኛ ድርጅቶች ጀርባ ሆነው የናፈቁትን ውሃ ሊጠጡ የኢህአዴግን መውደቅ አድፍጠው ሲጠብቁ የነበሩ ነበሩ። ለዚያም እጅጉን የተጉ ነበሩ።

ይህን ግብ ለምን መረጡት? ይህን በዚህ ዘመን ተግባራዊ ሊሆን የማይችል (infeasible system) ግብ የሙጥኝ ማለታቸው አንድም የኢ/ኦ/ቤተ ክርስቲያንና ምዕምኗን በተለየ መልኩ በባለርስትነት፣ በምርጥነት፣ በቀዳማዊነት፣ በላዕላይነት፣ በህጋዊ ወራሽነት ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ዴሞግራፊያዊና በተለይም ስነ-ልቦናዊ ጥቅምን በተለየ መልኩ ለቤተክርስቲያኗና ለምዕምኖቿ ሊያስከብር የሚችል ሌላ አንዳችም የአስተዳደር ሞዴል ሊኖር ባለመቻሉ ሲሆን ሁለትም ሩቅ ጠይቆ ብዙ ለማትረፍ በሚል ነው።
ይህ ግብ እጅግ ግዙፍ እክሎች (obstacle) አጋጥመውታል።

የመጀመሪያው እክል አጼ ሚናስን ያጋጠመው ግርታ (confusion) ነው። አጼ ሚናስና ተቀዳሚዎቹ ለዘመናት “እኛ ክርስቲያኖች ምርጦቹ የእግዚአብሔር ልጆች” ሆነው ሌሎቹ ያሏቸው ደግሞ “አህዛቦች፣ አዋሚዎች፣ ፈላሻዎች” ብለው ብዙ የአይዲዮሎጂ ስንቅና ትጥቅ ይዘው ሲታገሉ እንዳልኖሩ በሚናስ ዘመን ሃይማኖትን ሳይሆን ዘርን መሰረት ያደረገ የኦሮሞ ሃይል አጋጠመው። አፄ ሚናስን ጨነቀው፣ የታጠቀው የአይዲዮሎጂ ትጥቅ ለዚህ ዓይነቱ ተገዳዳሪ ሃይል በቅጡ የዳበረ ፎርሙላ አልነበረውም። እሱ በሃይማኖት እነሱ በዘር ሆነውበት ግራ ገባው።

ዛሬም ከላይ ያለውን ግብ ለማሳካት እየተፍጨረጨሩ የነበሩትና የህወሃት-ኢህአዴግን መውዴቅ ሲጠባበቁ የነበሩት ኃይሎች ያጋጠማቸው ከሚናስ የከፋ ነው። ወዲህ በብሄርተኝነት ፖለቲካ ጥርሱን ነቅሎ የደደረ የጎለመሰ የኦሮሞ ፖለቲካ፣ ወዲያ በካፒታሊስቶቹ የዘመናችን ባለ ሄጅሞኒዎች የሚዘወር የፕሮቴስታንት ሃይማኖት። ሶስትም የነቃ ሙስሊም ትውልድ! እነዚህ ዋነኞቹ እንቅፋቶች ቢሆኑም ወግ ላለማብዛት እናሳጥረው።

እነዚህ እክሎች ወይም እንቅፋቶች ወዳጆቻችንን ተስፋ መቁረጥ ውሥጥ ከተዋቸዋል። ተስፋ የቆረጠ አካል ደግሞ እንዳበደ ውሻ ያገኘውን ይለክፋል!

ምን ተስፋ አስቆረጣቸው ?

የመንፈሳዊነት ታሪክ እጦት

መንፈሳዊነት ጉልበት ነው። መንፈሳዊነት የትዕግስትና ጽናት እናት ነው። ወገኖቻችን ድህር አጼ ይኩኖ አምላክ ላይ ከመንፈሳዊነት ተናጥበዋል! ሮሃ ላይ በመንፈሳዊነትም በቁሳዊነትም ዓለምን ያስደመመውን የዛግዌውን መንግሥት “እኛ የንግሥቲቱ የሳባ ዘሮች የሰለሞን ትውልዶች ነን የጨዋይቱም የሳራ ዘሮች ነን” ብለው በሶሎሞናዊነት ስም የመጡት ኃይሎች እንደዚያ ዘመኑ የታላቋ የሮማን ካቶሊክ ብሎች እንደነ ቴምፕላራስ፣ እንደ ጥንተ ካባላ እርሾዎቹ፣ እንደ ተከታይ ፍሪሜሰንስ ሁሉ በኢትዮጵያችን የበቀሉ ህቡእ ኃይሎች ነበሩ። የአውሮፓዎቹ መንግሥትነትን ሊወርሱ ብዙ ዳከሩ ግና የቫቲካንን ኢንኪዩዚሽን ጽዋ እየጨለጡ እንደ አውሬም ታድነው አለቁ።
464 views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 09:55:06 በአዲስ አበባ ከተማ ሙስሊሙ ላይ ያነጣጠረ የጅምላ እስር እየተካሔደ መሆኑን ከተለያዩ ቦታዎች ነዋሪዎች ለሀሩን ሚዲያ ገልጸውልናል። የህግ አካል ነን የሚሉ ሰዎች በተለያዩ መስጅዶች ተሳትፎ ያላቸውን ሙስሊሞች በመምረጥ በጅምላ የማሰርና የመሰወር ስራ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን የታሰሩ ሙስሊሞች እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው ታውቋል።
..
የእስር ዘመቻው የጅምላ የሚመስል አፈና ነው ያሉት ነዋሪዎች ከ2004 ወዲህ ሙስሊሙ ላይ በዚህ ደረጃ አፈሳ ተደርጎ እንደማያውቅ ገልፀውልናል። ሀሩን ሚዲያ ከተለያዩ አካላት ለማጣራት ባደረገው ጥረትም በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ሙስሊም ወጣቶች በተቀናጀ በሚባል መልኩ እየታሰሩ መሆኑን ለመረዳት ችሏል። የዚህ እስር አላማው ምን እንደሆነና ምክንያቱ የማይታወቅ ሲሆን የሚታሰሩ አካላትም ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ እንዳልተመሰረታባቸው ለማወቅ ተችሏል።
..
ሀሩን ሚዲያ
873 views06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 09:35:45 ስለ ዶክመንተሪው ዝርዝር ነገር ማለት አልችልም። ነገር ግን በዶክመንተሪው ጭብጥ ብዙ ሰርፕራይዝ መሆን አይገባም። እኛ ላይ ደርሶ አላየነውም እንጂ፣ ብልፅግና እየሳመ መንከስን፣ እየዳበሰ መውጋትን የተካነ ''ቡድን'' ነው። ይሄ እጣ ከደረሰባቸው ግለሰቦችና ቡድኖች መማር ይቻል ነበር፤ አሁንም አልረፈደም። ብልጽግና ረፍዶም ቢሆን ድብቅ ማንንቱን ገልጦ መምጣቱ መልካም ነው። ካሸለብንበት እንንቃ!

ከዚያ ይልቅ ነገ ከነገ ወዲያ ጠ/ሚኒስትሩ በዶክመንተሪው ጉዳይ ''እጄ የለበትም'' ብለዋል፣ እንደውም ''ስሰማ ደንግጫለሁ'' ብለዋል የሚል ማደንዘዣ መርፌ እንዳይሰጠን አሁን ባለው አሠራር የትላንቱ ዓይነት ዶክመንተሪዎች ተሰርተው ለሕዝብ የሚቀርቡበትን ሂደት ላስቀምጥላችሁ።

በኢህአዴግ/ሕወሓት ዘመን ''አኬልዳማ'' እና ''ጅሃዳዊ ሀረካት''ን መሰል ዶክመንተሪዎች በደህንንት መሥሪያ ቤቱ ስክሪፕቱ ተዘጋጅቶ፣ ከኢቴቪ ጥሩ ድምጽ ያለው ጋዜጠኛ እዛው ደህንንት መሥሪያ ቤቱ በተዘጋጀ ስቱዲዮ ድምጹ ተቀርጾ፣ ፕሮዳክሽኑም እዚያው ደህንንት መሥሪያ ቤት ተጠናቅቆ ነበር ለሥርጭት ወደ ኢቲቪ የሚላከው።

አሁን የድሮው አሠራር ተቀይሯል። አሁን ባለው አሠራር የዶክመንተሪው ጭብጥና አሠራር ጠ/ሚ አብይ በሚመሩት ብሔራዊ የደህንንት ም/ቤት ግብረ ኃይል ተወስኖ፣ የጽሑፍ ስራው ለባለሞያ ይሰጣል።

በመቀጠል ስክሪፕቱ ግምገማ ከተደረገበት በኋላ ለፕሮዳክሽን ሥራ ወደ ፋና ይላካል። ፋና የሚመረጥት ምክንያት ጠ/ሚ አብይ ፋና ከለሌሎች የመንግሥት ጣቢያዎች የተሻለ የፕሮዳክሽንና የባለሞያ አቅም አለው ብለው ስለሚያምኑ ነው። ከዚያ በፊት የሜቴክን ዶክመንተሪዎች እንዲሠራ የተሰጠው ኦቢኤን የሠራው ፕሮዳክሽን በመንግሥት ባለሥልጣናት ዘንድ ብዙም አርኪ አልነበረም፤ ፋና ግን ለባለሥልጣናቱ የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል።

ፕሮዳክሽኑ ካለቀ በኋላ ብሔራዊ የደህንንት ም/ቤት ግብረ ኃይሉ የመጨረሻውን ቅጂ ተመልክቶ፣ በሁሉም ጣቢያዎች እንዲተላለፍ ትእዛዝ በመስጠት ለኮሙኒኬሽን ቢሮ ይልከዋል። የኮሙኒኬሽን ቢሮው በታዘዘው መሠረት በሁሉም የመንግሥት ጣቢኣዎች በተመሳሳይ ሰዓት እንዲሠራጭ ትእዛዝ ያስተላልፋል። ነገሩን ለመጠቅለል ትላንት የታየው ዶክመንተሪ ጥንስሱም ፍጻሜውም የተወሰነው ጠ/ሚ አብይ በሚመሩት ብሔራዊ የደህንንት ም/ቤት ግብረ ኃይል ነው።

@Akmel Negash
856 views06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 21:52:46 መንግስት... እንደ መንግስት ሰርአት አክብሮ ስርአት ባለማስከበሩ የማንም ስርአት አልበኛ ጢባጢቤ መጫወቻ ሆነናል::
ለዚህ ችግር ተጠያቂ መንግስትና መንግስት ብቻ ነው::
1.0K views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 10:33:19
970 views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ