Get Mystery Box with random crypto!

አምስት(5) ነገሮች ከማንም ጋር እንዳትጋሩ አልበርት አንስታይን ቲዮሮቲካል ፊዚክስ 1. የስኬታ | MEGA Et 💬

አምስት(5) ነገሮች ከማንም ጋር እንዳትጋሩ

አልበርት አንስታይን
ቲዮሮቲካል ፊዚክስ

1. የስኬታችሁን ሚስጥር...

ለማንኛውም ሰው የስኬት ሚስጥር ብትነግሯቸው... ሰዎች እናንተ እንዳደረጋችሁት ለማድረግ ይጥራሉ ግን ደግሞ ከወደቁ... እናንተን ተጠያቂ ያደርጋሉ እውነቱን ባለመናገራችሁ። ስለዚህ ለማንም የስኬታችሁን ሚስጥር አትንገሩ።

2. ችግሮቻችሁን ለማንም እንዳትናገሩ
ችግሮቻችንን ለሌሎች ማካፈል የተወሰነ ይቀለናል እና ሸክማችን ይቀንሳል ግን ችግሩ ከመፈታት ይልቅ ይጨምራል። እንደሁም ሀቁ... 70% ሰዎች ስለእናንተ ችግር መስማት ያስደስታቸዋል... 10% በመቶ ብቻ ናቸው ከምር የሚያሳስባቸው። ችግሮቻችንን ከመናገራችን በፊት በደንብ እናስብበት።

3. ህልማችሁን ለማንም እንዳትናገሩ:- ህልማችሁን እና ግባችሁን ካስቀመጣችሁ በኋላ... ምርጡ መንገድ ወደ ራስ ጠበቅ አድርጎ መያዝ ነው። ለሌሎች ህልማችንን መናገር ሊያዘናጋን፥  በሌሎች ጉዳዮች እንድንያዝ እና ዓላማችንን ሊያስት ይችላል። ሁልጊዜም ከሌሎች ሰዎች ተመሳሳይ ምክርና አማራጮች አትሰሙም ምክንያቱም ሁሉም ሰው የራሱ የዕይታ መስኮት ስላለው።

4. ምን ያህል እንደምታገኙ ለማንም እንዳትናገሩ:- የእናንተን ገቢ ሌሎች በፍፁም ሊያውቅት የማይገባ ነገር ነው።

5. የቤተሰብ ችግሮችን ለሌሎች በፍፁም እንዳትነግሩ
ችግር የሌለበት ቤተሰብ የለም... አንዳንዱ ትልቅ ነው ያለበት... አንዳንዱ ደግሞ ትንሽ ግን ከእንግዳ ሰው ጋር አሳብን መለዋወጥ በፍፁም ለችግሩ መፍትሄ አይሆንም።
እናንተ ማድረግ ያለባችሁ ከቤተሰብቻችሁ ጋር በችግሩ ዙሪያ ማውራት ነው። እነዚህ ችግሮች ለሌሎች አካላት መንገር ማባባስ ብቻ ነው ውጤቱ

@changeitwow