Get Mystery Box with random crypto!

ልማድ የገበያ ዕቃ - አናቱ ላይ ጭኖ፣ ጋሪውን ሲገፋ - ግራ አጋቢ ሆኖ። ይህንን ያየ ሰው - ቀ | የመፅሐፍ አለም 🇪🇹🇹

ልማድ

የገበያ ዕቃ - አናቱ ላይ ጭኖ፣
ጋሪውን ሲገፋ - ግራ አጋቢ ሆኖ።
ይህንን ያየ ሰው - ቀርቦ ተጠግቶ፣
ብልሃቱን ሊያሳየው - እጆቹን ዘርግቶ።
ዕቃውን አውርዶ - ጋሪው ላይ አስቀምጦ፣
እንዲሄድ ሲለቀው - ክብደቱን ለውጦ።
ዞር ብሎ ቢያየው - ያልታሰበ ሆነ፣
ጋሪውን ከእነዕቃው - አናቱ ላይ ጫነ።
....
እንዲህ ነው ነገሩ - ምንም ነገር ቢሆን፣
ቶሎ አይለወጥም - ከባድ ልማድ ሲሆን።  

መክብብ ወልደገብርኤል 
February 10, 2022