Get Mystery Box with random crypto!

#RIP አሜሪካኖች #የማታዋ_አበባ ይሏታል ለሚሊዮን ሰዎች ጥንካሬና ብርታት ሆናለች። በካንስር በ | መልካምነት ለራስ ነው!!!🌹🌹🌹

#RIP
አሜሪካኖች #የማታዋ_አበባ ይሏታል
ለሚሊዮን ሰዎች ጥንካሬና ብርታት ሆናለች።
በካንስር በሽታ ምክንያት ሰሞኑን በተወለደች በ31 ዓመቷ ከዚህ ዓለም ሁላችንም ወደ ማንቀርበትና ሰላማዊ እረፍትን ወደምናገኝበት ቦታ ኤዳለች።

ይህች እንስት ትክክለኛ ስሟ #ጄን ይባላል። ከ8 ወር በፊት AGT (America Got Talent) ላይ ቀርባ ስለ ራሷ ህይወት it’s ok እያለች በዘፈን መግለፅዋን እናስታውሳለን። ያ ዘፈንዋ ያ ዜማ በሚሊዮን ህዝብ ልብ ውስጥ ታተመ። ብዙሃን ሳያንገራግር በአንድ ልብ ወደዳት። ቆመውም አጨበጨቡላት።

ዳኛው ሳይመን ሳይቀር የወርቃማው ደውል ሰጣትና ወደ ቀጣዩ ዙር በቀጥታ አለፈች ነገር ግን በዶክተሮች:
በቅርቡ እንደምትሞትና የመዳን እድሏም ከ 100% 2% እንደሆነ የተነገራት እቺ ጠንካራ ሴት
ባላት ትንሽ ጊዜ ተሰፋ ሳትቆርጥ ለሰው ልጆች ይጠቅማል ያለችውን መልካም ነገር ማስተማር ጀመረች።

በምድር ላይ እያሉ ሰዎች ለሰዎች ጥሩ ነገር መስራትን እንዳለባቸው ደጋግማ ተናገረች።
በየቀኑ ህመሟ እየጠናባት ቢሄድም በተለያያ ቦታ በመገኘት ለሰው ልጅ ይጠቅማል የምትለውን በሙሉ ማስተማሯን ተያያዘች ነገር ግን ጉልበትዋ እየከዳት ሲመጣ ከውድድር ልትሰናበት ተገደደች።

ዶክተሮቹ በቃ :-
ነገ ትሞቻለሽ ዛሬ ትሞቻለሽ እያሏት እሷ ግን በፈጣሪ እረዳትነት በህይወት የምትቆይበት 8 ወሩ ተጨመረላት።
ነገር ግን ሰሞኑን ሳንባዋና ጉበቷ መስራት አቆሙ።
ሰውነቷ መንቀሳቀስ አቃታቸው። በስተመጨረሻም እስትንፋስዋ ከዳት.....።

It’s Ok
#RIP
Nan Pictures