Get Mystery Box with random crypto!

#የፋሲካ_በዓል ( #የኢየሱስ_ሞት) =============================== #በወንድም | ማርከን ᎢᏌᏴᎬ 🇪🇹

#የፋሲካ_በዓል ( #የኢየሱስ_ሞት)
===============================
#በወንድም_ሀብታሙ_አዲሱ

ደሙን ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ ዘፀ 12፡13
ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷል 1 ቆሮ 5፡7

ፋሲካ ማለት የቃሉ ትርጉም ማለፍ ሲሆን
Hebrew: פֶּסַח
Transliteration: peçach
Pronunciation: peh'-sakh
In English ፡ passover ማለፍ , አንድ ፍርድ በአንድ ነገር ምክንያት ሲያልፍህ ማለት ነው።

በብሉይ (በአሮጌው) ኪዳን እግዚአብሔር በግብፅ ሀገር በባርነት ቀንበር ለሚኖሩ እስራኤላውያን ከፈርዖን የጭቆና አገዛዝ ነፃ የሚወጡበትን እና ከእግዚአብሔር የሞት ፍርድ ማምለጥ የሚችሉበትን መንገድ አዘጋጅቶ ሲያድናቸው የምንመለከትበት ነው።

እኛም ፋሲካችን በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ የቤዛነት ስራ ከእግዚአብሔር ፍርድ እና ከጨለማ ሀይላት አገዛዝ ነጻ መውጣታችንን የሚያሳይ ነው።