Get Mystery Box with random crypto!

#በወሩ_የመጀመሪያ_ቀን_ልባርካችሁ። በጌታ በኢየሱስ ስም ልባርካችሁ፤ እናንተም ሌሎችንም ባርኩ፤ | የእግዚአብሔር ምኩራብ ቤተክርስቲያን/ SYNAGOGUE OF GOD CHURCH/ ⭐ ሲኤምሲ አጥቢያ ⭐

#በወሩ_የመጀመሪያ_ቀን_ልባርካችሁ።
በጌታ በኢየሱስ ስም ልባርካችሁ፤ እናንተም ሌሎችንም ባርኩ፤ ሚያዚያ 01/08/2015ዓ.ም።

አሜን ባላችሁበት አፍ፥ ባመናችሁበት እምነት ይህ የበረከት ቃል ይፈፀምባችሁ።

እመርቃችኋለሁ እንድትበዙ፣ እንድትኖሩ፣ ፍሬአችሁም በእግዚአብሔር ፊት እንዲኖር እመርቃችኋለሁ፣ እንዲሳካላችሁም እመርቃችኋለሁ።
እግዚአብሔር ፈቃዱን በመፈጸም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይባርካችሁ፣ የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ አድብቶ ሊይዝ ከሚፈልግ ስውር ኃጢአት እግዚአብሔር ያድናችሁ በጌታ በኢየሱስ ስም፣ እግርን በመያዝ ወደሚፈለግ እንዳትሔዱ ሊከለክሉ በሚፈልጉ መካከል ባለመያዝ ቀጥሉ፣ ባለመቆም ቀጥሉ፣ በጌታ በኢየሱስ ስም ድል ንሱ፣ አሸንፉ፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፣ ክፉዎችን ገንጥሎ ይስጣችሁ፣ ዝጎችን ደርምሶ ያሳልፋችሁ፣ አጥሮችን፤ ቅጥሮችን ያዘልላችሁ፣ እግዚአብሔር ወዳየላችሁ ሰፊ ሜዳ ያውጣችሁ።

እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተልዕኮ ላይ ትጋት ይጨምርላችሁ፣ እግዚአብሔር በከፈተላችሁ በር ላይ ትጋትን ይጨምርላችሁ፣ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ትዳር ላይ፤ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ኑሮ ላይ፤ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ስራ ላይ፤ እግዚአብሔር ነገር ላይ፤ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ጸጋ እንድትፈጽሙት በሰጣችሁ አገልግሎት ላይ ትጋትን እንዲጨምርላችሁ እፀልያለሁ። አሉባልታ የማታዩ፣ ፈተና የማያስቆማችሁ፣ ወደቀኝም ወደግራም የማትሉ፣ እስከጫፍ የምትጋደሉ እንድትሆኑ፤ ውስጣችሁ ሳይበርድ እስከጫፍ ስትቀጥሉ ራሳችሁን እንድታገኙ፣ በተግዳሮት መሐል፣ በፈተናዎች መሐል፣ በማይመቹ ሁኔታዎችና ጊዜዎች መካከል በጊዜውም አለጊዜውም እስከጫፍ የምትሔዱ፤ ፈጽሞ የምትጋደሉ እንድትሆኑ በጌታ በኢየሱስ ስም እንደዚህ እፀልያለዉ። ባለመቆም ሒዱ፣ ባለመብረድ ሒዱ፣ እስከጫፍ ትጉ፣ በጌታ በኢየሱስ ስም በዚህ ትጋት ይወቋችሁ፣ ባለመድከም ይወቋችሁ፣ ባለመሰልቸት ይወቋችሁ፣ በመጋደል ይወቋችሁ፣ እስከጫፍ በመሔድ ይወቋችሁ። በኢየሱስ ስም ድካምና ምክንያት የማታመጡ፣ እስከጫፍ የምትሰሩ፣ እስከጫፍ የማታቋርጡ፣ የምትጋደሉ፣ ለተሰጣችሁ ተልዕኮ የምትጨክኑ እንድትሆኑ፣ እግዚአብሔር ትጋትን ይስጣችሁ።

እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ትጋት ፈፃሚ ያድርጋችሁ፣ እግዚአብሔር በሰጣችሁ እድሜና በሰጣችሁ በየትኛውም እናንተን በሚፈልግ እንቅስቃሴ ዙሪያ የምትፈጽሙበትን ትጋት ይስጣችሁ፣ ለቤተክርስቲያን ትጋትን ይስጣችሁ፣ የማትበርዱ፣ የማትቀዘቅዙና ዳር የምትደርሱ ያድርጋችሁ። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የእግዚአብሔር ኘሮግራም በህይወታችሁ እንዲከናወን እመርቃችኋለሁ። የእግዚአብሔር ደግነት በእናንተ እንዲሆን፣ በእናንተ እንዲፈራ፣ በእናንተ የሚጠበቅ እንዲገኝባችሁ እመርቃችኋለሁ። እግዚአብሔር አሁንም ጎዳናችሁን ያቅና፤ እናንተ የእናንተ አይደላችሁምና እናንተ የእሱ ናችሁና የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ እንደሚል በጌታ በኢየሱስ ስም ከቆያችሁ፤ ከከረማችሁበት አምላክ ምናልባት እንድታድሩ ብቻ ከሰጣችሁ ቦታ፣ እንድትውሉ ካልሰጣችሁ ቦታ ዘግይታችሁ እንኳን ቢሆን በኢየሱስ ስም ወዳለበት ያውጣችሁ።

ከቆያችሁበት ያውጣችሁ፣ ከኖራችሁበት ያውጣችሁ፣ ካደራችሁበት ያውጣችሁ። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የሚቀጥለውን ለማየት ከነበራችሁበት ያውጣችሁ፣ ከአስተሳሰቦቻችሁ ያውጣችሁ። ልክ ነው ብላችሁ እስከመጨረሻ ከቆማችሁበት ነገር አሁንም ወደሚበልጠውና እርሱ ወዳለበት ልክ ቃሉ እንዲናገር እነርሱ ሁሉ ስለእኔ ይናገራሉና እናንተ ግን ህይወት እንዲሆንላችሁ ወደእኔ ልትመጡ አትወዱምን እንደሚል እየጠቀሱ እንደቀሩ የመጽሐፍትን ቃል እየተናገሩ ከእርሱ እንደቀሩ እንደዛ እንዳትሆኑ፣ እየዘመረ የቀረ፣ እየሰበከ የቀረ፣ በመጽሐፉ ምክንያት celebrate እያደረገ የቀረ ሰው እንዳትሆኑ ልክ ቃሉ እንደሚናገር በጌታ በኢየሱስ ስም ከዛ መውጣት ይሁንላችሁ። እግዚአብሔር ከማይፈለግና ከቆያችሁባቸው፣ ለጊዜው ከሰጣችሁ ቦታ ደግሞ እንደዚያ ቦታ ላይ እንዳትኖሩ እግዚአብሔር መውጣትን ይሰጣችሁ።

በፊታችሁ ይሄዳልና መከተልን ይስጣችሁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድምፁን ያሰማልና ድምፁን መስማት፣ ድምፁን መለየትና የህይወታችሁን መከናወን በምሪት ውስጥ ባለበትና እንዳደረገላችሁ ሁሉ ያለእርሱ የሆነን እንዳታፈሩ፣ ያለእርሱ የሆነ ነገር ስኬት ውስጥ እንዳትገቡና በተሳሳተ መንገድ successful ሆኛለሁ ብላችሁ በተሳሳተ ቦታ ተረጋግታችሁ፣ በተሳሳተ ቦታ ደግሞ እንዳትቆሙ በጌታ በኢየሱስ ስም ስኬታችሁን ባለበት ያድርግላችሁ። እረፍታችሁን ባለበት ያድርግላችሁ፣ ኑሯችሁን ባለበት ያድርግላችሁ። የህይወት በር፣ የአገልግሎት በር፣ የስራ በሮችን በኢየሱስ ስም ይክፈትላችሁ፣ በእርሱ ውጡና ግቡ፣ በእርሱ መሰማሪያን አግኙ። በጌታ በኢየሱስ ስም በዚህ መርቄአችኋለሁ፤ መባረካችሁ ባለበት ይሁንላችሁ፣ ስኬታችሁ እርሱ ባለበት ይሁንላችሁ መውጣት መግባት ይሁንላችሁ። በጌታ በኢየሱስ ስም ይህንን መርቄአችኋለሁ በዚህ ማለዳ፤ የሩቅ ጊዜአችሁን መርቄዋለሁ፣ ሳምንታችሁን መርቄዋለሁ፣ አመታቶቻችሁን መርቄአለሁ፣ እድሜአችሁን፡ ዘመናችሁን በዚህ መርቄአለሁ።

ባለበት ያኑራችሁ፣ በድምፁ ያስተዳድራችሁ፣ በጌታ በኢየሱስ ስም በዚህ መከናወንን አግኙ፣ በዚህ ሙላትን አግኙ፣ በዚህ ደስታን አግኙ፣ በዚህ ማፍራትን አግኙ፤ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በዚህ መርቄአችኋለሁ፤ አሜን። ወዳላችሁ ሂዱ፣ ወዳሳለማችሁ ሂዱ፣ ጨርሱ፣ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተሸናፊ ሳይሆን አሸናፊ፤ አቅም ያጣ ሳይሆን ጉልበታም በመሆን ጨርሱ፣ እግዚአብሔር ጎዳናችሁን ያቅና። እግዚአብሔር ይባርካችሁ፣ ዘመናችሁ የጣፈጠ ይሁን፣ እግዚአብሔር እናንተን፤ የምትኖሩባትን ምድር፣ ከተማ፣ የምትሰሩባቸውን ትምህርት ቤቶችና መስሪያ ቤቶች፣ የምትውሉባቸውን ቤቶች ሁሉ፣ እግዚአብሔር ይባርክ

መልካም ሰንበት። ሚያዚያ 01/08/2015ዓ.ም፤ “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።”
— 2ኛ ቆሮንቶስ 13፥14

#የእግዚአብሔር_አገልጋይ_ማስረሻ_በላይ
መልዕክቱን ለሌሎች አድርሱልኝ።