Get Mystery Box with random crypto!

በአሜሪካ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ስርጭት መባባሱን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ *** በአሜሪ | Medicine Daily

በአሜሪካ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ስርጭት መባባሱን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ
***
በአሜሪካ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ የአገሪቱ መንግሥት በሽታው የኅብረተሰብ የጤና ስጋት ነው ሲል አወጀ።

አሜሪካ እስከ ትናንትና ብቻ 7ሺህ የሚጠጋ ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ መያዛቸውን ማረጋገጧ የተነገረ ሲሆን ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው 25 ሺህ 800 ሰዎች የ25 በመቶውን ድርሻ ይይዛል ተብሏል፡፡

መንግሥት በሽታው የኅብረተሰብ ጤና ስጋት ነው ብሎ ማወጁ፤ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የክትባት ስርጭት እንዲስፋፋ፣ ሕክምና እና የፌደራል መንግሥት ሃብት እንዲጨምር ያደርጋል።

ይህ የአሜሪካ መንግሥት ውሳኔ የተሰማው የዓለም ጤና ድርጅት ከሁለት ሳምንት በፊት በሽታው የዓለም ሕዝብ የጤና ስጋት ነው ብሎ ካወጀ በኋላ ነው።

@medicinedaily
@medicinedaily
@medicinedaily