Get Mystery Box with random crypto!

.”ሆድ ብሶኝ ነው ጨንቆኝ ነው ርቦኝ ነው አትቀየመኝ ሲሳይ ወዳጄ፤ የመጨረሻ ወዳጄ” ባሉት፤ የበሬ | መልካምነት ለራስ ነው!!!🌹🌹🌹

.”ሆድ ብሶኝ ነው ጨንቆኝ ነው ርቦኝ ነው አትቀየመኝ ሲሳይ ወዳጄ፤ የመጨረሻ ወዳጄ” ባሉት፤ የበሬ ቋንቋ ባወቁና የልባቸውን በነገሩት።» ይለናል።

በሬና ላም ለአንድ የገበሬ ቤተሰብ የቤተሰቡ አካላት ናቸው፤ ስም ወጥቶላቸው፣ አንክብካቤ ሳይጓደልባቸው ይኖራሉ። ስጋቸው በዚያ ቤተሰብ አባል አይበላም። ያ በሬ ተሽጦ ሌላ ይገዛል ወይ ደግሞ ሌላ ይቀየርበታል እንጂ ፈጽሞ እርሱ አይታረድም። ችግር፣ ረሀብ ግን ይህንን ታሪክ ሲቀይረው ጋሽ ስብሐት በኛው ቋንቋ ይነግረናል። ምናልባት አንድ መርከብ ተገልብጦ በላዩ ላይ ያሉት ሰዎች ደካማውን ሰውዬ በሉት የሚል ዜና ሰምተን ይሆናል። ጋሽ ስብሐት ይሄንን ለአንድ ገበሬ ከዚያ የከፋ ነገር እንዳለ በኛው ሀገር አውድ ያሳየናል። «የማበላቸውን ከልከልለህ ልጆች የሰጠኸኝ ምነው?» እያሉ ፈጣሪን የሚሞግቱትን አቶ በርሱፈቃድን ያሳየናል ጋሽ ስብሐት።

«አረድኩት፤ ገፈፍኩት፤ ብልቱን አወጣሁት። ጠብሰን ቀቅለን በላነው ሲሳይን የመጨረሻ ወዳጃችንን። ወጥ እንዳይሆን እንጀራ የለን፤ ቋንጣ እንዳይሆን ቶሎ ጨረስነው። በላሁት ሲሳይ ዘመዴን። ለሆድ ለሰይጣን ሰዋሁት። ታዲያ ይሁዳ ከዳተኛ ነው ይላሉ። የኔን ታሪክ ያላወቁ። ይሁዳ እንኳን ተጸጸተ ተሰቀለ ዕዳውን ከፈለ። እኔ ግን! እኔ ግን! እኔ ግን!»

* * *

ከዚህ በታች ያለውን ምስክርነት ስለአጎቷ ስለ ጋሽ ስብሃት የፃፈችው Roman Tewolde ነች። ከበርካታ ዓመታት በፊት ስለርሱ በፃፍኩት ጽሁፍ ሥር በኮሜንት መልክ የፃፈችው ነበር፦

«Meet ETV በእንግሊዘኛ ባደረገው ኢንተርቪው (Youtube ላይ አለ) «መፃፍ ላንተ ቀላል ነው ወይ?» ብሎ ሲጠይቀው «ፁሁፍ ጥበብ ነው፣ እንደማንኛውም ጥበብ መታነጽ አለበት [. . .] አዎን ቀላል ነው፣ እንደማወራው ነው የምጽፈው። ያኔ እና አሁን አንድ አይነት ፀሃፊ አይደለሁም" ሲል መልሷል።

ይህን ሲል ለኔ እንደሚታየኝ እንደወሬ መፃፍ ማለት ሳይሆን፣ ሃሳብን ለንግግር በሚጠቀምበት ቋንቋ መፃፍ ማለቱ ይመስለኛል። አነጋገሩን በጣም ሳያከብድ፣ ሳያሸበረቀርቀው መፃፍ ማለት ይመስለኛል። ለዚህም ይመስለኛል ፅሁፎቹ እየጣሙን የምናነባቸው (ወሬ አይጠላም መቸም)። እንደዛም ሆኖ ግን ዝም ብሎ ወሬ ማብዛት እና የተንዛዛ ቀደዳ መቅደድ ማለት አይመስለኝም። ሃሳቦቹን በስነስርዓቱ ቅደም ተከል አስይዞ፣ በቅርፅና ይዘትም ማነፅና መፃፉ ነው የሚታየኝ።

እናማ እንደዚህ አይነት አፃፃፉ ውስጥ ልክ ለወሬ የምንጠቀምባቸውን ቃላት እና አባባሎች ይጠቀማል፣ "ሙቀጫ"ን "ሙቀጫ" ብሎ እንደመጥራት። ይህ በኔ አስተያየት ብልግና አይደለም - እንቅጩን መናገር/መፃፍ እንጂ።

መልክዓ ስብሃት ላይ ከትችት አልፎ ወደ ስድብ ያደላ ወቀሳ ተሰንዝሮበታል። አንዱም የተወቀሰበት ነገር ስድስት ኪሎ ሃውልት ላይ ሽንታችንን ሸናን ብሎ ሌቱም አይነጋልኝም ላይ የፃፈውን ነገር አስመልክቶ ነው። ይህም አገሩን እንደማይወድ፣ ለአገሩም ሆነ ለአድዋ ድል ምንም አክብሮት እንደሌለው ተደርጎ ቀርቧል።

ሌቱም አይነጋልኝም ላይ የተፃፈው "ኢትዮጵያውያን ፋሺሲዝንም ሳይሆን ጣልያንን ጠላት አደረጉት" ነው የሚለው። እናማ በዚህ አስተሳሰብ ለማሾፍ ያህል ይመስለኛል የሃውልቱ ነገር የተፃፈው።

ሁሉም ጣልያናዊ ፋሽት አይደለም። ጣልያን ሁላ ፋሽት ነው የሚለውን በሕብረተሰባችን አስተሳሰብ ውስጥ የነበረውን አመለካከት ለማሳየት ብሎም የፃፈው ነው የሚመስለኝ።

አገሩን የማይወድ ቢሆን ኖሮ ፈረንሳይም ሆነ አሜሪካ በነበረበት ግዜ እዛው መቅረት ይችል ነበር። በሕይወቱ በጣም ፈትኖታል ብዬ የማስበው ነገርም የአገር ፍቅሩ ይመስለኛል። የደርግ አብዮት ሲፈነዳ የሚወዳት ሚስቱና ልጁ አገር ለቀው መሄድ በነበረባቸው ግዜ እንኳን አብሯቸው መሄድ አልቻለም።

አዳም ረታ "አገሮች ግን ልጆቻቸውን ከፍቅር መለያያ ጥበብ አላቸው" ብሎ በይወስዳል መንገድ የፃፈው እውነታ እንግዲህ ይሄው ነው!

ስብሃት የራሱ አፃፃፍ ዘይቤ መፍጠር የቻለ ፀሃፊ ነው። አይነኬ የሚመስለን የተከበረውን የኢትዮጵያ ስነጽሁፍ በአሁኑ ግዜ ሁላችንም እንዳመጣልን እንድንሞነጭር ድፍረቱን ሰጥኖል ብዬም አምናለሁ። በዚህ ድፍረት ውስጥ ነው ደግሞ ሌሎችም የአፃፃፍ ዘይቤዎች እየተፈጠሩ ጥበቡ የበለጠ እየታነፀና እየበለፀገ የሚጓዘው ብዬም አምናለሁ።

ስለ አይነኬ ጉዳዮችም በድረፍት ፅፏል። ይህንንም ድፍረት የሚወስዱ ፀሃፊዎች አሉን/እየተፈጠሩም ነው።

የማሕበረሰብን አስተያየት እና አመለካከት የሚከፋፍልም ፀሃፊም ሰውም (ባሕሪያቱ ማለቴ ነው) ነው። የዚህ ጉዳት ምን እንደሆነም አይታየኝም። የተለያዩ አስተያየትና አመለካከቶች እየተፋጩና እየተጋጩ ነው ሌሎች አዳዲስ ሃሳቦችና አመለካከቶችን የሚፈጥረውና።»
* * *

ጋሽ ስብሃት የዛሬ 10 ዓመት በዛሬዋ ዕልተ ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።

ነፍሱ በሰላም ትረፍ!