Get Mystery Box with random crypto!

ወደእኔብረሪ በርግብ ክንፎችሽ ከአውሬው ስትሸሽ፣ በጸዳል እግሮችሽ ስትንከራተቺ በበረሃዉ ጉያ | መንፈሳዊ ግጥሞች ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

ወደእኔብረሪ
በርግብ ክንፎችሽ ከአውሬው ስትሸሽ፣
በጸዳል እግሮችሽ ስትንከራተቺ
በበረሃዉ ጉያ ስትመላለሽ
ከአህያይቱ ጀርባ ጫማ ተሸክሜ
ምነው በነበርኩኝ እኔ እንደ ሰሎሜ።
ከሄሮድስ ዱላ ከሳለው ጋሻ ጦር
ፈጥነሽ እንደበረርሽ ልጅሽን ለመሰወር
እኔም እንድሰደድ ከኃጢአቴ መንደር
ለጽድቅ እንድፋጠን በሰማይ እንድበር
ደግፊኝ እመ አምላክ ክንፌ እንዳይ ሰበር።
የቀላያት ጌታ ውኃ እንደተጠማ
በነፋስ የሚበርርበ ደመናው ማማ
ውኃ ስትለምኚ ጫማ እንደተቀማ
እኔን ድርቅ ያርገኝ ከኃጢአት ልጠማ
ደረቄን እንዳልቀር ከፍሬው አውድማ።
ምድርንም ያጸና ሰማይን የታታ
ግሩም እምግሩማን ያኀያላንጌታ
ለሰው ፍቅር ብሎ ብዙ ሲንገላታ
በዉኃ እንዳጠብሽው ኃይሉ እንዲበረታ
በእንባሽ እጠቢችኝ ኃጢአቴ በርትቶ የተረታሁ ለታ።
ጸሐይንያዘልሽው ደመና መፍጠኒት
የወርቅ ሐመልማል ርግብየ ኅሪት
አክናፍኪ መስቀል የሕይወት መሠረት
ሄሮድስ ሳይውጠኝ ሳልቀሰፍ በሞት፤ወደ እኔ ብረሪ አዝለሽልኝ ምሕረት።
የግብጽን በረሃ የጎበኘሻቸው
አድባረ አግአዚትን ዞረሽ ያየሻቸው
የሕይወትን ውኃ ያዘነብሽላቸው
ሐሩሩ ሕይወቴን ፍጹሙን በረሀ
ታስትይዮ ስቴ እሴፎ አሜሃ።
ነውር የሌለብሽ መልካም ጸጌረዳ
በመንከራተትሽ ውስተ ምድረበዳ
ሸክም ቀለለልን ከፈልሽልን እዳ
በምጽአቱ ጌዜ ፍቁርሽ እንግዳ
ቅርጫፍሽ ልሁን አይብላኝ አንጋዳ።
++++
መጋቤ ብሉይ ወ ሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ