Get Mystery Box with random crypto!

#አስቸኳይ_መልእክት_ወለጋ! በምዕራብ ወለጋ ዞን በቶሌ ከተማ ጉትን ሰፈር በተባለው አካባቢ ከተፈጸ | መንቆረር 🇪🇹 𝓣𝓲𝓶𝓮𝓼 🇪🇹

#አስቸኳይ_መልእክት_ወለጋ!
በምዕራብ ወለጋ ዞን በቶሌ ከተማ ጉትን ሰፈር በተባለው አካባቢ ከተፈጸመው የጅምላ ግድያ ተርፈው በየጫካው የተበተነው ግማሽ ያህሉ ነዋሪ በተደረገው ጥረት በአርጆ የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በየጢሻው ገብተው እስካሁን ያልተገኙ ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በመኖራቸው፤ ጥቃት ፈጽሞ ጫካ የገባው ሐይል ተጨማሪ ጥፋት እንዳያደርስ ከፍተኛ የሆነ ሐይል ከመንግሥት በኩል ያስፈልጋል።

#በተጨማሪም ነቀምት ጀምሮ እስከ ጊምቢ መካከል ባለው አርጆ ጉደቱ፣ አርጆ አውራጃ፣ ቶሌ፣ ጆግር፣ አባሴና ወሎሰፈር፣ሜጢ፣ እሁድ ገበያ፣ እና እስከ ጊምቢ ከተማ ድረስ የምትገኙ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ።

ከነቀምት እስከ አጋምሳ የምትገኙም በጽጌ 24፣ ጃርሶ፣ ኡኬ፣ መንደር 10፣ አባሙሳ፣መ.11 ጉትን፣ መንደር9;8፣ አርቁምቢ፣ ያሶ፣ ሶጌ፣ ፊጢበቆ፣ መንደር7; 6; 5; 4 እና ዋጃ፣ ለሊ ማሪያም፣ እንዶዴ፣ ዶሮበራ፣ ሻሾበር፣ ጌድዮ፣ ቆፍቆፌ፣ ሐሮ፣ ኪረሙና አጋምሳን ጨምሮ ጃቦዶበንና በአሙሩ ወረዳ ስር የምትገኙ ሁሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ።

ከቱሉጋና፣ ጫንጮ፣ ለጋዲ፣አሊጎራ፣ጫልቲ፣ ጋሌሳ ጨሩ፣ አሩሲ፣ ለጋጎርፌ፣ ሎሚጫ፣ ጨቆርሳ፣ ጎርቴ፣ ወባጥጭ፣ ዳልጆ፣ መንደር 21፣ ቆጨራ፣ ባታ ማሪያም፣ መድሐኒያለም፣ ጉደያቢላ፣ ሐሮ ሾጤ፣ ደቢስ፣ ጃርቴ ጃርዴጋ፣ ሻምቡ፣ በፊንጨዋ ና ቱሉዋዩ(አቤደንጎሮ) ወረዳ ስር የምትገኙ ሁሉ በአስቸኳይ የፀጥታ ሐይሉ በተጠንቀቅ ይቁም።

ከባኮ ነቀምት የምትገኙ ባኮትቤ 02፣ አኖ፣ ጉባሰዮ፣ አርብ ገበያ፣ ልጎ፣ አለልቱ፣ሐሙሲት፣አራተኛ፣ መርካቶ፣ ወጤ እና በሳሲጋ እና በሲቡስሬ ወረዳ ስር የምትገኙ ሁሉ በተጠንቀቅ ሁሉም በያለበት ይዘጋጅ።

ከጊምቢ እስከ አሶሳ ዳቡስ ወንዝ ድረስ ያላችሁ ነጆ፣ ቤጊ፣ አንገር ዲዲሳና ደንቢደሎ አጠቃላይ የአማራ ሰፈሮች ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ።

#በመጨረሻም በቶሌ ከተማ እስካሁን ድረስ ስክሬናቸው በመሰብሰብ ላይ ሲሆን የተረፉት በአርጆ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እንድደርሳቸው የሚመለከተው የመንግስ አካል እና የአለም አቀፉን ማህበረሰብ #አጉልዞ ጥያቄ ጥሪውን እያቀረበ ነብሳቸውን ላጡ ወገኖቻችን ነብሳቸው በሰላም በአፀደ ገነት እንድያሳርፍልን እንመኛለን

ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ መፅናናትን እንመኛለን : ነብስ ይማር!

ከአካባቢው ሰዎች (ተሟጋቾች) በውስጥ የተላከ

አራጋው ሲሳይ