Get Mystery Box with random crypto!

ማስታወቂያ ስለ ኮርሱ ማብራሪያ  የትምህርቱ ዋና ዓላማ ➺ የግእዝ ቋንቋን ተምረው | ማኅቶት ቲዩብ | Mahtot Tube 🇪🇹

ማስታወቂያ

ስለ ኮርሱ ማብራሪያ 

የትምህርቱ ዋና ዓላማ
➺ የግእዝ ቋንቋን ተምረው ለማያውቁ ከጅማሬው ማሳወቅ እና ቋንቋውን መደበኛ በሆነ መልኩ ለመማር የሚፈልጉትን አነሣሥቶ ጥንታዊ የሆነ ቋንቋዎችን ለዘመኑ ሰዎች በዘመናዊና በቀላል አቀራረብ ማስተማር ነው።

      የትምህርቱ አሰጣጥ
➺ ኮርሱ መሠረታዊ የሆኑ ትምህርቶች የያዘ ሲሆን በ 4 ምዕራፎች ተከፋፍሎ ይሰጣል። የትምህርት ጊዜያት ከሰኞ እስከ ዓርብ ሲሆን ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ ትምህርቶች ይለጠፋሉ። ስለዚህም በሚመችዎት ሰዓት ላይ ገብተው መከታተል ይችላሉ።

➺ ትምህርቶች የሚሰጡባቸው መንገዶች በጽሑፍ ፣ በድምፅ እና በቀጥታ ቮይስ ቻት (Voice Chat) ሲሆን አጠቃላይ ዘመኑን በዋጀ መልኩ ይሰጣል። በዚህም መሠረት በየዕለቱ ለጥቂት ደቂቃ ያክል (10'-15') ሰጥተው ትምህርቱን ያካሂዳሉ ማለት ነው።

➺ ውይይቶች፣ መልመጃዎች፣ የቤት ሥራዎች እንዲሁም የምዘና ፈተናዎች ይካሄዳሉ ። ትምህርቱን በአስፈላጊው ሁኔታ ላጠናቀቁ ተማሪዎችም የማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት (የምስክር ወረቀት) ይሰጣል።  በኮርሱም መጨረሻ ጥሩ ውጤት ላመጡት ሽልማት ይበረከታል።

መመዝገብ የምትፈልጉና  ማንኛውንም አይነት ከታች ባለው አድራሻ  መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ። 

+251914946589
@Asrategabriel