Get Mystery Box with random crypto!

እመቤታችንን ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ ትባላለች። ይህም፡- 'ንጽሕት' ስንል፡- ሌሎች ሰ | መንፈሳዊ ትምህርት ዘኦርቶዶክስ

እመቤታችንን ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ ትባላለች። ይህም፡-

"ንጽሕት" ስንል፡-
ሌሎች ሰዎች (ቅዱሳን) ቢነጹ ከገቢር፣ ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም፡፡ እርሷ ግን ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከኃልዮ ንጽሕት ናት፡፡ "ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ" ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል፡፡ (ተአምረ ማርያም)

"ጽንዕት" ስንል:-
ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በኋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ ጊዜ ጸኒስ ድኅረ ጸኒስ ቅድመ ወሊድ ጊዜ ወሊድ ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና:: "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት ቅዱስ ያሬድ "ወትረ ድንግል ማርያም" ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ፡፡ (መጽሐፈ ቅዳሴ)

"ክብርት" ስንል፡-
ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው እመቤታችንን ግን የምናከብራት "የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና፡፡

"ልዩ" ስንል፡-
ከእርሷ በቀር እናት ሆና ድንግል እመቤት ሆና አገልጋይ የሆነች በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና፡፡

በዚህም እመቤታችንን ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ እንላታለን፡፡
@menefesawinet
@menefesawinet
@menefesawinet