Get Mystery Box with random crypto!

የጉበትን ጤንነት ለመጠበቅ የሚጠቅሙ መንገዶች ጤናማ ክብደት ይኑርዎት ከመጠን በላይ ከፍተኛ | መርጌታ መንግስቱ የባህል መድሀኒት አዋቂ መስተፋቅር እና ሌሎች ህክምና አገልግሎት 0915854013

የጉበትን ጤንነት ለመጠበቅ የሚጠቅሙ መንገዶች

ጤናማ ክብደት ይኑርዎት

ከመጠን በላይ ከፍተኛ ውፍረት ያላቸው ሰዎች ለጉበት ላይ ስብ መከማቸት ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ። ክብደትን መቀነስ የጉበት ስብን ለመቀነስ ትልቅ ሚና ይጫወታል።

ጤናማ አመጋገብ ይከተሉ

ከፍተኛ የካሎሪ፣ የስኳር እና የቅባት ይዘት ያላቸውን ምግቦች ያስወግዱ።

አዘውትረው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ

በሳምንት ለ5 ቀናት ለ30 ደቂቃ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የጉበት ስብን በመቀነስ ጉበቶዎ ጤናማ እንዲሆን ይረዳዎታል።

ተጓዳኝ በሽታዎችን ይቆጣጠሩ

እንደ የስኳር ህመም፣ የደም ግፊት እና ከፍተኛ ኮሌስትሮል ያሉ የጤና ሁኔታዎች ለጉበት በሽታ ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው። በአመጋገብ እና በመዳኒቶች መቆጣጠር የጉበት ጉዳትን ለመከላከል ያስችላል።

አልኮል መጠቀምን ያስወግዱ ወይም ይቀንሱ

አልኮል ከመጠን በላይ መጠጣት የጉበት ህዋስ ሊጎዳ ወይም ሊያጠፋ እና ጉበትዎን ሊጎዳ ይችላል።

ማጨስ ያቁሙ

ማጨስ ከጉበት ካንሰር ጋር የተያያዘ ሲሆን አንዳንድ መድሃኒቶች በጉበት ላይ የሚያደርሱትን መርዛማ ተጽእኖ ሊያሳድግ ይችላል።

ጥንቃቄ ከጎደለው የግብረ ሥጋ ግኑኝነት ይቆጠቡ

ከብዙ አጋሮች ጋር ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ለሄፐታይተስ ቢ እና ለሄፐታይተስ ሲ የመጋለጥ እድልን ይጨምራል።

መዳኒት ከመውሰድዎ በፊት ባለሙያ ያማክሩ

መድሃኒቶችን በተሳሳተ መንገድ ሲወስዱ ወይም ከመጠን በላይ በመውሰድ ጉበትዎን ሊጎዱ ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ ከስር በተቀመጠው ስ.ቁ በስራ ሰዓት ይደውሉልን።
አድራሻ - ሽናሻ ቤንሻንጉል ጉምዝ
ስ. ቁ 0913255901
በኢሞ 0913255901
በዋትሳብ -0915854013
በቴሌግራም https://t.me/Mngistiu
የቴልግራም ቻናል https://t.me/mengistut
የቴሌግራም ግሩፕ https://t.me/Mengistuabebe
https://t.me/Mengistuabebez