Get Mystery Box with random crypto!

​​ ስህተቴ         ክፍል ሁለት (2) ከካፌዉ እንደወጣን ቦርሳዋን ይዤላት እያወራን | ❤️ ከምርጦች ማህደር

​​ ስህተቴ
        ክፍል ሁለት (2)

ከካፌዉ እንደወጣን ቦርሳዋን ይዤላት እያወራንና በየመሀሉ እየዘፈነችልኝ ወደ ቤቷ ሸኘኋት። ከሷ ጋር ስጨርስ ሚኪ ጋር ደወልኩለት። ፑል ቤት እየተጫወተ እየጠበቀኝ ነበር። ተገናኝተን ወደ እማዬ ምግብ ቤት ሄድን። እማዬ ምግብ ካቀረበችልን በኋላ "ከኛ ቤት ጎን የተሰራዉ ትልቁ ቤት እኮ ተሸጠ። ዛሬ ሰዎቹ ገቡበት።" አለችን።
እኔና ሚኪ ትምህርት በመሄዳችን እቃ አዉርደን የምናገኘዉን ብር ስላጣን ተበሳጨን። ለነገሩ ጎረቤት መቦጨቅ ደሞ አይነፋም። እማዬ ለሌላ ተስተናጋጅ ምግብ እያቀረበች "ደሞ ጥሩ ሰዎች ይመስላሉ። ሰዉየዉ ቁልፉን እንድሰጣቸዉ ደዉለዉ ሄጄ አይቻቸዉ ነበር።" አለች። እማዬ ቤቱ እስኪሸጥ ደላላ ሲመጣ እንድታሳይ አደራ ተብላ ቁልፉ እሷ ጋር ነበር።
.
ማታዉን እናቴ ቡና አፍልታ አዲሶቹ ጎረቤቶቻችን ጋር ሄድን። እኔ እንኳ ጀበናዉን እና ሽንብራዉን አድርሼላት ለመዉጣትና ከፌቪ ጋር ፌስቡክ ላይ ለመጀናጀን አስቤ ነበር። ሰዎቹ ጋር ስናንኳኳ አንድ ጠይም የሆነች፣ ረዥም ቀሚስ የለበሰች፣ ሂጃብ የጠመጠመችና ጥርሷ በብሬስ የታሰረ ወዛም ልጅ በሩን ከፈተችልን። እቃ አድርሶ የመመለሱን ሀሳብ ሰረዝኩት። ይህቺን የመሰለች ልጅ ያለችበት ቤት መቀመጡ ራሱ ደስ ይላል። እኔ ሴት ላይ ችግር አለብኝ። ያየሁት ሁሉ ያምረኛል። ለነገሩ ይህቺ እንኳ ትገባኛለች። የሰፈሬን ሴትማ ማንንም አላስበላም። እማዬ ሴቶቹ ጋር ገባች። እኔን ልጅቷ ወደ ሳሎን ወሰደችኝ።
ሳሎን ስገባ ምግብ ቀርቦ ነበር። አንድ ሸምገል ያሉ ሰዉዬ ስገምት አባቷ ይመስሉኛል "አምሪያ እጅ መታጠቢያዉን አሳይዉ ይቀላቀለን!" አሉ። አሀ ስሟ አምሪያ ነዉ ማለት ነዉ አልኩ በልቤ። ምናለ ስልኳንም በዛዉ ቢጠሩት። ፈገግ ብላ መታጠቢያ ቤት ወሰደችኝ። እየታጠብኩ "ስንተኛ ክፍል ነሽ?" አልኳት። ድፍረቴ ሳይገርማት አይቀርም። "ከወር በኋላ ኢንትራንስ እፈተናለሁ። አስራሁለተኛ ክፍል ነኝ።" አለችኝ በትህትና። ስለራሴ ትንሽ ነገርኳትና የአባቷን ስም ጠየቅኳት። "ራህመቶ" አለችኝ ፈገግ ብላ። ልጅቷ ፈገግታ ታበዛለች።  እኔ የአባቷን ስም የጠየቅኳት አባቷን መተዋወቅ ፈልጌ ሳ ይሆን ፌስቡክ ላይ ልፈልጋት ስላሰብኩ ነዉ።
ታጥቤ እየተመለስኩ ቆም አልኩና "ወንድም ምናምን የለሽም?" አልኳት። "ሶስት አሉኝ። ሳሎን ያሉት ሁለቱ ወንድሞቼ ናቸዉ። አንደኛዉ ልጁ ታማ ሄዷል። ሶስቱም አግብተዉ ወጥተዋል።" አለችኝ። የቤቱ ታናሽ መሆኗ ነዉ እንግዲህ! ለዛሬ ከበቂ በላይ መረጃ እንደሰበሰብኩ አሰብኩ። ነገ ለነሚኪ ይተረካል። ሳሎን ገብቼ በልተን ከጨረስን በኋላ አባቷ የጥያቄ መዓት አወረዱብኝ። ብዙዉ የሀይማኖት ትምህርት ለምን እንዳልተማርኩ ምናምን ነዉ። ሲጠይቁኝ ስወዛገብ አለመማሬ ገባቸዉ መሰለኝ። ሰዉየዉ ሀይማኖተኛ ነገር ናቸዉ።
ፌቪ አስሬ ትደዉላለች። ስልኬን ዘጋሁት። ደሞ በመጀመሪያ ቀን ልጠቆር እንዴ?
.
ሰዉየዉ አንድ በአንድ ሳሎን የነበሩትን ልጆች ካስተዋወቁኝ በኋላ አምሪያን ጠርተዉ ሰፈሩን እንዳላምዳት አደራ አሉኝ። ተመስገን! እንኳን አደራ ተብዬ ወትሮዉንም እንዲሁ ነኝ። አንገቴን ስደፋ ምንም የማላዉቅ መስያቸዋለሁ።
.
ከነአምሪያ ቤት እንደወጣሁ ፌቨን ጋር ደወልኩ። ፌቪ በጣም ተጨንቃ ነበር። ሁሌም ከሶስት ሰዓት በኋላ ስለምናወራ ስልክ አላነሳ ስላት ደንግጣለች። ድንጋጤዋ ሲበርድላት "አንድ አንድ እንዝፈን!" አለችኝ። ፌቪ ስዘፍን ድምፄን ትወደዋለች። አንድ አንድ ተዘፋፍነን ስልኩን ዘጋሁት።
ቤት ከገባሁ በኋላ አምሪያን ፌስቡክ ላይ አሰስኳት። መጨረሻ ላይ አንድ ፎቶ የሌለዉ አካዉንት የሷ ይሆናል ብዬ ገመትኩና ሪኳየስት ላኩኝ። ወዲያዉ ተቀበለችኝ። ትንሽ እንዳወራኋት እሷ አለመሆኗን አወቅኩ። ተበሳጨሁ።
.
ልተኛ ስል ሚኪ ደወለ "ኧ ሚኪ" አልኩ ስልኩን አንስቼ
"ሀቢቤ ያበደ እቅድ አለ ቸከሶቹን በተመለከተ! አሁን አያቴ ሰዉ ሲመክር ሰምቼ ነዉ። ጠዋት በሰፊዉ እተነትንልሀለሁ።" አለኝ። ሚኪ የሌለ ጓጉቷል። እኔም እስኪ ይንጋና ለነሚኪ ስለ አምሪያ ልተርተርላቸዉ።

share your channal
    
#Share