Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን ለዛሬ ትንሽ መረጃ ስለቡዳ እነሆ ቡዳ •••• ቡዳ ማለት በዓይኑ በማየት ብቻ | መርጌታ መንግስቱ የባህል መድሀኒት አዋቂ መስተፋቅር እና ሌሎች ህክምና አገልግሎት 0915854013

ሰላም ለእናንተ ይሁን ለዛሬ ትንሽ መረጃ ስለቡዳ እነሆ
ቡዳ
••••
ቡዳ ማለት በዓይኑ በማየት ብቻ ሰዎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ
ይችላል ተብሎ የሚታመንበት
መንፈስ ወይንም ሰው ነው። ይሄ አይነት እምነት በኢትዮጵያ
ብቻ የሚገኝ ሲሆን ለአነሳሱም ከ ዛር መንፈስ ጋር
ተመሳሳይ አፈ-ታሪክ አለው።
የቡዳ አፈ-ታሪክ
የቡዳን አመጣጥ የሰውን ልጅ አጥኝው (አንትሮፖሎጅስት)
ሬምኒክ መዝግቦት ይገኛል። እንደ አፈ ታሪኩ አገላለጽ፣
አዳም እና ሔዋን ከገነት ከተባረሩ በኋላ 30 ልጆች
የነበሯቸው ሲሆን አንድ ቀን እግዚአብሔር ሔዋን ልጆቿን
እንድታአየው ጠየቃት። እርሷ ግን በመፍራት 15ቶቹን እና
ቆንጆ የሆኑትን ልጆቿን በዋሻ ደብቃ 15ቱን ብቻ
ለእግዚአብሔር አሳዩ። እግዚአብሔርም በውሸቷና
በአለመታዘዟ በማዘን ዋሻው ውስጥ ያሉት 15ቹ ልጆች
የተረገሙና መጥፎ እንዲሆኑ ተራገመ። አንድ አንዶቹ ልጆች
ግን እግዚአብሔርን ይቅርታ ጠየቁ። አምላክም በመራራት
ገሚሶቹን ቀበሮ፣ ጥንቸል ወዘተ አደረጋቸው። ገሚሶቹን
ደግሞ ሰው እንደሆኑ ትቶ ግን የሰይጣን መልዕክተኛ
እንደሆኑ እንዲቀጥሉ አደረገ። እኒህ እንግዲህ የቡዳ ሰዎች
የቀደሙ ወላጆች ናቸው። ሬምኒክ የመዘገበው አፈ ታሪክ
ሰፊ እምነት አይደለምና አብዛኞቹ ሰምተውት አያውቁም።
በአንዳንድ ሥፍራ ብቻ የሚታመን ሊሆን ይችላል።
በመጽሐፍ ቅዱስ አስተያየት ስለዚህ ትምህርት አንዳችም
አይገኝም። እንኳን «ዛር» ወይም «ቡዳ» የሚሉት ቃላት
በመጽሐፍ ቅዱስ በፍጹም አይገኙም። ሆኖም የመጽሐፍ
ቅዱስ ትምህርት ይህን ትንሽ ይመስላል። በመጽሐፈ ኩፋሌ
ና ሌሎች መጻሕፍት መሠረት፣ የአዳምና የሕይዋን ልጅ
ቃየል ወንድሙን አቤልን ከገደለው በኋለ ከእኅቱ ጋራ
ተባረረ። የቃየል ልጆች በዘመናት ላይ እጅግ በደለኞች ሆኑ።
የአዳምና ሕይዋን ሌላ ልጅ ሴት ግን ጻድቃን ልጆች ወለደ፤
የእግዚአብሔርም ልጆች ተባሉ። ሴት እራሱ ከሞተ በኋላ
ልጆቹ አመጸኞች ሆኑ፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ንቀው ወደ
ቃየል ልጆች ወረዱና ከነርሱ ጋር ተደባለቁ፤ አብረው ክፉ
ልጆች (ናፊል) ወለዱ። እግዚአብሔር ማየ አይኅ ያመጣው
ስለዚህ ነው ይባላል። ከሰው ልጆች
ኖህ ና ቤተሠቡ ብቻ አመለጡ፤ ዳሩ ግን በጥፋት ውኃው
የጠፉት ክፉ ሰዎች አስማተኞች ስለ ነበሩ፣ የኖህን ልጆች
በፈተና ለማታለል እስከ ፍርድ ቀን ድረስ አጋንንት ሆነው
እንዲቆዩ እግዚአብሔርን ለመኑት። እግዚአብሔርም
በምኅረቱ እንግዲህ 10 ከመቶ (አንድ አሥረኛ) ያለ
ሰውነቶች ክፉ መናፍስት ብቻ ሆነው የሚሰሙዋቸውን
ሰነፎች ለማታለል እስከ ዕለተ ደይን ድረስ እንዲቆዩ
ፈቀዳቸው። (ኩፋሌ 10፡3-7)
በቡዳ መበላት እና ለዚህ በሽታ መድሃኒት ነው ተብሎ
የሚሰራበት ዘዴ
አንድ ሰው በፈራ ጊዜ፣ በደነገጠ ጊዜ በቡዳ የመበላት
ዕድሉ ከፍተኛ ሆነ ተብሎ በዚሁ ነገር በሚያምኑ ሰዎች
ይገለጻል። ቡዳ በሶስት አይነት መንገድ ሰውን ይበላል
ተብሎ ይታመናል፣ ይሄውም ወደ ጅብነት በመቀየር፣
የአትክል ስር በመጠመዘዝ እና በ ቡዳ ዓይን በመመልከት
ናቸው።
በዚሁ ባህል መሰረት አንድ ሰው በቡዳ ሲበላ በ4 አይነት
መንገድ መድሃኒት ይፈለግለታል። አንደኛው ደብተራዎች
ሲጸልዩለትና በጸበል ውሃ ሲረጩት ነው። ሁለተኛው ወደ
ቃልቻ ቤት በመሄድ የቡዳውን መንፈስ በ ዛር መንፈስ
በመተካት ነው። ሦስተኛው የኩበት ጭስ በማጨስ ሲሆን።
አራተኛው ደግሞ በይውን ቡዳ ይዞ በማምጣት የጋለ
መጥረቢያ ላይ ምራቁን እንዲተፋ በማድረግ ናቸው።
ለበለጠ መረጃ ከስር በተቀመጠው ስ.ቁ በስራ ሰዓት ይደውሉልን።
አድራሻ - ሽናሻ ቤንሻንጉል ጉምዝ
ስ. ቁ 0915854013
በኢሞ 0913255901
በዋትሳብ -0915854013
በቴሌግራም https://t.me/Mngistiu
የቴልግራም ቻናል https://t.me/mengistut
የቴሌግራም ግሩፕ https://t.me/Mengistuabebe