Get Mystery Box with random crypto!

#Monkeypox ጎረቤታችን ሱዳን በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው ማግኘቷን አስታወቀች። የሀገሪቱ | Medicine Daily

#Monkeypox

ጎረቤታችን ሱዳን በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው ማግኘቷን አስታወቀች።

የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር በምዕራብ ዳርፉር የዝንጀሮ ፈንጣጣ ያለበት ሰው ማግኘቱን አሳውቋል።

የዝንጀሮ ፈንጣጣው በብሔራዊ የህዝብ ጤና ቤተሙከራ በተካሄደ ምርመራ በአንድ የ 16 ዓመት ተማሪ ላይ ሀሙስ ዕለት መገኘቱ ተገልጿል።

ወረርሽኙ ከአንድ ሰው ውጭ በሌሎች ላይ አለመገኘቱን ሀገሪቱ አሳውቃለች።

ወረርሽኙ አለባቸው ተብለው የተጠረጠሩት 38 ሰዎች ቢሆኑም በሽታው የተገኘው ግን በአንድ ሰው ላይ ብቻ ነው ተብሏል።

የዳርፉር ግዛትና የሱዳን የጤና ሚኒስቴር ጉዳዩን እየተከታተሉት እንደሆነ ገልጸዋል።

መረጃውን የሱዳን ዜና አገልግሎት/ አል ዓይን ኒውስ ነው።

ይቀላቀሉን

@medicinedaily