Get Mystery Box with random crypto!

፡ ' ኧረ አንቺ ልጅ አደብ ያዢ! ሳቅሽን ቀንሺ ምንድነው እንደ ጅል ዝም ብሎ መገልፈጥ...' የአ | mahiinah islamic post🌙📿

፡ " ኧረ አንቺ ልጅ አደብ ያዢ! ሳቅሽን ቀንሺ ምንድነው እንደ ጅል ዝም ብሎ መገልፈጥ..." የአባቴ የሁልጊዜ ምሬትናቁጣ የተቀላቀለበት ምክር ነው።

" አይይ አንቺ የደላሽ! ዝም ብለሽ መሳቅ ነዋ?ምናል አንቺን ባደረገን..."ይሄ ደሞ የጓደኞቼ የእለትተእለት ንግግራቸው ነው።
ታዲያ እነሱ እንዲ ሲሉኝ አለማወቃቸው ይበልጥ ያስቀኛል..ሳቄ የውስጥ ቁስሌ እንዳያመረቅዝብኝ መሽፈኛዬ፤ ህመሜን ማስታገሻ ና ማደንዘዣዬ፤ እደሆነ አለማወቃቸው ያስቀኛል።

ፈገግታዬ ለብቸኛዋ ነብሴ አዎ ለዚህች ተረጂ፣ አዳማጭ፣ አጋዠ ለሌላት ነብሴ ጓደኛ፣ደጋፊ፣ድክመቴን እና ሽንፈቴን ደባቂ እንደሆነች አለማወቃቸው ያስቀኛል።

አዎ እንግዲህ እኔ እንዲህ ነኝ። ገልጠህ ካላነበብከኝ በሽፋኔ ብቻ ማታውቀኝ፤ የሸክሜን ክብደት በኔ ሚዛን ካልሆነ የማታውቀው፤ ለሰው ከእንባዬ ይልቅ ጥርሴን ማሳየት የሚቀናኝ ነኝ፤ ከብዙ ችግሮቼ ይልቅ እጄ ላይ ያለችው ትንሿ ነገር ደስታን ምትሰጠኝ፤ ለደቂቃዎች አዝኜ ከመታየት ይልቅ እስከ እድሜ አመሻሽ የውሸቴን እየፈገግኩ መኖርን የምመርጥ ሰው ነኝ።

እንግዲ ውስጤ ቢታመምም፤ ኑሮ ቢያስጠላኝ፣ መተንፈስ ቢሰለቸኝ፤ ልቤ በሰዎች ቢደማ፣ ስብርብሩ ቢወጣም እኔ እንደው የእውነትም ይሁን ለማስመሰልም ቢሆን ጥርሴን ዘግቼ መገልፈጤን አላቆምም!
እየሳቅን

~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~~~